ባለፉት 7 ወራት ከልዩ ልዩ የገቢ አርእስቶች ከ128 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


ባለፉት 7 ወራት ከልዩ ልዩ የገቢ አርእስቶች ከ128 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡አፈፃፀሙ ካለፈው ዓመት ብልጫ ያለው መሆኑንም ገልፀዋል፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሻለ ቡላዶ እንዳሉት ከመደበኛ ገቢ 116 ሚሊዮን ከማዘጋጃ ቤቶች ደግሞ 12 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡
የንግዱ ማህበረሰብ በታክስ ክፍያ ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ማደግ ለገቢው መጨመር አስተዋፅኦው የጐላ እንደነበር መግለፃቸውንም የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ