Posts

የሴቶች ማሕበራዊ፣ኢኮኖሚያዊና ፖለቲካዊ ተጠቃሚነት እየጐለበተ መምጣቱን የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች መምሪያ ገለፀ፡፡

መምሪያው የማርች 8 በዓልን ከከተማው የተውጣጡ አመራሮች፣የየክፍለ ከተማው ተወካዮች እንዲሁም ባለድርሻ አካላት በተገኙበት በተለያዩ ዝግጅቶች አክብሮ ውሏል፡፡ ሴቶች ሕገመንግስቱ ባረጋገጠላቸው መብቶችና ጥበቃወች በመጠቀም ረገድ ከወንዶች እኩል መብት እንዳላቸው እንዲሁም ከተለያዩ ፆታን መሠረት ካደረጉ ጐጂ ልማዳዊ ድርጊቶች የመጠበቅና አገልግሎት የማግኘት መብታቸው የተጠበቀ መሆኑ በግልፅ ተደንግጓል፡፡ በዓሉ የሀገራችን ሴቶች በሕገ መንግስቱ የተረጋገጠላቸው መብቶች ለማስከበር የትግል አንድነታቸውን የሚያጠናክሩበት የተጀመረውን የሠላምና የዴሞክራሲያዊ ጐዞ እንዳይቀለበስ ለማድረግ እንዲሁም በኢኮኖሚያዊ ፖለቲካዊና ማሕበራዊ ዘርፎች በንቃት ተሳትፈው እና ተጠቃሚ ለመሆን ትግላቸውን የሚያጠናክሩበት ነው፡፡ የሀዋሳ ከተማ አስተዳደር ምክር ቤት ዋና አፈ - ጉባኤ አቶ ደምሴ ዶንጊሶ በዓሉን በንግግር ሲከፍቱ እንዳሉት በሀገሪቱ በክልሉና ሆነ በከተማው ከተመዘገቡ ፈጣን የኢክኖሚ ዕድገት የሴቶችን ተሳተፊነትና ተጠቃሚነት ለማረጋገጥ ባለፉት 20 ዓመታት በርካታ ተግባራት ተከናውነዋል፡፡ ሕገ መንግስቱ መሠረት በማድረግም በክልሉ የቤተሰብ ሕግ ተሻሽሎ መውጣቱ ሴቶተ ቤተሰብን በመገንባት ረገድ እኩል መብትና ኃላፊነት እንዲሃራቸው ማድረጉ ይጠቀሳል ብለዋል፡፡ የከተማው ሴቶች ሕፃናትና ወጣቶች ጉዳይ መምሪያ ኃላፊ ወይዘሪት ሥምረት ግርማ በበኩላቸው በዓሉ የሴቶችን ሁለንተናዊ ተጠቃሚነት ከማጐልበቱ በተጨማሪ ሴቶች በድንበር፣በኃይማኖት፣በቀለም፣በቋንቋ እንዲሁም በባሕል ሳይለያዩ የሚደርሱባቸውን ጭቆናና መማሎ የሚያወግዙበት መሆኑን ገልፀዋል፡፡ በዕለቱም ሥርዓተ ፆታና ልማት የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን ዕቅድ ያለው ፋይዳ እንዲሁም የሴቶች የተደራጀ ተሳትፎና ንቅናቄ ለዕቅዱ ስኬት ያለው

እየተመዘገበ የሚገኘውን የኢኮኖሚ ዕድገት ለማስቀጠል የመንግስት ተቋማት የተሻሉ የአሰራር ሥርዓቶችን መዘርጋት እንዳለባቸው የሲዳማ ዞን ዋና አስተዳዳሪ አስታወቀ፡፡

በዞኑ የሚገኙ የሲቪል ሰርቪስ ጽሕፈት ቤቶች የ 6 ወራት እንቅስቃሴ ሲገመገም ዋና አስተዳዳሪው እንዳሉት የመንግስት ተቋማት ፈጣን ልማትና መልካም አስተዳደርን ለማረጋገጥና ለማስፈን የሚያስችል አደረጃጀትና የአሰራር ሥርዓትን መዘርጋት ይጠበቅባቸዋል፡፡ በየደረጃው የሚገኙት የሲቪል ሰርቪስ ሴክተር መሥሪያ ቤቶች የሠራተኛውን ነባርና ኋላ ቀር አስተሳሰብ አሰራሮችን ወደ ልማታዊና  ዴሞክራሲያዊ መስመር ማስገባት ጊዜ የማይሰጠው ጉዳይ መሆኑንም ገልፀዋል፡፡ ተቋማቱም በየጊዜው የአፈፃፀም ብቃታቸውን በመፈተሽና በመለካት መገምገም እንዳለባቸው መግለፃቸውንም ከዞኑ ባሕል ቱሪዝምና  የመንግስት ኮሙኒኬሽን ጉዳዮች የደረሰን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Hawassa is changing ... take a look

Image

Sidama Lodge offering different art to suit every taste

Image
Art Appreciation’s Never-ending The crowded lobby of Sidama Lodge offering different art to suit every taste, on Wednesday, March 2, 2011, with works by various artists including, from top left, Osman,Adamseged Michael, Kidist Brehane, Teferi Mekonnen, and Nebiyu Assefa. Upon entering Sidama Lodge, located on Cape Verde Street around Bole Rwanda, one meets the work of Fitsum Wubeshet, a local artist participating in his fourth exhibition at the lodge. The general theme of his work on show depicts desolate scenes of seemingly abandoned umbrellas over wheelbarrows, and stationary bajaj taxis, seemingly going nowhere in a dust blown sunny scene. He charges 4,000 Br for each of his four artworks on show. “I determine the price according to my feeling of how good it is,” Fitsum told Fortune. “I try to say something with each piece.” Along with his participating colleagues, of which the official number is 25, but Fortune counted a total of 28, there is a lot to say. Between t

የሃዋሳ ከተማን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ልማት ለማፋጠን የነዋሪዎችና የልማት አጋሮች ተሣትፎ ወሣኝ ነው

ሃዋሣ, የካቲት 14 ቀን 2003 (ሃዋሳ) - የሃዋሳ ከተማን የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ልማት ለማጥፋጠን በሚደረገው ጥረት የነዋሪዎችና የልማት በአጋሮች ድጋፋቸውን አጠናክረው መቀጠል እንዳለባቸው የከተማው አስተዳደር ከንቲባ አስታወቁ፡፡ የሃዋሣ 50ኛ ዓመትና ሁለተኛው የኢትዮጵያ ከተሞች ቀን በስኬት እንዲጠናቀቅ አስተዋጽኦ ላደረጉ ከ80 በላይ ግለሰቦችና ድርጅቶች የከተማው አስተዳደር ትናንት የምስጋና የምስክር ወረቀት ሰጥቷል፡፡ በዚሁ ወቅት ከንቲባው አቶ ሽብቁ ማጋኔ እንደገለፁት በዓሉ በፈጠረው ምቹ ሁኔታ የከተማውን ሁለንተናዊ ገጽታ ለማስተዋወቅ ተችሏል፡፡ ከ80 በላይ የኢትዮጵያ ከተሞችና ከ40 በላይ ድርጅቶች የተሣተፉበትን ይህንኑ በዓል ተከትሎ የኢንቨስትመንትና የቱሪዝም ፍሰት በእጅጉ መጨመሩን ገልፀዋል፡፡ በአሉ ሃዋሳ ለኢንቨስትመንትና ለቱሪዝም ምቹ እንዲሁም የፈጣን ልማት፣ የእድገትና የአንድነት ተምሣሌት መሆኗን ማስመስከር የተቻለበት መሆኑን አስታውቀዋል፡፡ ለዚህም ስኬት መላው ነዋሪ ህዝብና የልማት አጋሮች ያደረጉት ተሣትፎ ከፍተኛ እንደነበር ገልፀዋል፡፡ ለበአሉ ስኬታማነት አስተዋጽኦ ያደረጉ ከ80 በላይ ግለሰቦችና ድርጅቶች ትናንት ምሽት በተዘጋጀው ኘሮግራም ላይ ከከተማው ከንቲባ ከአቶ ሽብቁ ማጋኔ እጅ የምስጋና የምስክር ወረቀት ተቀብለዋል፡፡