ኣንድባል የምጋሩ የሲዳማ ሴቶች የመሬት ባለቤትነት ወይም የመጠቀም መብት እስከምን ደረጃ ነው?

በሲዳማ የሴቶች የመሬት ባለቤትነት በተለይ ኣንድ ባል የሚጋሩ ምስቶች (ባለቤቶቻቸው ከኣንድ በላይ ምስቶች ያሏቸው ከሆነ) የመሬት ባለቤትነት ወይም የመጠቀም መብት እስከምን ደረጃ ነው?

Impacts of Polygamous Marriage on Women's Land Rights in Ethiopia: Its Impacts on Women's Rural Land Rights in Sidama Zone,Southern Nations, Nationalities and Peoples Regional State በምል ርዕስ በቴሬዛ ጴጥሮስ የተዘጋጀው መጽሐፍ በዚህ ጉዳይ ላይ የተሰራውን ጥናት ይዞ ቀርቧል።

መጽሐፉ ከኣንድ በላይ ጋብቻ በሴቶች የመሬት ባለቤትነት እና ተጠቃሚነት ላይ ያለውን ተጽዕኖ ከሲዳማ ሴቶች ኣንጻር የምተነትን ሲሆን ያለውን ኣሉታዊ ገጽታን ያብራራል።

መጽሐፉ ሴቶችን በኢኮኖሚ ብሎም በሌሎች ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ መስኮች ራሳቸውን ለማስቻል በመንግስት እና መንግስታዊ ባልሆኑ ድርጅቶች ለምደረገው ስራ ኣጋዥ የሆነ መረጃ ይዟል።

በኣጠቃላይ ከኣንድ በላይ ጋብቻ በሲዳማ ሴቶች ላይ ያለውን ኣሉታዊ ገጽታ በኣግባቡ ለመረዳት መጽሐፉ ጠቃሚ መረጃ ይስጣል።


ለተጨማሪ መረጃ ከታች ይጫኑ፦ http://www.amazon.com/Impacts-Polygamous-Marriage-Womens-Ethiopia/dp/3659197424/ref=sr_1_4/186-0184352-4930450?s=books&ie=UTF8&qid=1409839362&sr=1-4&keywords=Sidama

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር