የወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ሶስት አዳዲስ ፕሮግራሞችን ሊከፍት ነው



ሃዋሳ ሀምሌ 3/2004 በአየር ንብረትና አካባቢ ጥበቃ ላይ በድህረ ምረቃ መርሀ ግብር ሶስት አዳዲስ የትምህርት ፕሮግራሞች በቅርቡ እንደሚከፍት የወንዶ ገነት የደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ገለጸ፡፡
የኮሌጁ ሃላፊ ዶክተር ጸጋዬ በቀለ ሰሞኑን ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በሁለተኛና በዶክትሬት የትምህርት ደረጃ የሚከፍታቸው ሶስቱ የድህረ ምረቃ ፕሮግራሞች ዘላቂ የደን አያያዝና አስተዳደር፣ የላንድ ስኬፕ ማኔጅመንት፣ ክላይሜት ቼንጅ ኤንድ ባዮ ኢነርጂ ዴቬሎፕመንት መርሀ ግብር ናቸው፡፡
በሁለተኛ ድግሪ 30 ተማሪዎችን በዶክትሬት ደረጃ ደግሞ 10 ያህል ተማሪዎችን ተቀብሎ ለማስተማር በአሁኑ ወቅት የስርዓተ ትምህርት ቀረጻ፣ ተጨማሪ የመማሪያ ክፍሎች የማስፋፋት ስራ ፣ የመምህራን ምደባና ሌሎች ለመማር ማስተማሩ ስራ የሚያስፈልጉ ሌሎችም ቅድመ ዝግጅቶችን እያደረገ በመሆኑ ፕሮግራሞቹ በቅርቡ እንደሚጀምሩ አስታውቀዋል፡፡
የፕሮግራሞቹ መከፈት የአየር ንብረት፣ የአካካባቢና የተፈጥሮ ሀብት ጥበቃና ልማትን በማጎልበትና በማዳበር ሀገራችንን ከድህነት ለማዋጣት የሚደረገውን ጥረት የሚጠናክር በመሆኑ የመንግስት ከፍተኛ ትኩረትና ድጋፍ አንዳላቸው ገልጸዋል፡፡
ኮሌጁ ነባርና አዳዲስ ፕሮግራሞችን የሚካሄደው በተቀናጀ የምርምርና ጥናት ላይ በመመስረት ህብረተሰቡን በማሳተፍና ችግር ፈቺ መሆናቸውን በማረጋገጥ መሆኑን ገልጸው በተለይ በህብረተሰብ አገልግሎት ዘርፍ ለሴቶች ልዩ ትኩረት እንደሚሰጥ አስታውቀዋል።
የደን ልማት የአፈርና ውሃ ጥበቃ፣ የፍራፍሬና አትክልት ልማት ፣ የጥቃቅንና አነስተኛ ስራዎች ላይ በትንሽ ገንዘብ ብዙ ሃብት ማፍራት በሚቻልበትና የግጭት አፈታት ዘዴዎችን ጨምሮ በርካታ ስራዎችን አጠናክሮ መቀጠሉን ገልጸዋል፡፡ በደንና ተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅነት ለሀገሪቱ ብቸኛና አንጋፋ የሆነው የወንዶ ገነት የደንና የተፈጥሮ ሀብት ኮሌጅ ከተመሰረተ ከ1970 ጀምሮ እሰካሁን ከዲፕሎማ እስከ ዶክትሬት ድግሪ ከ4ሺህ 800 በላይ ተማሪዎችን አሰልጥኖ ማውጣቱን አስታውሰዋል፡፡

http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=705&K=1

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር