በሀዋሣ ታቦር ክፍለ ከተማ የፋራ ቀበሌ አስተዳደር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት የምሳ ግብዣ አደረገ:


በሀዋሣ ታቦር ክፍለ ከተማ የፋራ ቀበሌ አስተዳደር የፋሲካ በዓልን ምክንያት በማድረግ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት የምሳ ግብዣ አደረገ::የቀበሌው ዋና አስተዳዳሪ አቶ በልጉዳ ባሪሳ በዝግጅቱ ላይ እንዳሉት የሁላችንም የጋራ ጠላት የሆነውን ድህነትና ኃላቀርነትን ለማሸነፍ በተሰማራንበት መስክ የበኩላችንን ድርሻ ልንወጣ ይገባል::በቀበሌው ከ47ዐ በላይ አረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት ለምሳ ግብዣው በመጥራት በአሉን በጋራ ማክበር መቻላቸውን አስረድተዋል::
ድጋፍ ያደረጉ ባለሀብቶች በበኩላቸው አመት በዓልን ጠብቆ ለአረጋዊያንና ወላጅ አጥ ህፃናት ከሚደረገው ድጋፍ ባሻገር በዘላቂነት ህይወታቸውን ለመቀየር አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ ተናግረዋል::የሀዋሣ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ተዋካይ አቶ አየለ ኪአ ቀበሌው እንደዚህ አይነት ዝግጅት በራሱ ተነሳሽነት ማካሄዱ የሚያመሰግነው መሆኑን ገልፀው፤ ሌሎችም አርአያነቱን ሊከተሉ እንደሚገባ አውስተዋል::
የፋራ ቀበሌ ከአመት በዓል ዝግጅቶች ባለፈ የችግረኛ ወገኖችን  ተጠቃሚነት የሚያረጋግጥ ስራ እየሰራ መሆኑን ተገልጿል ሲል ባልደረባችን ወንድወሰን ሽመልስ ዘግቧል::

Comments

Popular posts from this blog

ስለከሸፈው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ጥራዝ አንዳንድ ነጥቦች

SIDAMA Micro-Finance Institution

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት