በኢትዮጵያና ኬንያ ወሰን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው

ታህሳስ 5፣ 2011 (ኤፍ.ቢ.ሲ) በኢትዮጵያና ኬንያ ወሰን ሰላምና ደህንነት ጉዳዮች ላይ የሚመክር መድረክ በሀዋሳ ከተማ እየተካሄደ ነው።
በውይይት መድረኩ ላይ ከሁለቱ ሀገራት የተወከሉ የመንግስት የስራ ሃለፊዎችና ባለሙያዎች እየተሳተፉ መሆኑም ተገልጿል።
ውይይቱ በሁለቱ ሀገራት ወሰን አካባቢ ከጋራ ሃብት አጠቃቀሞ ጋር በተያያዘ የሚነሱ የተለመዱ ግጭቶችን በመፍታት አስተማማኝና ዘላቂ ሰላም ለማስፈን ያለመ ነው ተብሏል።
ለዚህም ቀደም ሲል በደቡብ ኦሞና ቱርካና ሃይቅ፣ በኢትዮጵያና ኬኒያ ሁለቱም ሞያሌዎች አካባቢ የሁለቱን ሀገራት ህዝቦችን ያሳተፉ ተመሳሳይ ውይይቶች ሲካሄዱ መቆየታቸው ነው የተገለጸው።
ከእነዚህ ውይይቶች የመነሻ ግብዓት ተወስዶ በባለሙያዎች በዛሬው ውይይትላይ ቀርቦ ውይይት እየተደረገበት መሆኑ ተገልጿል።
የኢፌዴሪ የሰላም ሚኒስቴር ሚኒስትር ዴኤታ አቶ ዘይኑ ጀማል እንደገለጹት የኢትዮጵያና ኬኒያ መልካም ጉርብትና በአፍሪካ በአረያነት የሚጠቀስነው ብለዋል።
አልፎ አልፎ በሁለቱ ሀገራት ወሰን አካባቢ ከሃብት አጠቃቀም ጋር በተያያዘ የሚነሱ የተለመዱ ግጭቶች መኖራቸውን በመግለጽ የውይይት መድረኩ ችግሮችን ለመፍታት በሚያስችሉ ጉዳዮች ላይ እየተካሄደ መሆኑን ገልጸዋል።
የሁለቱ ሀገራት መልካም ጉርብትና የበለጠ ለማጠናከርና አልፎ አልፎ የሚከሰቱ ግጭቶችን በባህላዊ መንገድ ለመፍታት ያለመ መሆኑም ተነግሯል።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር