በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በተያዘው የምርት ዘመን ከ171 ሺህ ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ::




በሲዳማ ዞን ሸበዲኖ ወረዳ በተያዘው የምርት ዘመን ከ171 ሺህ  ኩንታል በላይ ምርት መሰብሰቡን የወረዳው አስተዳደር አስታወቀ::
የወረዳው ዋና አስተዳዳሪ አቶ ታረቀኝ ጋቤራ ለወረዳው ምክር ቤት 3ኛ ዙር 11ኛ መደበኛ ጉባኤ ባቀረቡት የሥራ አፈፃፀም ሪፖርት ምርቱ የተሰበሰበው በ6 ሺህ 5 መቶ 9ዐ ሄክታር መሬት ላይ ከተመረቱ በቆሎ፣ ጤፍ፣ ስንዴ፣ ገብስ፣ ቦሎቄና ከሌሎች ሰብሎች መሆኑን ገልፀዋል::በምርት ዘመኑ 625 ሺህ የቡና ችግኞች ለበልግ የተከላ ወቅት መዘጋጀታቸውን የጠቆሙት ዋና አስተዳዳሪው በ156 ሄክታር መሬት ላይ የነበሩ ያረጁ የቡና ተክሎች ተጐንድለዋል::2ዐ ኩንታል የቡና ዘር መዘጋጀቱን ተናግረዋል::
በወረዳው የተሻሻሉ ምርጥ የከብት ዝሪያዎችን ለማርባት 82 ከብቶች በሰው ሠራሽ ዘዴ፣ 447 ደግሞ በኮርማ መዳቀላቸውን አውስተው የእንስሳት በሽታን አስቀድሞ ለመከላከል በተደረገው ጥረት ለ6 መቶ ከብቶች ክትባት መሰጠቱን ገለፀዋል::ሪፖርተራችን ካሳ ጀንቦላ ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው::

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ