Posts

በሃዋሳ ከተማ የግል ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ለመፍቀድ በወጣው ጨረታ ተወዳዳሪ መታጣቱ ተሰማ

Image
ዜናው የሪፖርተር ጋዜጣ ነው -ለሐዋሳና ባህር ዳር ለወጣው ጨረታ ተወዳዳሪዎች አልቀረቡም የኢትዮጵያ ብሮድካስት ባለሥልጣን በአዲስ አበባ ከተማ ለሚሠራጭ የንግድ (የግል) ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ አገልግሎት ባወጣው ጨረታ ተሳትፈው ላሸነፉ ድርጅቶች ዛሬ ፈቃዳቸውን ይሰጣል፡፡ ባለሥልጣኑ ለአዲስ አበባ ከተማ፣ ለባህር ዳር ከተማና ለሐዋሳ ከተማ የግል ሬዲዮ ጣቢያ ለመፍቀድ ጨረታ ያወጣ ቢሆንም፣ ለባህር ዳርና ለሐዋሳ ቀርቦ የሚወዳደር ድርጅት አለማግኘቱን አስታውቋል፡፡ ለአዲስ አበባ ለሚፈቀደው 102.9 ኤፍኤም ሬዲዮ ለውድድር የቀረቡት ሦስት ድርጅቶች ብቻ ናቸው፡፡ ከቀረቡት ሦስት ተወዳዳሪዎች ውስጥ ‹‹እግር ኳስን በሬዲዮ ይመልከቱ›› በሚል በፋና ብሮድካስት ኮርፖሬት 98.1 ኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያ ላይ እየሠራ የሚገኘው አቶ መሰለ መንግሥቱ ድርጅት መሆኑ የተጠቆመው ‹‹ዓባይ›› የተባለው ድርጅት አሸናፊ ሆኗል፡፡ ባለሥልጣኑ በአዲስ አበባ ሌላ ተጨማሪ ጣቢያ ለመስጠት በድጋሚ ባወጣው ጨረታ ሁለት ተጫራቾች ብቻ ቀርበዋል፡፡ ከሁለቱ ተጫራቾች ብሥራት የተባለ ድርጅት ኤፍኤም 101.1 ሬዴዮ ጣቢያን ማሸነፉ ታውቋል፡፡ በመሆኑም ባለሥልጣኑ በአዋጅ ቁጥር 533/99 በተሰጠው ሥልጣን መሠረት ያወጣውን የኤፍኤም ሬዲዮ ጣቢያዎችን አሸናፊ ተወዳዳሪዎች ድርጅቶች ዛሬ ፈቃዳቸውን እንደሚያስረክብ አስታውቋል፡፡ በጨረታው አዲስ ስቴይለር፣ አዲካ ኢቨንት ኤንድ ኮሙዩኒኬሸን፣ አክሱም ፒክቸርስ (ኢትዮፒካ ሊንክ) እና ሌሎችም ሁለት ድርጅቶች የተሳተፉ ቢሆንም፣ ማሸነፍ አለመቻላቸው ተጠቁሟል፡፡  በጨረታው ለመሳተፍ የሚያስፈልጉ መሥፈርቶችና ስለጨረታው አከፋፈት ማብራሪያ እንዲሰጡ የባለሥልጣኑን የሕዝብ ግንኙነት ማስተባበሪያ ኃላፊ አቶ ወርቅነህ ጣፍን ከሪፖርተር ጥያቄ ቢቀር

መድረክ በሐዋሳ የጠራው ሰላማዊ ሠልፍ በእንግልት ተካሄደ አለ

Image
የኢትዮጵያ ፌዴራላዊ ዲሞክራሲያዊ መድረክ (መድረክ) እና አባል ድርጅቶቹ የሲዳማ አርነት ንቅናቄ (ሲአን)፣ የኢትዮጵያ ማኅበረ ዲሞክራሲ ደቡብ ኅብረት አንድነት ፓርቲ (አማዲደህአፓ)፣ የኦሮሞ ፌዴራሊስት ኮንግረስ (ኦፌኮ) እና አረና ትግራይ ለዲሞክራሲና ሉዓላዊነት ፓርቲ (አረና) ጋር በደቡብ ክልል ዋና ከተማ ሐዋሳ ያካሄደው ሰላማዊ ሠልፍ በእንግልት መካሄዱን አስታወቀ፡፡  የአገሪቱን ወቅታዊ ሁኔታ አስመልክቶ ‹‹ሰላማዊና ዲሞክራሲያዊ ተቃውሞዎችን በኃይል ማፈን ይቁም›› በሚል ሰኔ 7 ቀን 2006 ዓ.ም. በሐዋሳ ከተማ ያካሄደው ሰላማዊ ሠልፍ በሰላም ቢጠናቀቅም፣ ገዥው ፓርቲ ሕዝቡ ወደ ሠልፍ እንዳይወጣ የተለያዩ ማነቆዎችን መፍጠሩን መድረክ ገልጿል፡፡ የፓርቲው ሕዝብ ግንኙነት ኃላፊ አቶ ጥላሁን እንደሻው፣ ‹‹ገዥው ፓርቲ አፈና ሲያደርግብን ነበር፡፡ ቅዳሜ ልናካሄድ ላሰብነው ሰላማዊ ሠልፍ የዕውቅና ደብዳቤ የሰጠን ሐሙስ 11 ሰዓት ላይ ነው፤›› በማለት ገዥው ፓርቲን የኮነኑ ሲሆን፣ ‹‹ቢሆንም ግን ሕዝቡ ይህን አፈና ተቋቁሞ በመውጣት የተሳካ ሠልፍ አካሂደናል፤›› ሲሉ ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡    ፓርቲው አገሪቱ ውስጥ ተፈጥረዋል ያላቸውን መሠረታዊ ችግሮች በዝርዝር ለሕዝብ ያቀረበ መሆኑን፣ በሕገ መንግሥቱ ተደንግገው ነገር ግን መፈጸም ያልተቻሉ ያላቸውን ዝርዝር ጉዳዮች እንዲሁ ለሕዝቡ ማቅረቡን ገልጿል፡፡  መሠረታዊ ችግሮች በሚል ፓርቲው በዝርዝር ካስቀመጣቸው ነጥቦች መካከል የሕዝቡ የሥልጣን ባለቤትነት እውን እንዳይሆንና የመድበለ ፓርቲ ዲሞክራሲ በትክክል ሥራ ላይ እንዳይውል የምርጫ ቦርድ ለኢሕአዴግ ወገንተኛ መሆኑን፣ በነፃነት በሰላማዊ መንገድ ለመንቀሳቀስ በሚፈልጉ ተቃዋሚ ፓርቲዎች ላይ ልዩ ልዩ የማቀጨጭ ሥልቶችን ተጠቅሞ ተፅዕኖዎችን

ኢትዮጵያ በዓለም ብጥብጥ ከነገሰባቸው ኣገራት ተርታ 24 ደረጃ ይዛለች

Image
As the civil war in Iraq dominates headlines, it is no surprise that the world continued a seven-year-slide away from peacefulness over the last 12 months, as measured by the Institute for Economics and Peace. Syria displaced Afghanistan   as the world’s least peaceful nation in its newly-released Global Peace Index, compiled before the latest upsurge in fighting in Iraq. Iceland maintained its status as the most peaceful country, with six other European countries plus Canada, Australian in the top 10. Britain was ranked in 47th place, one above France and one below Lithuania. World's least peaceful countries COUNTRY SCORE RANK Syria 3.65 162/162 Afghanistan 3.42 161/162 South Sudan 3.40 160/162 Iraq 3.38 159/162 Somalia 3.37 158/162 Sudan 3.36 157/162 Central African Republic 3.33 156/162 Democratic Republic of the Congo 3.21 155/162 Pakistan 3.11 154/162 North Korea 3.07 153/162 Russia 3.04 152/162 Nigeria 2.71 151/162 Colombia 2.70

Marriot International soon in Hawassa

Image
Following the continually rising interest of investing in Ethiopia in all aspects and the double digit economic growth it celebrated for the last decade, the country is becoming the conference hub of the continent. This has been making conference tourism, one of the investment area attracting foreign investors. In an attempt to reap the opportunity, thus, created the presence of international brand hotels in the nation's hospitality sector is expanding. Marriot International is not the exception. As part of a management deal sealed between Marriot and Sunshine Construction plc, Sunshine has laid a corner stone in Hawassa town on last Sunday, May 8, 2014. The CEO and owner of Sunshine, Samuel Tefese was accompanied by the President of Southern Region, Dessie Dalkie and the city mayor of Hawassa, Yonas Yosef (middle) during the laying of the corner stone. Source

የጉምሩክ አዋጅ ሊሻሻል ነው

-  ክስ የማይመሠረትባቸው የጉምሩክ ጥፋቶች ተዘርዝረዋል     -  የምርት ሒደታቸውን ባላጠናቀቁ ምርቶች ላይ የቀረጥ ነፃ አሠራር ይፈቅዳል      -   ዋና ዳይሬክተሩ ክስ አለመመሥረት የሚችልባቸው አሠራሮች ተቀምጠዋል በ2001 ዓ.ም. ፀድቆ ሥራ ላይ የዋለውን የጉምሩክ አዋጅ የሚያሻሽልና የአገሪቱን የማኑፋክቸሪንግ ዘመቻ የመደገፍ ግብ የያዘ የጉምሩክ ማሻሻያ አዋጅ ለሕዝብ ተወካዮች ምክር ቤት ቀረበ፡፡ አዋጁ ለአገር ውስጥ ፍጆታ የሚውሉ የምርት ሒደታቸውን ያላጠናቀቁ ምርቶች ከቀረጥ ነፃ ገብተው በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር የምርት ሒደታቸውን እንዲያጠናቅቁ ይፈቅዳል፡፡ ምንጭ በአገሪቱ እየታየ ያለው የኢኮኖሚ ዕድገት የሚጠይቀው የጉምሩክ አሠራርን ማካተት አስፈላጊ መሆኑን መንግሥት ስላመነበት ማሻሻያ ረቂቁ መዘጋጀቱን፣ ባለፈው ሐሙስ ለፓርላማ የቀረበው የአዋጁ ማብራርያ ይገልጻል፡፡ አዋጁን ለማሻሻል ምክንያት ከሆኑት መካከል የወጪና ገቢ ንግድ ዕድገት፣ በተለይም የማኑፋክቸሪንግ ኢንዱስትሪ ልማት የሚጠይቃቸውን ቀልጣፋ የጉምሩክ አገልግሎት ለመስጠትና የተመጣጠነ ቁጥጥር ለማድረግ የሚያስችሉ አሠራሮችን ሥራ ላይ ለማዋል፣ ዘመናዊና በዓለም አቀፍ ደረጃ ተቀባይነት ያገኙ የጉምሩክ አሠራሮችን ለማስፈጸም የሚያስችል ሕግ ማውጣት አስፈላጊ መሆኑ ይገኙበታል፡፡ አዋጁ ካካተታቸው ዋና ዋና ለውጦች መካከል የምርት ሒደታቸውን ሳያጠናቅቁ ወደ አገር የሚገቡ ዕቃዎች ያለቀረጥ የሚስተናገዱበትና በጉምሩክ ቁጥጥር ሥር የሚጠናቀቁበት አሠራር አንዱ ነው፡፡ ይህ አሠራር ከውጭ አገር የመጡ ዕቃዎች ለአገር ውስጥ ፍጆታ ከመለቀቃቸው በፊት አገር ውስጥ የምርት ሒደታቸውን የሚያጠናቅቁበትና ለአገር ውስጥ ፍጆታ ሲለቀቁ ቀረጥና ታክስ እንዲከፈልባቸው የሚደረግበት አሠራር መሆኑን የ