የዞኖቹ ክልል የመሆን ጥያቄ ለምን በረታ? እንዴትስ በረከተ?

የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የመፍረስ አሊያም ቅርጹን የመቀየር እጣ-ፈንታ ገጥሞታል። ቀድሞም በሕዝቦች ይሁንታ አልተዋቀረም በሚባልለት ክልል ለቀረቡት ጥያቄዎች መበርከትና መበርታት ኢሕአዴግ የገባበት የውስጥ ሽኩቻና ግንባሩ ይከተለው የነበረው የማዕከላዊ ዴሞክራሲያዊነት መርኅ መላላት ተጨማሪ ገፊ ምክንያቶች እንደሆኑ ይናገራል።

ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

የኢትዮጵያ ፌድራላዊ ሥርዓተ-መንግሥት ስኬት ተደርጎ በኢሕአዴግ ልሒቃን ይወደስ የነበረው የደቡብ ብሔሮች ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልል የመፍረስ አሊያም ቅርጹን የመቀየር እጣ-ፈንታ ገጥሞታል። በአስራ አራት ዞኖች እና ሶስት ልዩ ወረዳዎች በተዋቀረው ደቡብ 'ክልል መሆን እንሻለን' የሚል ጥያቄ በተደጋጋሚ እየተደመጠ ነው።
ታሪኩን ያጠኑ፤ ፖለቲካውን የተነተኑ እና የገጠመው ፈተና የታያቸው ምሁራን ቀድሞም በሕዝቦች ፍላጎት እና ፈቃድ የተመሠረተ አለመሆኑ ዛሬ ለገባበት ቅርቃር ዋንኛው ምክንያት እንደሆነ ይናገራሉ። ገዢው የኢትዮጵያ ሕዝቦች አብዮታዊ ዴሞክራሲያዊ ግንባር (ኢሕአዴግ) የገጠመው የውስጥ ሽኩቻ በተለይም ይከተለው የነበረው የማዕከላዊ ዴሞክራሲያዊነት መርኅ መላላት ሌላው ገፊ ምክንያት እንደሆነ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
የዞኖቹ ጥያቄ ቢመለስ ክልሉን በብቸኝነት ላለፉት አመታት የመራው ደኢሕዴን ሊፈርስ፣ በአገሪቱ ፖለቲካ ላይ ይጫት የነበረው ሚናም እንደሚዳከም ጉዳዩን በቅርበት የሚከታተሉ ባለሙያዎች ይናገራሉ።
በሳምንቱ እንወያይ መሰናዶ ሲዳማ፣ ወላይታ፣ የከፋ እና የከንባታ ጠንባሮ ዞኖች ያነሱት ጥያቄ በክልሉ እጣ-ፈንታ ላይ የሚያሳድረውን አዎንታዊ እና አሉታዊ ተፅዕኖ ይዳስሳል። በውይይቱ የታሪክ ባለሙያው አቶ አባቡ አሊጋዝ፣ የሕግ እና የፌድራሊዝም ጥናት ባለሙያው ፕሮፌሰር ዮናታን ፍሰሐ እና የመልካም አስተዳደር ጥናት ባለሙያው ዶክተር የሺጥላ ወንድሜነሕ ተሳትፈዋል።
ሙሉ ውይይቱን ለማድመጥ የድምፅ ማዕቀፉን ይጫኑ

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር