በህብረሰቡ ጤና ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ የደረቅና ፈሳሽ የማስወገጃ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየሠራ መሆኑን የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀ፡፡


በህብረሰቡ ጤና ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ የደረቅና ፈሳሽ የማስወገጃ ሥራ በተጠናከረ መልኩ እየሠራ መሆኑን የሀዋሣ ከተማ ማዘጋጃ ቤት አስታወቀች፡፡ከአሁን በፊት በከተማው የነበረው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓት በህብረተሰቡ ጤና ላይ ጉዳት የሚያደርስ ሲሆን አዲስ አሠራር ችግሩን መቅረፍ እንደሚችል ነው ነዋሪዎቹ የተናገሩት፡፡
ማዘጋጃ ቤቱ አሠራሩን አጠናክሮ እንደሚቀጥልም ጠቁመዋል፡፡በአገራችን አብዛኞቹ በሽታዎች የሚከሰቱት በግልና በአካባቢ ንጽህና ጉድለት ነው፡፡ችግሩን በቀላሉ መቅረፍ እንዲቻል  በደየደረጃው የጤና ኤክስቴንሽን ኘሮግራም ተዘርግቶ የግልና የአካባቢ ንጽህና አጠባበቅ ዙሪያ ትምህርት በመስጠት በንጽህና ጉድለት የሚመጡ በሽታዎችን አስቀድሞ መከላከል እየተቻለ ነው፡፡
ቀደም ሲል በሀዋሣ ከተማ የነበረው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ቆሻሻው በሚጣልባቸው አካባቢዎች በሚኖሩ የህብረተሰብ ክፍሎች ላይ አሉታዊ ተፅዕኖ ይፈጥር እንደነበር ነው ነዋሪዎቹ የሚናገሩት፡፡በአሁኑ ሰዓት ከየአቅጣጫው የሚሰበሰበው ደረቅ ቆሻሻ በማጠራቀሚያ ቦታ ላይ ተከማችቶ ሳይቆይ ከአፈር ጋር የማደባለቅ ሥራ በመሠራቱ በአካባቢው የሚፈጠረው መጥፎ ሽታ እየቀነሰ መምጣቱን ነው አንዳንዱቹ የሚያስረዱት፡፡
የከተማው ማዘጋጃ ቤት ምክትል ሥራ አስኪያጅ አቶ ብሩ ወልዴ በበኩላቸው የደረቅ ቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓቱ በህብረተሰቡ ጤናና  አካባቢ ላይ ጉዳት በማያደርስ መልኩ ጥናት ተደርጐበት ወደ ሥራ መገባቱን ገልፀዋል፡፡ከደረቅ ቆሻሻ ጋር ተቀላቅለው የሚመጡ ኘላስቲኮች በንፋስ እየተነሱ አካባቢን እንዳይበክሉ ለማድረግ ለብቻ ተለቅመው ተመልሰው አገልግሎት ላይ የሚውሉበትን ሁኔታ በማመቻቸት ላይ እንደሚገኙም ጠቁመዋል፡፡
ከተለያዩ አካባቢዎች በአህያ ጋሪ የሚጓጓዘው ደረቅ ቆሻሻ በከተማ ውስጥ የሚያልፍበት ሰዓት በየመንገዱ እንዳይጣል መሸፈን እንዳለበት ከስምምነት ተደርሷል፡፡ከአሁን በፊት በህብረተሰቡ ላይ ይፈፀም የነበረው ችግር ደግም እንዳይከሰት በትኩረት እንደሚሠራ ነው አቶ ብሩ የጠቆሙት፡፡የከተማው ፅዳት፣ ውበትና መናፈሻ አገልግሎት የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኤልያስ ዘለቀ በከተማው ዋና ዋና መንገዶችና በድንጋይ ንጣፍ መንገድ ላይ የሚደረገው የፅዳትና ውበት ስራ በየክፍለ ከተሞቹም  ተጠናክረው ይቀጥላሉ ብለዋል፡፡
ሀዋሣ ውበቷን ጠብቃ እንድትኖር  የቆሻሻ አወጋገድ ሥርዓትን ማጠናከር ቅድሚያ ሊሰጥ የሚገባ ጉዳይ መሆኑንም አስረድተዋል፡፡የከተማው አስተዳደር ጤና መምሪያ ጤናና ጤና ነክ አገልግሎትና ግብዓቶች ጥራት ቁጥጥር ዋና የሥራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ዘመን ለገሠ እንደገለፁት የደረቅና ፍሳሽ ቆሻሻ ተለይቶ እንዲወገድ መደረጉ በህብረተሰቡ ላይ የሚደርሰውን ተላላፊ በሽታ ለመግታት የሚጫወተው ሚና ከፍተኛ ነው፡፡
ቆሻሻ መጠል ካለበት ሥፍራ ወጪ ከተጠላ ከጐርፍ ጋር እየተቀላቀለ ለተለያዩ የመተንፈሻ በሽታዎች ስለሚደርግ ህብረተሰቡ በጥንቃቄ ማስወገድ እንደሚጠበቅበት አቶ ዘመን አስገንዝበዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

Israel Eshetu back to his childhood club

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት