ሃዋሳ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ ዝዋይና ሻላ ሐይቆችን ከደለል ለመታደግ እየተሰራ ነው

የሃዋሳ፣ አባያ፣ ጫሞ፣ ዝዋይና ሻላ ሐይቆችን ከደለል ሙላት ለመከላከል በ65ሺህ ሄክታር መሬት ላይ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ እየተካሄደ መሆኑን የፌደራል ስምጥ ሸለቆ ሐይቆች ባለስልጣን አስታወቀ።
ባለስልጣኑ ሰሞኑን በሃዋሳ ከተማ ባዘጋጀው መድረክ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ የስድስት ወራት አፈጻጸምን ገምግሟል።
በባለስልጣኑ የተቀናጀ ተፋሰስ እንክብካቤና ወንዝ አመራር ዳይሬክተር አቶ ኤሊያስ ዶጊሶ እንደገለጹት፣ በበጀት ዓመቱ ሐይቆቹን ከደለል ለመከላከል በ23 ወረዳዎች ለሚካሄደው የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ ከ12 ሚሊዮን ብር በላይ በጀት ተመድቧል።
“እስካሁን በተከናወኑ ተግባራት ከታቀደው መሬት ግማሽ ያክሉ ለምቷል” ያሉት ዳይሬክተሩ፣ የሃዋሳን ሐይቅ ከደለል ለመከላከል በሲዳማ ዞን ቦርቻ ፣ ሸበዲኖና ወንዶገነት ወረዳዎች እንዲሁም በምዕራብ አርሲ ሻላ ወረዳ ላይ የተከናወኑ የእርከንና ሌሎች ስራዎች በተሞክሮነት የሚወሰዱ መሆናቸውን ለአብነት ጠቅሰዋል ።
የባለስልጣኑ ዋና ዳይሬክተር ዶክተር ከበደ ካንቹላ በበኩላቸው በተፋሰሶቹ የሚከናወኑ ተግባራት ጠቃሚ ቢሆኑም ሳይንሳዊ ይዘት እንዲኖራቸው ለማድረግ ከከፍተኛ ትምህርት ተቋማት ጋር በቅንጅት እየተሰራ መሆኑን ተናግረዋል ።
ሐይቆቹ እየደረሰባቸው ያሉ የጉዳት አይነቶችና መንስኤዎችን ለመለየት ጥናት እየተካሄደ መሆኑንም ተናግረዋል።
ባለስልጣን መስሪያ ቤቱ በመንግስት በጀት ታግዞ በሚያከናውነው ሥራ ብቻ ሐይቆቹን በዘላቂነት ከደለል መታደግ ስለማይቻል የተቀናጀ ጥረት ያስፈልጋል" ብለዋል።
በተለይ በሐይቆቹ ዳርቻ የሚከናወኑ የኢንቨስትመንት ሥራዎች ተፅዕኖ እንዳይኖራቸው ጥንቃቄ ሊደረግ እንደሚገባ አስገንዘበዋል።
በደቡብ ክልል ሲዳማ ዞን ወንዶገነት ወረዳ የአፈርና ውሃ ጥበቃ ሥራ አስተባባሪ አቶ ግርማ አንቀና በሰጡት አስተያየት የሃዋሳ ሐይቅን ከደልል ለመከላከል ባለፉት አምስት ዓመታት የተጀመሩ የአፈርና ውሀ ጥበቃ ስራዎች ዘንድሮም ተጠናክረው ቀጥለዋል።
ሙሉ ዜናውን ከእዚህ ያንቡ

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር