በተለያዩ የሲዳማ ከተሞች በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ማህበራት ተደራጅተው ያሉ የሲዳማ ወጣቶች የመንግስት ትኩረት ያሻቸዋል ተባለ

በሃዋሳ ከተማ በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ኢንዱስትሪ ስር የታቀፉ የሲዳማ ወጣት ልጆች በቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ በመጨመር ላይ መሆናቸውን ሪፖርተራችን ሰሞኑን ከሃዋሳ ከተማ ያጠናቀረው ዘገባ ኣመልክቷል።
የሲዳማ ወጣቶች በድንጋይ መፍጨት ስራ፤ በኮብል ስቶን ስራ፤ ቢም እና ፕረካስት ስራ የብረታብረት እና የእንጨት ስራ እና በመሳሰሉት የስራ መስኮች በኣነስተኛ እና ጥቃቂን ኢንዱስትሪ በማህበር በመደራጀት በመስራት ላይ ሲሆኑ፤ በራሳቸው ማለትም ብቻቸውን ተደራጅተው ካቋቋሙት ማህበራት በተጨማሪ ከሌሎች ብሄር እና ብሄረሰቦች ልጆች ጋር ተደራጅተው በመስራት ላይ መሆናቸው ተሰሞቷል።
በሃዋሳ ከተማ ውስጥ ካሉት በተጨማሪ በሁሉም የሲዳማ ከተሞች በመስል መልኩ የማህበራት በመደራጀት በተለያዩ የስራ መስኮች የገንዘብ እና የስልጣና ድጋፎችን ኣግኝተው የራሳቸውን እና የቤተሰቦቻቸውን ኑሮ ለማሻሻል በመጣር ላይ ናቸው።
ወጣቶቹ በጥቃቂን እና ኣነስተኛ ማህበራት ተደራጅተው ስራ መስራታቸው መልካም ሆኖ ሳለ በምሰሩት ስራ ያሳዩት ወጤት ብዙም ኣጥጋብ ኣይደለም።
በእርግጥ ከተለያዩ የትምህርት ተቋማት የወጡትን ጨምሮ ብዙ የተግባር ስራ ልምድ የሌላቸው ጊዜያቸውን ባልቧለ ቦታ ያሳልፉ የነበሩት ወጣቶች ወደ ስራ ገብተው ውጤታማ መሆን መጀመራቸው የምካድ ባይሆንም፤ እያስመዘጋቡ ያሉትን ውጤት ከሌሎች ክልል ማህበራት የስራ ውጤቶች ጋር ሲወዳደር ልዩነቱ የእትዬ ሌሌ ነው። ከዚህ ባሻገር በስራ ላይ ውጤት በማጣታቸውም የተነሳ እስከ መበተን የደረሱም ኣሉ።
እንደ ጥቻ ወራና ዘጋባ ከሆነ በሃዋሳ ከተማ ሲዳማውያን ብቻ ተደራጅተው ካቋቋሟቸው ማህበራት መካከል ሁለቱ በኣያያዝ ችግር የተነሳ ፈርሰው ከዚህ በፊት ለስራ በከታማዋ ማዘጋጃ የተሰጣቸውን የስራ ቦታ ሊያጡ የግድ ሆኖባቸዋል።
የሲዳማ ወጣቶች ራሳቸውን እና ቤተሰባቸውን ብሎም ሳይማር ያስተማራቸውን ማህበረሰብ ለመርዳት እንድያስችላቸው እና በተሰማሩባቸው የስራ መስኮች ውጤታማ እንድሆኑ የዞኑ መንግስት ኣሁን በማድረግ ላይ ያለው ድጋፍ እንዳለ ሆኖ ማህባራቱ ባለባቸው ድክመቶች ላይ ትኩረት ስጥተው Supportive Monitoring and evaluation ስራዎችን ብሰራ መልካም ነው ።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር