እየተመዘገበ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል የመንግስት ተቋማት የተሻሉ የአሰራር ሥርዓቶችን መዘርጋት እንዳለባቸው የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቀ፡፡


በዞኑ የሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ጽሕፈት ቤቶች የ6 ወራት እንቅስቃሴ ሲገመገም ዋና አስተዳዳሪው እንዳሉት የመንግስት ተቋማት ፈጣን ልማትና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥና ለማስፈን የሚያስችል አደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓትን መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡

በየደረጃው የሚገኙት የሲቪል ሰርቪስ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሠራተኛውን ነባርና ኋላ ቀር አስተሳሰብ አሰራሮችን ወደ ልማታዊና 

ዴሞክራሲያዊ መስመር ማስገባት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡

ተቋማቱም በየጊዜው የአፈፃፀም ብቃታቸውን በመፈተሽና በመለካት መገምገም እንዳለባቸው መግለፃቸውንም ከዞኑ ባሕል ቱሪዝምና 

የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ