የኤድስ ስርጭትን እኤአ እስከ 2030 ማቆም እንደሚቻል ተመድ ገለጸ

ሐምሌ ፱(ዘጠኝ)ቀን ፳፻፮ ዓ/ም ኢሳት ዜና :-የተባበሩት መንግስታት ድርጅት የኤድስ ኤጀንሲ እንደገለጸው ኢትዮጵያና ደቡብ አፍሪካን ጨምሮ በብዙ አገሮች የኤደስ ወረርሽኝ ስርጭት እየቀነ ሲሆን ፣
ስርጭቱንም ከ14 አመታት በሁዋላ  ማቆም እንደሚቻል ገልጿል።
አሁንም በርካታ ዜጎች መድሃኒት አጥተው በመሰቃየት ላይ መሆናቸውን ድንበር የለሽ የሃኪሞች ቡድን ገልጿል። በዚህ አመት በአለም ደረጃ 2 ሚሊዮን 300 ሺ ሰዎች ብቻ በኤች አይ ቪ ቫይረስ ተይዘዋል።
በአጠቃላይ በአለም ላይ 35 ሚሊዮን የሚሆን ህዝብ በቫይረሱ ተይዟል።
ምንጭ፦ ኢሳት

Comments

Popular posts from this blog

ስለከሸፈው “መክሸፍ እንደ ኢትዮጵያ ታሪክ” ጥራዝ አንዳንድ ነጥቦች

SIDAMA Micro-Finance Institution

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት