በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ አስተዳደር ባለፈው ግማሽ የበጀት ዓመት በህብረተሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ተቃሚነት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ፡


በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ አስተዳደር ባለፈው ግማሽ የበጀት ዓመት በህብረተሰቡ ማህበራዊ፣ ኢኮኖሚያዊና በመልካም አስተዳደር ተቃሚነት ላይ ትኩረት ያደረጉ ተግባራት ማከናወኑን አስታወቀ፡፡የአስተዳደሩ ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ተመስገን መንግስቱ እንደገፁት በተጠናቀቀው ግማሽ የበጀት ዓመት 13ዐ የህዝብ አቤቱታዎች ለወረዳው አስተዳደር ቀርበው እልባት ላይ እንዲደርሱ ተደርጓል፡፡
በተለያዩ ምክንያቶችና ጊዜያት የአካል ጉዳት ለደረሰባቸው ሰዎች ሰው ሠራሽ እግርና ባለ ብረት የአካል ድጋፍ ተገዝቶ አንደተሰጣቸው ጠቁመዋል፡፡የገንዘብ ችግር ያለባቸው 28 ሰዎች በይርጋለም ሆስፒታልና ጤና ጣቢያ ነፃ የህክምና አገልግሎት እንዲያገኙ መደረጉን አቶ ተመስገን መግለፃቸውን የዘገበው የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት ነው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ