የሲዳማ ዞን ነዋሪዎች የተለያዩ ፖለቲካዊ ጥያቄዎቻቸውን ለምመለከተው መንግስታዊ ኣካል በሰላማዊ መንገድ ለማቅረብ እንዲያስችላቸው በየወረዳዎች ደረጃ የሚወክሏቸውን ተወካዮች በመምረጥ ላይ ሲሆኑ፤ የክልል ባለስልጣናት በበኩላቸው ህዝብ እንዲረጋጋ በመጠየቅ ላይ ናቸው::



በየኣስር ኣመቱ በክልል ባለስልጣናት እየረቀቀ የሚቀርበውን የሃዋሳን ከተማ በኮታ የማስተዳደር ጥያቄ ለኣንዴና ለመጨረሻ ጊዜ እልባት እንዲያገኝ ታስቦ የተጀመረውን የክልል ጥያቄ ከዳር ለማድረስ የተቀጣጠለው ህዝባዊ ንቅናቄ እንደቀጠለ ሲሆን: የሲዳማ ህዝብ ያሉትን የመልካም ኣስተዳደር ችግሮን እና የክልል ጥያቄውን በሰላማዊ መንገድ ለሚመለከተው መንግስታዊ ኣካል ለማቀረብ እንቅስቃሴ ጀምሯል::

የበንሳ ወረዳ የህዝብ ንቅናቄ ኣባላት የወረዳው ህዝብ በመወከል ህዝባዊ ጥያቄዎችን የሚያቀረቡ ሽማግሌ ተወካዮቻቸውን የመረጡ ሲሆን ሌሎች የዞኑ ወረዳዎችም የባንሳ ወረዳ ኣረኣያ በመከተል ተወካዮቻቸውን በመምረጥ ላይ መሆናቸው ተገልጿል::

ሰሞኑን በዞኑ ኣስተዳዳሪ የተመራው ኣንድ ከሲዳማ ዞን እና ከክልል ቢሮዎች የተወጣጣ የሲዳማ ልኡካን ቡድን ወደ ኣዲስ ኣበባ ኣቅንቶ የተመለስ ሲሆን በዛሬው ቀን ሙሉ ቀኑን የዞን ካቢኔዎች ስብሰባ ላይ በመሆናቸው ተጓዧቹ ከፈዴራል መንግስት ባለስጣናት የተሰጣቸውን ምላሽ ለመስማት ኣልተቻለም:: ሆኖም ለቀረቡት ጥያቄዎች የፈዴራል መንግስት ኣጥጋቢ ምላሽ ሳይሰጥ እንዳልቀረ ከውስጥ ኣዋቅ ምንጮች ያገኝናቸው መረጃዎች ያሳያሉ::  

በዛሬው እለት መላዋ ሲዳማ በተለይ የሃዋሳ ከተማ ምንም እንኳን በከፍተኛ ጥበቃ ስር ያለ ቢሆንም በከተማዋ ጸጥ ረጭ ብለው የነበሩ ንግድና ሌሎች እንቅስቃሴዎች ወደ ቀደሞው እየተመለሱ መሆናቸው ተገልጿል:: 

በሌላ በኩል የክልሉ ፕሬዚዴንት ኣቶ ሽፈራው ሽጉጤ ከክልሉ ኤፍ ኤም ሬድዮ ጋር ባደረገው ቃለ ምልልስ ህዝቡ እንዲረጋጋ መልእክት ያስተላላፉ ሲሆን፤ በደኢህዴን ተዘጋጅቶ ወሳኔ ሳይሰጥበት በድንገት ወደ ህዝብ ጆሮ የደረሰው እና ለተፈጠረው ህዝባዊ ንቅናቄ መሰረት የሆነው ጽሁፍ “በሬ ወለደ ወሬ” ነው በማለት ኣጣጥለውታል::

የራሳቸው ሰዎች ያዘጋጁት እና በብዙ ኮፒዎች ተዛዝተው ከህዝብ እጅ የገባው ባለ 15 ገጽ የማወያያ ጽሁፍ እንዴት ሆኖ በሬ ወለደ ወሬ ልሆን እንደቻለ ብዙም ያሉት ነገር ባይኖርም፤ የማወያያ ጽሁፉን መሰረት ተደርጎ የሚወሰድ ወሳኔ እንደሌለ ግን ተናግረዋል::

በተጨማሪም የሲዳማ ህዝብ እንግዳ ተቀባይ እና ከሌሎች ብሄርና ብሄረሰቦች ጋር ለብዙ ኣመታት በሰላም የኖረ ህዝብ መሆኑን ግልጸው በሲዳማና በሌላው ህዝብ መካከል ግጭት ለመፍጠር ኣሉባልታ የምያናፍሱትን ነቅፈዋል:: 

ኣክለውም በሲዳማ ህዝብ የተነሱትን የተለያዩ የመልካም ኣስተዳደር ጥያቄዎች ለማስተናገድ ዝግጁ መሆናቸውን ኣስታውቀዋል::  
    

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር