በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ በህዝብ የሚመራ የጤና ልማት ስራ እያከናወነ መሆኑን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


በሲዳማ ዞን ዳራ ወረዳ በህዝብ የሚመራ የጤና ልማት ስራ እያከናወነ መሆኑን የወረዳው ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
ለዚሁም ጽህፈት ቤቱ በ16ቱ ጤና ኤክስቴንሽን ፖኬጆች ዙሪያ አዲስ የትግበራ ስልት በመንደፍ ለጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ለባለሙያዎችና ለሱፐርቫይዘሮች ስልጠና እየሰጠ እንደሚገኝ ተጠቁሟል፡፡
በጽህፈት ቤቱ በሽታ መከላከልና ጤና ማጐልበት ዋና ስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ማቴዎስ ማልጌ በወረዳው የትግበራ ስልቱን ውጤታማ ለማድረግ በሁሉም ቀበሌያት የጤና ልማት ሰራዊት መገንባት ወሳኝ መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዋናነትም የእናቶችና ህፃናት ሞትን ለመቀነስ እንደሚሰራ ጠቁመው በዚሁ መሰረት ነፍሰጡር እናቶች በወረዳው በሚገኙ ጤና ጣቢያዎች ተጠቃሚ እንዲሆኑ ግንዛቤ በማስጨበጥ ረገድ ትኩረት ተሰጥቶ ይሰራል ብለዋል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሸን ጉዳዮች ጽሀፈት ቤት እንደዘገበው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ