በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በግማሽ የበጀት ዓመት በአፈፃፀማቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ 6 ቀበሌየት የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ፡፡


በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በግማሽ የበጀት ዓመት በአፈፃፀማቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ 6 ቀበሌየት የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ፡፡የወረዳው ምክር ቤት በ6 ወር የእቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከቀበሌ አፈ ጉባኤዎች፣ ሊቀነ መናብርትና ሥራ አስኪያጆች ጋር ሰሞኑን ውይይት አካሂዷል፡፡
የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ በላይነሽ ብዙነህ እንደተናገሩት ቀበሌያቱ ሊሸለሙ የቻሉት ደረጃውን የጠበቀ የቀበሌ ምክር ቤት በማቋቋም የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ፈጣን አገልግሎት መስጠት በመቻላቸው ነው፡፡
ቀበሌያቱ ለተለያዩ የልማት ሥራዎት የቅርብ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እንዲሁም በየወሩ የሸንጎ አባላት ጉባኤ በማካሄድ ለወረዳ ምክር ቤት ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት በማቅረባቸው ጭምር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ