የሴቶች ማሕበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት እየጐለበተ መምጣቱን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች መምሪያ ገለፀ፡፡


መምሪያው የማርች 8 በዓልን ከከተማው የተውጣጡ አመራሮች፣የየክፍለ ከተማው ተወካዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሮ ውሏል፡፡

ሴቶች ሕገመንግስቱ ባረጋገጠላቸው መብቶችና ጥበቃወች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው እንዲሁም ከተለያዩ ፆታን መሠረት ካደረጉ ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የመጠበቅና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል፡፡
በዓሉ የሀገራችን ሴቶች በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸው መብቶች ለማስከበር የትግል አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት የተጀመረውን የሠላምና የዴሞክራሲያዊ ጐዞ እንዳይቀለበስ ለማድረግ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ዘርፎች በንቃት ተሳትፈው እና ተጠቃሚ ለመሆን ትግላቸውን የሚያጠናክሩበት ነው፡፡
የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ-ጉባኤ አቶ ደምሴ ዶንጊሶ በዓሉን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት በሀገሪቱ በክልሉና ሆነ በከተማው ከተመዘገቡ ፈጣን የኢክኖሚ ዕድገት የሴቶችን ተሳተፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡
ሕገ መንግስቱ መሠረት በማድረግም በክልሉ የቤተሰብ ሕግ ተሻሽሎ መውጣቱ ሴቶተ ቤተሰብን በመገንባት ረገድ እኩል መብትና ኃላፊነት እንዲሃራቸው ማድረጉ ይጠቀሳል ብለዋል፡፡
የከተማው ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ሥምረት ግርማ በበኩላቸው በዓሉ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማጐልበቱ በተጨማሪ ሴቶች በድንበር፣በኃይማኖት፣በቀለም፣በቋንቋ እንዲሁም በባሕል ሳይለያዩ የሚደርሱባቸውን ጭቆናና መማሎ የሚያወግዙበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡
በዕለቱም ሥርዓተ ፆታና ልማት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያለው ፋይዳ እንዲሁም የሴቶች የተደራጀ ተሳትፎና ንቅናቄ ለዕቅዱ ስኬት ያለው ሚና በሚመለከት ፁሑፍ ቀርቦ ውይይት በተሰብሳቢዎች ተደርጓል፡፡
ከዚህም ሌላ በከተማው ከሚገኙ የግልና የመንግስት ትምህርት ቤቶች ጥሩ ውጤት ላስመዘገቡ ሴቶች ሽልማት የተሰጠ ሲሆን የተለያዩ ኪነ ጥበባዊ ዝግጅቶች በመድረኩ ቀርቧል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር