በሀዋሳ ከተማ አንድ ነዳጅ የጫነ ቦቴ በእሳት በመያያዙ በንብረት ላይ ጉዳት ደረሰ

አዋሳ ጥር 12/2006 በሀዋሳ ከተማ ከትናንት በስቲያ ምሽት አንድ የነዳጅ መጫኛ ቦቴ ባልታወቀ ምክንያት በእሳት በመያያዙ ተሽከርካሪውና ነዳጁ መውደማቸዉን  የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን አስታወቀ ።
የክልሉ ፖሊስ ኮሚሽን የህዝብ ግንኙነት ኃላፊ ዋና ኢንስፔክተር ዳንኤል ገዛኽኝ ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በእለቱ ከምሽቱ  አንድ ሰዓት ገደማ ላይ አደጋዉ የደረሰዉ ቦቴዉ የጫነዉን ነዳጅ በኦይል ሊቢያ ነዳጅ ማደያ ዉስጥ በማራገፍ ላይ እንዳለ በተነሳዉ ድንገተኛ እሳት ነዉ  ።
የነዳጅ መጫኛ ቦቴዉ  በእሳት በመያያዙ ሾፌሩ በፍጥነት መኪናውን ከነዳጅ ማደያው በማውጣትና ወደ ዋናው መንገድ ላይ ወስዶ በማቆም እሳቱ ወደ  እንዳይዛመት በማድረግ ሊደርስ ይችል የነበረዉን አደጋ መከላከል መቻሉን አስታዉቀዋል ።
አሽከርካሪውን በፍጥነት ከማደያዉ አካባቢው በማራቁም  በአቅራቢያ  በሚገኙ ሁለት ሌሎች የነዳጅ ማደያ ጣቢያዎች ላይ ሊደርስ የሚችለዉን  አደጋ መከላከል መቻሉን  ተናግረዋል ።
እሳቱን ለማጥፋት የከተማው ነዋሪዎችና የፖሊስ አባላት ከፍተኛ ርብርብ ማድረጋቸዉንና በንብረት ውጪ በሰው ህይወት  ላይ የደረሰ ጉዳት አለመኖሩን ዋና ኢንስፔክተሩ ጠቁመው የአደጋው መንስኤና የደረሰው ውድመት እየተጣራ ነዉ ብለዋል ።
የነዳጅ ቦቴው በውስጡ ባሉት አራት ክፍሎች  በአጠቃላይ እስከ 600 ሺህ ሊትር ነዳጅ የመያዝ አቅም እንዳለው ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸዉ ባለሙያዎች ጠቁመዋል ።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር