Posts

Featured Post

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ

Image
በባህርዳር ከተማ ተገኝተው ልምዱን ያካፈሉት “የሲዳማ ብሔራዊ ክልላዊ መንግስት የፍትህ ቢሮ ም/ሀላፊና የህግ ጉዳዮች ዘርፍ ሀላፊ ክብርት ወ/ሮ አሽሌ ዳንኤል ሲሆኑ:- እንደ ሲዳማ ብሔር ይህ ቱባ ባህል የከበረ ባህል ሲሆን ዕድሜ ጠገብና እጅግ የሚያኮራ እንዲሁም ለዕርቅና ለሰላም ግንባታ ትልቅ ሚና ያለው ባህል ብለዋል። "አፊኒ" ትልቅ የሀገር እሴት መሆኑንና ይህንንም ባህላዊ የዳኝነት ስርአትን የሚደግፍ የማህበረሰብ ፍትህ አገልግሎትን ለማጠናከር የሚረዳ አዋጅ በሲዳማ ክልል ምክር ቤቱ እንዳፀደቀ ገልፀዋል:: በመድረኩ የኢፌዲሪ ፍትህ ሚኒስቴር ዴኤታ ክቡር ዶ/ር ኤርሚያስ የማነብርሐን, የክልሉ ም/ቤት አፈጉባኤ ክብርት ፋንቱ ተስፋዬና የጠቅላይ ፍርድ ቤት ፕሬዝደንት ክቡር አለምአንተ አግደዉ ተገኝተው መልዕክት አስተላልፈዋል:: የማህበረስብ አቀፍ ፍትህ አገልግሎት ሚናን አስመልክቶ የሲዳማ ብሔር "አፊኒ" ባህላዊ ዳኝነት ስርዓትና ተሞክሮን በተመለከተ ህብረተሰቡ ዘመናዊ የዳኝነት ስርዓትን በማይቃረን መልኩ ሳይጉላላና ለአላስፈላጊ ወጪ ሳይዳረግ ፍትህ እንዲያገኝ በማሰብ እየተሰራ ያለ መሆኑ ተገልፆአል:: በአማራ ክልል ባህርዳር ከተማ የተዘጋጀው መድረክ ላይ ክልሉ የራሱን የረቂቅ ሞዴል ህግ እንዲሁም ሌሎች የጥናት ጽሁፎችና የኦሮሚያ ክልል ልምድም ቀርቦ በሀገር ሽማግሌዎች: የሐይማኖት አባቶችና ምሁራን ሠፊ ውይይት ተደርጎአል። የባህል ፍርድ ቤቶችን ስለማቋቋምና እዉቅና ስለመስጠት፣ የባህላዊ ግጭት መፍቻ ዘዴዎች ዳሰሳ መደረጉ ስርአቱን ለማጠንከር ማህበረሰዋዊና ብሎም ሀገራዊ ሰላምን አብሮነትን የሚያጠነክር መሆኑም ተነስቶ ከሲዳማና ከኦሮሚያ ክልል ለቀረቡ ልምዶች ላቅ ያለ ምስጋና ተችሮአል:: FastMereja.com  

የፍቅር እና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነውን የሲዳማ ህዝብ "ዳዮኤ ቡሹ" ለማስተዋወቅ እየተሰራ ነው

Image
  በቢሮው ድጋፍ የሚሰራው "የዳዎኤ ቡሹ ፊልም የማስጀመሪያ መርሐ ግብር ዛሬ በሀዋሳ ከተማ ተካሂዷል። በመርሃ ግብሩ ላይም የተገኙት የሲዳማ ክልል ባህል ቱሪዝም እና ስፖርት ቢሮ ኃላፊ የሆኑት አቶ ጃጎ አገኘሁ የፍቅር እና የአብሮነት ተምሳሌት የሆነውን የሲዳማ ህዝብን "ዳዮኤ ቡሹ" ለማስተዋወቅ እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ። የፊልሙ ደራሲ እና አዘጋጅ የሆኑት ዶ/ር በዛብህ ብርሃኑ ፊልሙን በአጭር ቀናት ውስጥ ሰርቶ ለማጠናቀቅ እና ቢሮው የሰጠውን ሃለፊነት ለመወጣት ቅድመ ዝግጅት ማጠናቀቁን ተናግረዋል። በተጨማሪም የፊልሙ ተዋናዮችም ፊልሙ ላይ ለመሳተፍ በመመረጣቸው ደስታ እንደተሰማቸውና የሲዳማን እምቅ ባህልን በሙያቸው ቀሚመው ለማስተዋወቅ መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል ። በፊልሙ ላይም በተወዳጅ 9ኛው ሺ ተከታታይ ድራማ ላይ የምናውቃቸው ተወዳጅ ተዋናዮች አርቲስት አበበ ተምትም ፣ አርቲስት ስናፍቅሽ ተስፋዬ እንዲሁም በተለያዩ ፊልሞች ላይ የምናውቀው አርቲስት ፈለቀ ካሳ እንዲሁም ከ50 የሚበልጡ ተዋናዮች እንደሚሳተፉበት ታውቋል።

የአንካራው ስምምነት የኢትዮ-ሶማሊላንድ ስምምነትን ይሽራልን?

Image
ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለአንድ ዓመት የቆዩበትን ውጥረት በቱርክ አደራዳሪነት በአንካራ ማርገባቸው ለሁለቱ አገራት እና ለአፍሪቃ ቀንድ እፎታን የሰጠ ይመስላል። ለስምንት ሰዓታት የዘለቀዉ ታሪካዊ የተባለው የአንካራው ስምምነት ኢትዮጵያ የሶማሊያን አገራዊ ሉዓላዊነት ባከበረ መንገድ ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር እንደምታገኝ ያመላክታል፤ ተብሏል። የአንካራው ስምምነት የኢትዮ-ሶማሊላንድ ስምምነትን ይሽራልን? ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ለአንድ ዓመት የቆዩበትን ውጥረት በቱርክ አደራዳሪነት በአንካራ ማርገባቸው ለሁለቱ አገራት እና ለአፍሪቃ ቀንድ እፎታን ሰጥቷል፡፡ በቱርክ ፕሬዝዳንት ሬሲፕ ጣይር ኤርዶሃን አሸማጋይነት ስምንት ሰዓታትን የፈጀው ታሪካዊ የተባለው የአንካራው ስምምነት ኢትዮጵያ የሶማሊያን አገራዊ ሉዓላዊነት ባከበረ መንገድ ደህንነቱ የተጠበቀ የባህር በር እንደምታገኝ ያወሳል፡፡ ይህ የአንካራው ስምምነት ኢትዮጵያ እየተገባደደ ባለው የጎርጎሳውያን ኣመት መጀመሪያ ከ11 ወራት በፊት እራሷን እንደ አገር ከምትቆጥረውና ሶማሊያ ግን የግዛቷ አካል አድርጋ ከምትመለከተው ከራስ ገዟ ሶማሊላንድ ጋር ያሰረችው የመግባቢያ ስምምነት ስለመሻር አለመሻሩ ግን በግልጽ የተቀመጠ ነገር አልተሰማም፡፡ ኢትዮጵያ እና ሶማሊያ ባለፈው ዓመት ታህሳስ መጨረሻ ኢትዮጵያ ከራስገዟ ሶማሊላንድ ጋር የወደብ አጠቃቀም ስምምነት ማሰሯን ተከትሎ የለየለት ዲፕሎማሲያዊ መካረር ውስጥ ገብተው ዓመቱን ሙሉ ዘልቀዋል፡፡ ቱርክ ሁለቱን አገራት ከዚህ በፊት በሁለት ዙር በመጥራት ችግሩን በዲፕሎማሲያዊ መንገድ ለማርገብ ያደረገችው ጥረትም አልሰምር ብሎ፤ አሁን በሶስተኛ ዙር ለመጀመሪያ ጊዜ የኢትዮጵያውን ጠቅላይ ሚኒሰርትር ዐቢይ አህመድን ከሶማሊያው አቻቸው ፕሬዝዳንት ሀሰን ሼኸክ ሞሀመድ ጋር ፊትለፊት በማገናኘ...

በሲዳማ ክልል ከ489 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ ነው

Image
በሲዳማ ክልል ሁለት ወረዳዎች ከ489 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የንጹህ መጠጥ ውሃ ፕሮጀክቶች ሊገነቡ መሆኑ ተገለጸ። ለፕሮጀክቶቹ የውሃና ኢነርጂ ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው ዲንጋሞ (ዶ/ር)ን ጨምሮ የፌዴራልና የክልል የመንግስት የስራ ኃላፊዎች በተገኙበት ዛሬ የመሰረተ ድንጋይ ተቀምጧል። በዚህ ወቅት ሚኒስትር ዴኤታ አምባሳደር አስፋው እንደገለጹት፤ የአንድ ቋት የመጠጥ ውሃና ሳንቴሽን ፕሮግራም አካል በሆነው በዋን ዋሽ ፕሮግራም በአገሪቱ የተለያዩ ወረዳዎችና ከተሞች የሚከናወኑ የውሃ ፕሮጀክቶች ይኖራሉ። ዛሬ በሲዳማ ክልል ሁለት ወረዳዎች መሰረት ድንጋይ የተቀመጠላቸው የውሃ ፕሮጀክቶች በዋን ዋሽ እና በአፍሪካ ቀንድ ዘላቂ የከርሰ ምድር ውሃ ፕሮግራሞች አማካይነት የሚከናውኑ መሆኑን ተናግረዋል። ለፕሮጀክቶቹ ግንባታ ከ489 ሚሊዮን ብር በላይ መመደቡን አስታውቀዋል። የውሃ ፕሮጀክቶቹ 49 የሚደርሱ የውሃ ቦኖዎች፣ ዘመናዊ መጸዳጃ ቤቶች፣ የእንስሳት ውሃ ማጠጫዎችን እንዲሁም የጤናና ትምህርት ተቋማትን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ግንባታዎችን እንደሚያካትቱ አብራርተዋል። የሲዳማ ክልል ውሃ ማዕድንና ኢነርጂ ቢሮ ሃላፊ ኢንጂነር ከበደ ጋኖሌ በበኩላቸው፤ በሃዋሳ ዙሪያና ቦርቻ ወረዳዎች የሚገነቡት የውሃ ፕሮጀክቶች ከ60 ሺህ የሚበልጡ ሰዎችን ተጠቃሚ እንደሚያደርጉ ገልጸዋል። ከዚህ ቀደም የነበረውን ከፍተኛ የውሃ ችግር የሚያቃልል መሆኑን ተናግረዋል። ሁለቱንም ፕሮጀክቶች በአንድ ዓመት ጊዜ ውስጥ በማጠናቀቅ ህብረተሰቡን ተጠቃሚ ለማድረግ በትኩረት ይሰራል ብለዋል። ከአካባቢው ነዋሪዎች መካከል አቶ ፍሬው ፈለቀና አቶ አለሙ ሳና፤ የውሃ ችግራቸውን ለማቃለል የፌደራልና የክልሉ መንግስት ላደረጉት ጥረት ምስጋና አቅርበዋል። የውሃ ፕሮጀክቶቹ በተያዘላቸው ጊዜ እንዲጠናቀቁ የሚጠበቅ...

9ኛው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የ2017ዓ.ም የመጀመሪያ ዙር ውድድር በሀዋሳ ከተማ እሁድ ታህሳስ 6 እንደሚጀመር ተገለፀ።

Image
በሀገራችን ካሉ ስኬታማ እና ውስን ፕሪሚየር ሊጎች ከግንባር ቀደሞቹ ተርታ የሚገኘው የኢትዮጵያ እጅ ኳስ ፕሪሚየር ሊግ የ2017ዓ.ም መርሀ-ግብር ሊጀመር እንደሆነ ተገልጿል። ውድድሩ በ10 ክለቦች መካከል የሚካሄድ ሲሆን የመቻል፣ የኦሜድላ፣ የፌደራል ማረሚያ፣ የቂርቆስ፣ የኮልፌ ቀራንዮ፣ የመቀሌ 70 እንደርታ፣ የከንባታ ዱራሜ፣ የፋሲል ከነማ፣ የሚዛን አማን እና የባህር ዳር ከነማ እጅ ኳስ ክለብ ይሳተፋበታል። ውድድሩ በሀዋሳ፣ በአዲስ አበባ እና በተመረጡ የሀገራች ከተሞች አመቱን ሙሉ የሚካሄድ ሲሆን መክፈቻ ፕሮግራሙ እሁድ ታህሳስ 6, 2017ዓ.ም የክብር እንግዶች በተገኙበት በድምቀት ይካሄዳል ሲሉ የፌዴሬሽኑ እና የምስራቅ አፍሪካ ዞን 5 ፕሬዝደንት ዶ/ር ፍትህ ወልደ ሰንበት አሳወቀዋል።

Harassment Allegations Surface at Fura College Gudumale Campus

Image
Reports from Fura College’s Gudumale campus reveal alarming claims of harassment involving more than 1,000 students. SDC with support from security forces, has allegedly obstructed students who have studied for years from accessing their academic credentials. Students report facing intimidation and delays in obtaining the documents essential for their future endeavors. The situation has prompted calls for immediate intervention from higher authorities to investigate the allegations and ensure the rights of the affected students are upheld. Students emphasize the need for transparency and accountability to resolve the crisis and restore trust in the institution.

ከተማዋን ያነቃቃው የሀዋሳ ከተማ የኮሪደር ልማት

Image