ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል።



ሰኔ ፲፰ (አስራ ስምንት) ቀን ፳፻፬ ዓ/ም

ኢሳት ዜና:-ባለፈው ሳምንት ከአዋሳ እና ከሲዳማ ዞን ጋር በተያያዘ የተነሳውን ተቃውሞ ተከትሎ በካናዳ ትምህርታዊ ጉብኝት ሲያደርጉ የነበሩት አቶ ሽፈራው ሽጉጤ ጉብኝታቸውን ትተው በመመለስ ትናንት መግለጫ ሰጥተዋል። ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል።

አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በአዋሳ ጉዳይ ለተነሳው ተቃውሞና ለጠፋው የሰው ህይወት ችግሩን የቀሰቀሱትን ለፍርድ እንደሚያቀርቡ ለክልሉ ራዲዮ ተናግረዋል።

አቶ ሽፈራው የአዋሳ ጉዳይ በሀሳብ ደረጃ ተነሳ እንጅ ውሳኔ ያልተሰጠበት በመሆኑ ህዝቡ እንዲረጋጋ ጠይቀዋል። ከህዝቡና ፣ ከሀገር ሽማግሌዎችና ከሚመለከታቸው ሰዎች ጋር በመሆን ጉዳዩን እንደሚያብላሉትም ገልጠዋል። ፕሬዚዳንቱ ሰሞኑነ በተነሳው ግጭት የሰው ህይወት መጥፋቱንና ንብረት መውደሙን ቢገልጡም ሀላፊነቱን ለመውሰድና ይቅርታ ለመጠየቅ አልሞከሩም፣ ይልቁንም ችግሩን የፈጠሩት የተቃዋሚ አባላት ፓርቲና አንዳንድ ባለሀብቶች መሆናቸውን በመግለጥ ህጋዊ እርምጃ ለመውሰድ መዘጋጀታቸውን ነው የተናገሩት። ሌሎች ወገኖች ግን ግጭቱን የቀሰቀሱት የደኢህዴግ ኢህአዴግ አባላት ናቸው::

አዋሳ አሁንም በፌደራል ፖሊስ እየተጠበቀች ነው። ወደ ይርጋለም በሚወስደው መንገድ ላይ ቁጥራቸው ከፍተኛ የሆነ የፌደራል ፖሊስ አባላት ሰፍረው ይገኛሉ።

ይህ በእንዲህ እንዳለ ባለፈው ሳምንት በሲዳማ ዞን የተነሳው ተቃውሞ ወደ ዘር ግጭት ሊያመራ ይችላል የሚለው የኢሳት ዘገባ የሲዳማ ተወላጆች ያነሱትን ዋነኛ ጥያቄ ያልዳሰሰ ነው በማለት የሲዳማ ተወላጆች አስተያየቶቻቸውን ልከዋል። ለጉዳዩ ቅርበት አለን የሚሉ ወገኖች ለኢሳት በላኩት መልእክት የአዋሳ ህዝብ መሰረታዊ ጥያቄ የፍትህ ጥያቄ በመሆኑ በሌሎች አካባቢዎች ከሚነሱት ጥያቄዎች የተለየ አይደለም።

Comments

Popular posts from this blog

Israel Eshetu back to his childhood club

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት