የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


የእናቶችንና የህፃናትን ሞት ለመቀነስ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ታደሰ አነቦ ባለፉት ወራት የእናቶችን ሞት ለመቀነስ በተደረገው እንቅስቃሴ ለ2 ሺህ 985 እናቶች የቅድመ ወሊድና የድህረ ወሊድ ምርመራ እንዳደረገላቸውም ተናግረዋል፡፡
14 ሺህ 49ዐ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን አብራርተው ቁጥራቸው በተጨማሪም እናቶች በባለሙያ የተደገፈ የወሊድ አገልግሎት እያገኙ መሆናቸውን ጠቁመዋል፡፡በአንፃሩ የህፃናትን ሞት ለመቀነስ በተደረገው ርብርብ 3 ሺህ 383 ህፃናት የተለያዩ በሽታዎችን የሚከላከል ክትባት ማግኘታቸው መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ