አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሃዋሳ ከነማ ክለብን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተሰማ

አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሃዋሳ ከነማ ክለብን ለማሰልጠን ከጫፍ ደረሰ
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የሃዋሳ ከነማ ክለብን ለመቀላቀል ከጫፍ መድረሱ ተሰማ።
የቀድሞው የኢትዮጵያ ቡና፣ አዳማ ከነማ፣ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክና ደደቢት ክለቦች አሰልጣኝ ውበቱ አባተ ለሱዳኑ አል አህሊ ሸንዲ ዋና አሰልጣኝ ሆኖ ሰርቷል።
አሰልጣኙ ቀደም ሲል ለስድስት ወራት እንዲያሰለጥን ጥያቄ ቀርቦለት የነበር ቢሆንም ባለመስማማቱ፥ ክለቡ በአዲስ መልክ የአንድ ዓመት ከስድስት ወራት ኮንትራት አቅርቦለት ከስምምነት ላይ መድረሱ ነው የተነገረው።
በኢትዮጵያ ፕሪምየር ሊግ ውጤት እየራቀው የሚገኘውን ሀዋሳ ከነማ ወደ ውጤት ለመመለስ የአሰልጣኙ ወደክለቡ መምጣት ከፍተኛ ጠቀሜታ እንዳለውም ተጠቁሟል።
አሰልጣኝ ውበቱ አባተ የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ በአዲስ መልክ ከተዋቀረ በኋላ ኢትዮጵያ ቡና ብቸኛውን የሊጉን  ዋንጫ እንዲያጣጥም በማገዝ ታሪካዊ ስራ መስራቱም አይዘነጋም።

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር