በ 270 ሚሊየን ብር የተገነባው የሃዋሳ ከተማ ውሃና ፍሳሽ ማስፋፊያ ፕሮጀክት ተጠናቀቀ

(ኤፍ.ቢ.ሲ)በ270 ሚሊየን ብር ወጪ የተገነባው የሃዋሳ ከተማ የውሃና ፍሳሽ ማስፋፊያ ፕሮጀክት መጠናቀቁ ተገለፀ።
ፕሮጀክቱ የሃዋሳ ከተማ ፈጣን ዕድገትና የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ፍላጎትን ለማመጠጠን ሲባል ከዓለም ባንክ ጋር በተደረገ የብድር ስምምነት የተገነባው መሆኑ ነው የተገለፀው።
በከተማዋ የሚስተዋለውን የንፁህ መጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር በዘላቂነት ለመፍታት ያስችላል የተባለው ይህ ፕሮጀክት ፥ የፊታችን ታህሳስ 13 ቀን 2011 ዓ.ም የሚመረቅ መሆኑን ከውሃ፣መስኖ እና ኢነርጂ ሚኒስቴር ያገኘነው መረጃ ያመላክታል።
በሌላ በኩል  በአካባቢው በሚገኘው አምቦ ምንጭ ላይ በተከናወነ የማጎልበት ስራ በሃዋሳ ከተማ የሚገኙ የአዲስ ከተማና የምስራቅ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችን ንፁህ የመጠጥ ውሃ አቅርቦት ችግር መፍታት መቻሉ ተገልጿል።
ከምጭ ማጎልበቱ ስራ በተጨማሪም  11 ኪሎ ሜትር ውሃ ማስተላለፊያ ቧንቧ ፣1 ሺህ ሜትር ኩብ ውሃ የሚይዝ ተገጣጣሚ  የውሃ ማጠራቀሚያ እና 2 ነጥብ 5 ኪሎ ሜትር የውሃ ማሰራጫ ዋና መስመር ዝርጋት ስራ መከናወኑ ተገልጿል ።
በአጠቃላይ ከአምቦ ውሃ ፕሮጀክት በቀን ተጨማሪ 4 ነጥብ 8 ሚሊዬን ሊትር ውሃ የተገኘ ሲሆን ፥ይህም የአዲስ ከተማ ክፍለ ከተማ ነዋሪዎችን ችግር ከመቅረፍ ባሻገር በከተማዋ ውሃ በፈረቃ የሚከፋፈልበትን ሂፈደት ያስቀራል ተብሏል።
የአምቦ ምንጭ ፕሮጀክት በ2002 ዓ.ም ተጀምሮ በ2003 ዓ.ም ቢጠናቀቅም፥ በአካባቢው በነበረው ማህበራዊ ችግር ምክንያት ውሃው ጥቅም ላይ የዋለው በ2004 ዓ.ም መሆኑ ይታወሳል።
ከዚህ ባለፈም የሃዋሳ ከተማን ውሃ ችግር በዘላቂነት ለመፍታት በተጨማሪ የፋይናስ ስምምነት 9 ጥልቅ የውሃ ጉድጓዶች በመቆፈር በቀን ተጨማሪ 25 ሚሊየን ሊትር ውሃ ለከተማዋ ተጠቃሚዎች ማዳረስ ተችሏል።
ይህንስራ  ለማሳካት ከተከናወኑ ስራዎች ወሰስጥም 5ሺህ 596 ሜትር የማስተላላፊያ ቧንቧ መስመር ዝርጋታ ፣4 ሺህ ሜትር ኩብ ኮንክሪት ውሃ ማጠራቀሚያ ፣2 ሺህ 660 ሜትር ኩብ ተገጣጣሚ ውሃ ማጠራቀሚያ እና ለውሃ ግፊት የሚያገለግሉ የተለያዩ  ጄኔሬተሮችና የውሃ ፍሳሽ አገልግሎት ባለ አራት  ፎቅ ህንፃ ቢሮ ግንባታ ተከናውኗል።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር