የፍቼ ጨምበላላ በዓል በሀገር አቀፍ ደረጃ በሀዋሳ ይከበራል


(ኤፍ.ቢ.ሲ) የሲዳማ ብሔር ፍቼ ጨምበላላ የዘመን መለወጫ በዓልን በተለየ ሁኔታ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው።
በዓሉ በአለም ቅርስነት ከተመዘገበ በኋላ ለመጀመሪያ ጊዜ የፊታችን ሰኔ 23 እና 24 በዋናነት በሃዋሳ ከተማ በተለያዩ ዝግጅቶች ይከበራል፡፡
ይህን ተከትሎም በሲዳማ ዞን በሚገኙ የተለያዩ ወረዳዎች በዓሉ ለሁለት ሳምንት እንደሚከበር ተመልክቷል።
የደቡብ ክልል ባህልና ቱሪዝም ቢሮ ምክትል ኃላፊ አቶ ለማ መለሰ እንደገለጹት፥ ቀደም ሲል በብሔሩ ተወላጆች ብቻ ይከበር የነበረው በዓል ለመጀመሪያ ጊዜ ሀገር አቀፍ ይዘት እንዲኖረው አድርጎ ለማክበር ዝግጅት እየተደረገ ነው፡፡
የፍቼ ጨምባላላ በሃገሪቱ በማይዳሰስ ቅርስነት ከተመዘገበው የመስቀል በዓል ቀጥሎ ሁለተኛ ሆኖ በተባበሩት መንግስታት የትምህርት፣ የሳይንስና የባህል ማዕከል (ዩኔስኮ) የተመዘገበው ባለፈው ህዳር ወር መሆኑ ይታወሳል።

Comments

Popular posts from this blog

የሲዳማ ክልል ባለስልጣናትን ጨምሮ የተገለገሉት የሰሞኑ የቻርተር አውሮፕላን በረራዎች!

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ብሔር በሰፊው የሚታወቀው የ"አፊኒ" ባህላዊ የዳኝነት ስርዓትና የአዋጅ ረቂቅ ተሞክሮ በአማራ ክልል ባህር ዳር ከተማ በተዘጋጀው የውይይት መድረክ ላይ ቀረበ