የሲዳማ አባቶች ታርክ
ይህ ጽሑፍ ከ Equality Equity Struggle ከተሰኘ የማህበራዊ ገጽ ላይ የተወሰደ ሲሆን፤ በጽሑፉ ላይ የተነሱ ሀሳቦች በሙሉ የማህበራዊ ገጹ ጻፊዎች መሆኑን መግለጽ እወዳለሁ።
በሲዳማ ጎሳዎች መካከል የተፈጠረ ልዩነት በሲዳማ ጎሳዎች መካከል ልዩነት የተጀመረው ከሆፋዎች መሸነፍና መጥፋት ተከትሎ መሆኑ ጆን ኤች ሀመር በፃፈ መጽሐፍ እንዲህ ሲል ገልጿል።“ከሆፋዎች መሸነፍና መጥፋት በኋላ የቡሼ ጎሳዎች እርስ በርስና የማልዴያ ሲዳማ ጎሳዎች ወደግጭት እንደገቡ አንስተዋል። /ከሆፋዎች መሸነፍ በኋላ ወዲያውኑ ወደግጭት ገቡ የሚለው በግምት1590-1665 ከዛሬ 337 ዓመት በፊት መሆኑን የሚያሳይ ነውሏ“shortly after this defeat the conflict began between theMaldeans and the Busheans.”
የልዩነቱ ዋነኛ ምክንያት የሆፋዎች መጥፋት ተከትሎ መሬት ወይም የሀብትክፍፍልመሆኑንይነገራል።በዚህ መሰረት የቡሼ ወገን የሆኑት ሼቤዲኖ፣ያናሴ፣ዊጋ፣ማልጋ፣ሆሎ፣ጋርብቾ እና ሀርቤጎና ሆፋን ለማጥፋት በተደረገው ትግል ግንበር ቀደም በመሆናቸውና ይህንን የተገኘውን መሬት በባለቤትናት ለመያዝ የሚያስችላቸውን“የመርቾ”ብለው ቡድን መፍጠራቸውን ይነገራል።
ይሁን እንጅ ሆፋን ለማጥፋት ከተደረገው ትግል ውጭ የማልዴያ የሲዳማ ወገን ብዙም ግንኙነት ያልነበረው ሲሆን በኃላ በዚህ ስብስበ መካተት እንደሚገባው ባነሳው ጥያቄ መሰረት ከማልዴያ ወገን ሐዌላ፣ሳኦላና ቀዌና እንድካተቱ ተደርጓል።
ከቡሼ ወገን ሀድቾ በቡድኑ ያልተካተተ ሲሆን ከማልዴያ ወገን አለታ እና ሌሎች በማልዴያ ንዑስ ጎሳዎች የተካተቱ ጎሳዎች ሳይካተቱ ቀርቷል።
ጆን ኤች ሀመር “Humane Development:Participation and Change Among theSidama of Ethiopia”በሚለው መጽሐፉ ገጽ 32ላይእንዲህ ብሎ አስፍሯል።
ለምንድነው እነዚህ የሲዳማ ጎሳ አባላት በየመርቾ ቡድን ሳይካተቱ የቀሩት? የሚለውን ጥያቄ በእርግጠኝነት መመለስ ባይቻልም በአፌ-ታሪክ እና በአሉታ ሏተባለ ተብሎ በተፃፉ ጽሑፍች መነሻ መመልከት ጠቃሚ ነው።
ከቡሼ የዘር ግንድ አባላት መካከል ሳይካተት የቀረው ሀድቾ መሆኑን ይነገራል። ሀድቾ በየመርቾ ያልተካተተው በሶስት ምክንያት እንደሆነ ይገመታል።
የመጀመሪያው ሀድቾ የቡሼ የመጀመሪያ ልጅ ሲሆን የተወለደውም ከሆፋን ዘር ሀረግ ከሆነችው እናትሏ ሴት ከሲራሮ ሲዳ በመወለድ ምክንያት እንደሆነ ይነሳል።የጥላቻውም መነሻ ሆፋዎች ያደረሱባቸውን በደል መነሻ መሆኑ ይነሳል፣ ከአሩስ ሴትሏ እናት የተወለዱ ማሊጊቻና ሐሜ መሬቱን ለመቆጣጠሪ እንዲቻላቸው እንዳገለሉአቸው የሀድቾ ጎሳ አባላት ያነሳሉ፣ ቡሼ ወደ ቴላሞ ልጅ ወልዶ ሲመጣ የሆፋ ንጉስ እኔን የሚወርስ ልጅ ተወልዶል ብሏል መባሉ በሌሎች በቡሹ ልጆች ላይ ጥርጣሬእና ቅናት መፍጠሩ እንደተጨማሪ ምክንያት የሚያነሳ ሲሆን በተጨማሪ ከሆፋ ንጉስ በተገባለት ቃል መሰረት ያገኘው መሬት በመሆኑ መሬቱን ይወርሳል የሚል አስተሳሰብ በሌሎች የቡሼ ልጆች ጋ እንደ ተፈጠረ እና ኔኦ በርካታ ልጆችን መውለዱ በምክንያት ያነሳሉ።
በዚህ ሁኔታ ከ1258-1528 ጀምሮ በአማካይ በግምት ለ234 ዓመታት ያለምንም ችግር የቆዩ ቢሆንም ከዚህ ጊዜ በኃላ የቡሼ ከአሩሲ እናትሏ ሴት የተወለዱ እና በኔኦ ልጆችመካከልልዩነ እየተፈጠረእንደሄደይነገራል።ይህም መገለልና ልዩነት የጀመረው በግምትከ1590-1665 በአማካይ በግምት ከዛሬ 384ዓመት በፊት እንደሆነ ይነገራል።በዚህም መነሻ የየመሪቾ ቡድን ሲመሰረት የሀድቾ ጎሳ አባል እንዳይሆን እንደተደረገ የጎሳው አባላት ያነሳሉ።
ከማልዴያ ወገን የየመሪቾ ቡድን ከመመስረቱ በፊት ከቡሼ ተገንጥለው የራሳቸው መሬት እያስፋፉ መቆየታቸው የሚነገር ሲሆን በተለይ አለታ ከግዳቦ ወንዝ ማዶ የነበረውን ሰፊ መሬት እያሰፋ መቆየቱ ይነገራል። አለታ በ12 ንዑስ ጎሳዎች የተደራጀ ሲሆን 7ቱ ከማልዴያ ሲሆን አምስቱ ከሌሎች ጎሳዎች ሆኖ አንዱ ከጉጅ ጉሳ የተገኘ መሆኑን ጆን ኤች ሀመር ገጽ30 ላይ አስፍሮት እናያለን በሌላ በኩል አለታ ወደ ደቡባዊ አከባብ ሲሄድ ሌሎች የማልዴያ የዘር ሀረግ ሀዌላ፣ሳዎላናቄዌና በሰሜን በኩል እንደቀሩ ይነሳል።
በዚህ መሰረት አለታ በርካታ መሬት በመቆጣጠር በራሱ እጅ ያስገባ በመሆኑ በየመርቾ ቡድን መታቀፍ እንዳልቻለ ይነገራል። የየመርቾ ቡድንም አለታን ለማቀፍ ፍቃደኛ አለመሆናቸውንና በኃላም ይህ ልዩነት እየሰፋ መሄዱን ይነሳል።አለታ ጎሳ በየመርቾ ቡድን በዋነኛነት ያልተከተተበት ምክንያት ሲያነሳ አለታ በ12 ንዑስ ጎሳዎች የተዋቀረ መሆኑንና 7ከማልዴያ፣አንዱ ከጉጂ ኦሮሞ እና4ጎሳዎችየዘርግንዳቸው የማይታወቅ መሆኑ እንደ ምክነያት የተነሳ ቢሆንም ዋነኛ ምክንያቱ ቀደም ብሎ ከግዳቦ ወንዝ ማዶ ሰፊ መሬት በመያዙ ምክንያት በተገኘው መሬት ክፍፍል ላይ ላለማሳተፍ የተፈጠረ ምክንያት መሆኑ ይነገራል።ይህንን ልዩነት ከአለታ በኩልተቀባይነት ያላገኘ ሲሆን በእነዚህና በሌሎች ምክንያት በአለታና በየመርቾ ቡድን መካከል በተፈጠረው ግጭት አለታዎች በአሸናፊነት መውጣታቸው ይነገራል።
በዚህም የየመርቾ ቡድን በመሸነፉ ምክንያት የመርቾ ተብሎ ይጠራ የነበረው ቡድን ፈርሶ አለታንና ሌሎች ጎሳዎችን ያቀፈ አዲስ ቡድን እንደተመሰረተ ይነገራል።ይህም ቡድን ቀድሞ የመርቾ የጀመረውን የመንፃት ሥርዓትን/አይዶሎጅ/ ሪዮተ-ዓለምሏ መነሻ ያደረገና ከዚህ በፊት ያልተካተቱትን አካቶ “ወላዊቾ” ቡድን በማለት እንዲመሰረት ተደርጓል።
አንዳንድ ፀሐፊዎች ስለዚህ ቡድን ሲያነሱ ከሀድቾና ከጥቅት ጎሳዎች ውጭ ሁሉም ጎሳዎች በዚህ ቡድን እንዲካተት መደረጉ የሚነሳ ሲሆን በአሁኑ ጊዜ ከቡድኑ ውጭ እንዲሆን የተደረገው “አዋቾ” ጭምር የቡድኑ አባል እንደሆነ ይነገራል።
በዚህ መሰረት በዚህ ቡድኖች የተካተቱ ጎሳዎች ራሳቸውን ከሌሎች በመለየትና መሬቱን ለመቆጣጠር የሚያስችላቸውን ዘዴ መፍጠራቸውን ይነሳል። በዚህ በየመርቾ ቡድን የተዋቀሩ ጎሳዎች የመሬቱ ባለቤት መሆናቸውንና ከእነሱውጭ የሚኖሩ የሲዳማ ጎሳዎች ካለነሱ ፍቃድ መሬት መያዝ እንደማይችሉእና ለእነርሱ መገበር እንደሚገባቸውና በሲዳማ በየትኛውም የባህል ስርዓት ራሳቸውን ችለው እንዳይፈጽሙና ለሚፈጸሙ ሥርዓቶች የየመርቾ ቡድን አባላት ይሁንታ ማግኘት እንደሚገባቸው አደረጉ።
በዚህ መሰረት የራሱ የሲዳማ ጎሳ አባል የሆኑ ጎሳዎች ከመሬት ባለበትነት በመነጠል ለየመርቾ ገባር እንዲሆኑ ተደረጓል። ይህ የሆነው በ16ኛና 17ኛክፍለ-ዘመንሏ ከ1590 1665/ ጀምሮ መሆኑን ይነገራል።
ይሁን እንጂ ከእነዚህ ከቀደምት ከሁለቱ የሲዳማ አባቶች ምንማረው ብዙ ነገር አለ።ሁለቱ አባቶች ከተለያየ ዘር ሀረግ የመጡ መሆናቸውን በአፈ-ታሪክ ይነገራል።ይሁን እንጂ የተለየን ነንብለው ልዩነት አልፈጠሩም።
ይልቁንም ቡሼ መሬት ሲያገኝ ቶሎ የጠራው ማልዴያን እንደሆነ ይነገራል።ከሆፋዎችጋር ተስምተው ለ234ዓመታት ኖረዋል።በመጨረሻም ከሆፋዎች ላጋጠማቸው ችግር አብረው ተጋፍጠፋል።ድልም አግኝተዋል።
በአንድ ብሔር እንዲጠሩም ቋንቋውን፣ባህሉንናሌሎችየጋራ ሊያደርጓቸው የሚችሉ ሥራዎችን ሰርተዋል። ይሁን-እንጂ የቡሼ ወገን ከ7ትውልድ በኃላ ከራሱ ወገን ጋር ለምን መስማማት አቃተው? የሚል ጥያቄ ግን በዚህ ትውልድ መልስ ማግኘት የሚገባው ነው።
በአሁኑ ጊዜ በአብዛኛው መገለል የደረሰባቸው የቡሼ የዘርሀረግ አባል የሆኑ ሲሆኑ ከማልዴያ ወገን ግን መገለል ና አድሎ የደረሰባቸው በጉልህ አይታይም። ለምሳሌ በማልዴያ ዘር ግንድ ከሆኑት ከ12ቱ የአለታ ንዑስ ጎሳዎች መካከል 5ቱ ንዑሳን ጎሳዎች ቀጥታ የማልዴያ ዘርሀረግ ባይሆኑም በአለታነት ታቅፈው የጎላ በደልና መገለል ሳይደርስባቸው ይኖራሉ።
ከቡሼ ዘርሀረግ ከሆኑ 3ቱ ጎሳዎች ወይም ወንድሞች መካከል ሀድቾ (በተጨማር ከንዑስ ጎሳ አዋቾ) መገለሉ የደረሰባቸው ከማልዴያ ወገን ሳይሆን ከራሱ ከቡሼ ወገን መሆኑ ለምን? የሚል ጥያቄ ያስነሳል። በመሆኑም ከተለያዩ የዘር-ሀረግ የመጡ የሲዳማ አባቶች እንደአንድ ሲዳማ ብሔር ፈጥረው ሲሰጡን እኛ ከአንድ ጎሳ የተፈጠርን የቡሼ ልጆች አንድመሆን አቅቶን በየዘመበመካከላችን ልዩነትን እየፈጠርን እየሄድን እንደገኛለን። በተለይ የቡሼ የዘር-ሀረግ የሆንን ሲዳማዎች ከማልዴያ የዘር-ሀረግ ከሆኑ ሲዳማዎች በተለይ ከአለታ ብዙ መማሪ ይኖርብናል።
ቀድሞ የነበረው አስተሳሰብና አመለካከት የማህበረሰቡ የንቃቴ ህልና ውስንነት ያለ ቢሆንም በዚሁ ዘመን የተማሩና አወቁ የሚባሉ የሲዳማ ሹማምንት ሳይቀር ከዚህ አስተሳሰብ አለመላቀቃቸውና በማህበረሰቡ መካከል ልዩነት እንዲሰፍን ማድረጋቸው ወደኃላ ተመልሰው ከ500ዓመት በፊት ከኖሩት ከቡሼና ከማልዴያ አባቾቻች ልምድና ገድል መውሰድ ይገባቸዋል።
ለውይይት የቀረበ ጥያቄ
ቡሹ እንዴት ወደ ቴላሞ መጣ?እንዴትስ ከሆፋዎች ጋር ተገናኘ?
ሽማግሎች ጠይቁ ይኑግሩሃል።
Comments
Post a Comment