ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታው ስራ እየተከናወነ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡


ከ2 ነጥብ 5 ሚሊዮን በሚበልጥ ወጪ የንፁህ መጠጥ ውሃ ግንባታው ስራ እየተከናወነ መሆኑን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ውሃ፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ዘለቀ በላይነህ እንደገለፁት ህብረተሰቡን ከውሃ ወሊድ በሽታ ለመታደግና የንፁህ መጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ የዘጠኝ አነስተኛና መለስተኛ የውሃ ተቋማት ግንባታዎች እየተካሄደ ይገኛል ብለዋል፡፡በአሁኑ ጊዜ እየተገነቡ ከሚገኙ መካከልም 1 የጥልቅና 3 መለስተኛ የውሃ ጉድጓድ እንዲሁም 5 የአዳዲስ ምንጮች ግንባታ እንደሚገኝ አስተባባሪው አስረድተዋል፡፡ሲል መለሰ ሱኩሌ ከበንሳ ቅርንጫፍ ጣቢያ ዘግቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ