Posts

ባለፉት 7 ወራት ከልዩ ልዩ የገቢ አርእስቶች ከ128 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡

ባለፉት 7 ወራት ከልዩ ልዩ የገቢ አርእስቶች ከ128 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ መሰብሰቡን የሲዳማ ዞን ገቢዎች ባለስልጣን ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡አፈፃፀሙ ካለፈው ዓመት ብልጫ ያለው መሆኑንም ገልፀዋል፡፡የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ተሻለ ቡላዶ እንዳሉት ከመደበኛ ገቢ 116 ሚሊዮን ከማዘጋጃ ቤቶች ደግሞ 12 ነጥብ 4 ሚሊዮን ብር በላይ ገቢ ተሰብስቧል፡፡ የንግዱ ማህበረሰብ በታክስ ክፍያ ዙሪያ ያላቸው ግንዛቤ ማደግ ለገቢው መጨመር አስተዋፅኦው የጐላ እንደነበር መግለፃቸውንም የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25MegTextN404.html

በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ከ33 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ እየተሰራ ነው፡

በሲዳማ ዞን አሮሬሳ ወረዳ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ግንባታ ከ33 ኪሎ ሜትር በላይ መንገድ እየተሰራ ነው፡፡በወረዳው በመገንባትና በመጠገን ላይ የሚገኙት መንገዶች ሁሉም ቀበሌያት ከወረዳዋ ዋና ከተማ የሚያገናኙ ናቸው፡፡የወረዳው የመንገዶችና ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ ተወካይ አቶ ድንቅነህ አለማየሁ ግንባታዎቹ የህዝቡን ማህበራዊና ኢኮኖሚያዊ አገልግሎት ተጠቃሚነትን ወደ ተሻለ ደረጃ ያደርሱታል፡፡ በተለይ ወረዳውን ከኦሮሚያ ክልል የሚያገናኘው ሔማ የተባለው የ18 ኪሎ ሜትር መንገድ ሲጠናቀቅ ኢኮኖሚያዊ ጠቀሜታው የላቀ እንደሆነ መግለፃቸውንም የሲዳማ ዞን የመንግስት ኮሚኒኬሽን ዘግቧል፡፡ http://www.smm.gov.et/_Text/25MegTextN504.html

በህብረሰቡ ጤና ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ የደረቅና ፈሳሽ የማስወገጃ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየሠራ መሆኑን የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ፡፡

በህብረሰቡ ጤና ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ የደረቅና ፈሳሽ የማስወገጃ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየሠራ መሆኑን የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀች፡፡ከአሁን በፊት በከተማው የነበረው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሲሆን አዲስ አሠራር ችግሩን መቅረፍ እንደሚችል ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት፡፡ ማዘጋጃ ቤቱ አሠራሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡በአገራችን አብዛኞቹ በሽታዎች የሚከሰቱት በግልና በአካባቢ ንጽህና ጉድለት ነው፡፡ችግሩን በቀላሉ መቅረፍ እንዲቻል  በደየደረጃው የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም ተዘርግቶ የግልና የአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ ዙሪያ ትምህርት በመስጠት በንጽህና ጉድለት የሚመጡ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል እየተቻለ ነው፡፡ ቀደም ሲል በሀዋሣ ከተማ የነበረው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ቆሻሻው በሚጣልባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥር እንደነበር ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት፡፡በአሁኑ ሰዓት ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው ደረቅ ቆሻሻ በማጠራቀሚያ ቦታ ላይ ተከማችቶ ሳይቆይ ከአፈር ጋር የማደባለቅ ሥራ በመሠራቱ በአካባቢው የሚፈጠረው መጥፎ ሽታ እየቀነሰ መምጣቱን ነው አንዳንዱቹ የሚያስረዱት፡፡ የከተማው ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩ ወልዴ በበኩላቸው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓቱ በህብረተሰቡ ጤናና  አካባቢ ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ ጥናት ተደርጐበት ወደ ሥራ መገባቱን ገልፀዋል፡፡ከደረቅ ቆሻሻ ጋር ተቀላቅለው የሚመጡ ኘላስቲኮች በንፋስ እየተነሱ አካባቢን እንዳይበክሉ ለማድረግ ለብቻ ተለቅመው ተመልሰው አገልግሎት ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡ ከተለያዩ አካባቢዎች በአህያ ጋሪ የሚጓጓዘው ደረቅ ቆሻሻ በከተማ ውስጥ የሚ

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ፡፡

የዳራ ወረዳ ውና፣ ማዕድንና ኢነርጂ ጽህፈት ቤት ከ2 ነጥብ 1 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ ህብረተሰቡን ንፁህ የመጠጥ ውሃ ተጠቃሚ ለማድረግ መንግስታዊ ካልሆነ ድርጅት ጋር በመቀናጀት እየሰራ መሆኑን ገለፀ ፡፡ የጽህፈት ቤቱ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና የተቋማት አስተዳደር ሥራ ሂደት አስተባባሪ ተወካይ አቶ ባንታየሁ ጉዲሳ አንደገለፁት በንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦትና ሳኒቴሽን ኘሮግራም እቅድ ከተያዙት 17 ምንጮች የ12ቱ ግንባታ 87 በመቶ ተጠናቋል ፡፡ የግንባታው ወጪም 85 በመቶ ትንሳኤና ብርሃን በተሰኘ ግብረ ሰናይ ድርጅት የሚሸፈን ሲሆን 15 በመቶ በወረዳው በጀት ይሸፈናል ፡፡ ግንባታው ሲጠናቀቅ የወረዳው የንፁህ መጠጥ ውሃ ሽፋን 38 ነጥብ 8 በመቶ ይደርሳል ማለታቸውን የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጽህፈት ቤት ዘግቧል ፡፡

በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በግማሽ የበጀት ዓመት በአፈፃፀማቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ 6 ቀበሌየት የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ፡፡

በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በግማሽ የበጀት ዓመት በአፈፃፀማቸው የተሻለ ውጤት ላስመዘገቡ 6 ቀበሌየት የማበረታቻ ሽልማት ተሰጠ፡፡የወረዳው ምክር ቤት በ6 ወር የእቅድ አፈፃፀም ዙሪያ ከቀበሌ አፈ ጉባኤዎች፣ ሊቀነ መናብርትና ሥራ አስኪያጆች ጋር ሰሞኑን ውይይት አካሂዷል፡፡ የምክር ቤቱ ምክትል አፈ ጉባኤ ወይዘሮ በላይነሽ ብዙነህ እንደተናገሩት ቀበሌያቱ ሊሸለሙ የቻሉት ደረጃውን የጠበቀ የቀበሌ ምክር ቤት በማቋቋም የህብረተሰቡን ፍላጎት መሠረት ያደረጉ ፈጣን አገልግሎት መስጠት በመቻላቸው ነው፡፡ ቀበሌያቱ ለተለያዩ የልማት ሥራዎት የቅርብ ድጋፍና ክትትል በማድረግ እንዲሁም በየወሩ የሸንጎ አባላት ጉባኤ በማካሄድ ለወረዳ ምክር ቤት ወቅቱን የጠበቀ ሪፖርት በማቅረባቸው ጭምር መሆኑንም አስረድተዋል፡፡የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ዘግቧል፡፡