ደቡብ ግሎባል ባንክ ዓመታዊ ትርፉን በ252 በመቶ በማደሳግ 142 ሚሊዮን ብር አደረሰ

ደቡብ ግሎባል ባንክ በ2010 የሒሳብ ዓመት ከታክስ በፊት 142 ሚሊዮን ብር በማትረፍ ሒሳብ ዓመቱን ማጠናቀቁን አስታወቀ፡፡
ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ ከታክስ በፊት ያስመዘገበው የትርፍ መጠን ከባለፈው የሒሳብ ዓመት ጋር ሲነጻጸር በ252 በመቶ ዕድገት የተመዘገበበት ነው፡፡ ይህ የትርፍ መጠን ዕድገት በኢንዱስትሪው ቀዳሚው ያደርገዋል፡፡
በአዲሱ የሒሳብ አሠራር መሠረት በተዘጋጀው የሒሳብ ሪፖርት ባንኩ ለመጀመሪያ ጊዜ ትርፉን ከመቶ ሚሊዮን ብር በላይ ማሻገር መቻሉን አመላክቷል፡፡
ባንኩ ቅዳሜ ታኅሳስ 6 ቀን 2011 ዓ.ም. ባካሔደው ጠቅላላ ጉባዔ ላይ እንደተመለከተው ከታክስ በኋላ ያገኘው ትርፍ 106.6 ሚሊዮን ብር መድረሱን የባንኩ ዳይሬክተሮች ቦርድ ሊቀመንበር ገልጸዋል፡፡
ደቡብ ግሎባል ባንክ ኢንዱስትሪውን ዘግየት ብለው ከተቀላቀሉ ባንኮች መካከል አንዱ ሲሆን፣ በ2010 መጨረሻ ላይ የባንኩ ጠቅላላ ሀብት በ58 በመቶ ጨምሮ 3.3 ቢሊዮን ብር ደርሷል፡፡
ባንኩ በሒሳብ ዓመቱ የሰጠው የብድር መጠንም በ101 በመቶ በማደግ 1.58 ቢሊዮን ብር መድረሱም ተጠቅሷል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር