በከተማዋ ያሉ የተለያዩ አደረጃጀቶች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ ውጤታማ እንዲሆን ድጋፉን አጠናክሮ እንደሚቀጥል የሃዋሳ ከተማ አስተዳደር አስታወቀ፡፡


የከተማው የህዝብ ግንኙነትና አደረጃጀት ዘርፍ ሃላፊ አቶ ተገኔ ታደሰ የሴቶችንና የወጣቶችን አደረጃጀት ለማጠናከር በተካሄደው ውይይት ላይ እንዳመለከቱት የአምስት ዓመቱን እቅድ ለማሳካት እያንዳንዱ አደረጃጀት ሚናውን ሊወጣ ይገባል፡፡
እነዚህ አደረጃጀቶች የሚያደርጉት እንቅስቃሴ መልካም ቢሆንም በቂ አይደለም ያሉት አቶ ተገኔ በሚደረግላቸው ድጋፍ የልማት ተዋናይነት ሚናቸውን መወጣት ይገባቸዋል፡፡
የሃዋሳ ከተማ ሴቶች፣ ህጻናትና ወጣቶች መምሪያ ሃላፊ ወይዘሪት ስምረት ግርማ በበኩላቸው መድረኩ ውስጣዊና ውጫዊ ችግሮችን በመለየት የተጠናከረ አደረጃጀት ለመፍጠር  ታስቦ መዘጋጀቱን ተናግረዋል፡፡
በከተማዋ ከሚገኙ የተለያዩ አደረጃጀቶች የተወጣጡ አካላት የመድረኩ ተሳታፊ ነበሩ ሲል ደስታ ወ/ሰንበት ዘግቧል፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ