በይርጋለም ከተማ በትምህርቱ ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ገለፁ :


በይርጋለም ከተማ በትምህርቱ ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርት ውጤት እያስገኘ መሆኑን የከተማዋ ከንቲባ ገለፁ፡፡የይርጋለም ከተማ ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ተክለስላሴ ዌኬሬ እንዳሉት ሀገሪቱ የተያያዘችውን የትራንስፎርሜሽን እቅድ ለማሣካት የሚቻለው የምክር ቤት አባላት በግንባር ቀደምትነት ተሳታፊ ሲሆኑ ነው ብለዋል፡፡
የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አቶ ወንድወሰን ቦልካ በ6 ወራቱ የስራ ክንውን መከላከልን መሰረት ያደረገው የጤና ፖሊሲ ውጤት እያስገኘ መሆኑን ገልጿል፡፡በተለይም በከተማ የጤና ኤክስቴንሽን ረገድ፡፡በትምህርት ዘርፍ የጐልማሶች ትምህርትን ለማጠናከር በተደረገው ጥረትም ውጤታማ ተግባር መከናወኑን ተናግረዋል፡፡ምክር ቤቱ የ3 ካቢኔ አባላትን ሹመት ያፀደቀ ሲሆን በቀጣይም ለሚሰሩ ተግባራት አቅጣጫ በማስቀመጥ መጠናቀቁን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ