የሲዳማ ቡና ኣምራች ኣርሶ ኣደር የቡና ምርቱን በዝቅተኛ ዋጋ በመሸጥ ላይ ነው፤ ከሲዳማ ዞን ዘንድሮ ከ 32 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ በመስ፤ የሲዳማ ቡና ኣምራች ኣርሶ ኣደር የቡና ምርቱን በዝቅተኛ ዋጋ በመሸጥ ላይ ነው

በሲዳማ ዞን ዘንድሮ ከ32 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ እየተሰራ መሆኑ ተገለጸ
ሃዋሳ ህዳር 25/2006 በሲዳማ ዞን በተያዘው የበጀት ዓመት ከ32 ሺህ ቶን በላይ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ ታቅዶ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብይትና ህብረት ስራ መምሪያ አስታወቀ፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት ከእቅዱ ከ5ሺህ ቶን በላይ ቡና ለገበያ መቅረቡም ተገልፀዋል፡፡ የመምሪያው ኃላፊ አቶ ዘውዴ ገቢባ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት በበጀት አመቱ ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብ የታቀደው ቡና ካለፈው ዓመት ተመሳሳይ ወቅት ጋር ሲነፃፀር ከ7 ሺህ 500 ቶን በላይ ብልጫ አለው፡፡ ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብ ከተያዘው እቅድ ውስጥ 29 ሺህ 500 ቶን የታጠበ ሲሆን ቀሪው 3 ሺህ ቶን ደግሞ ጀንፈል ቅሽር ቡና መሆኑንም አመልክተዋል፡፡ በዞኑ ቡና አምራች ከሆኑ የተለያዩ ወረዳዎች ለማእከላዊ ገበያ ለማቅረብ የተያዘው ዕቅድ ለማሳካት በየደረጃው የተቋቋሙ የቡና ጥራትና ንግድ ቁጥጥር አስተባባሪ ግብረ ሃይሎችን በማጠናከር ህገ ወጥ ንግድ እንዲቆም ለማድረግ ተከታታይነት ያለው የግንዛቤ ማስጨበጫ ስልጠና ለአስፈጻሚዎች፣ ለአምራቹና ለአቅራቢዎች በመሰጠት ላይ ይገኛል ብለዋል፡፡ እንዲሁም ከግል አቅራቢዎች ባሻገር በተለይ የመሰረታዊ ህብረት ስራ ማህበራትን የገበያ ድርሻ አሁን ካለበት 11 በመቶ ወደ 20 በመቶ ለማሳደግ እየሰሩ መሆናቸውን የመምሪያው ኃላፊ ተናግረዋል፡፡ በዞኑ ቡናን አዘጋጅተው ለማዕከላዊ ገበያ በማቅረብ በመሳተፍ ላይ ያሉ 51 መሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራት፣ 249 የግል ባለሀብቶች እንዲሁም ከቡና ተክል ልማት ድርጅት በተጨማሪም በስራውም ላይ 95 የቡና ማዘጋጃ የህብረት ስራ ማህበራት ኢንዱስተሪዎች መሳተፋቸውን አቶ ዘውዴ አስታውቀዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት በመሰረታዊ የህብረት ስራ ማህበራትና በግል ባለሃብቶች ከእቅዱ ከ5 ሺህ ቶን በላይ የታጠበና ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ ለማቅረብ መቻሉን ተናግረዋል፡፡ በዞኑ ባለፈው የበጀት ዓመት 23 ሺህ ቶን የታጠበና 3ሺህ ቶን ያልታጠበ ቡና ለማዕከላዊ ገበያ መቅረቡን የገለጹት አቶ ዘውዴ በእድገትና ትራንስፎርሜሽን እቅድ ዘመን መጨረሻ በዞኑ ለማዕከላዊ ገበያ የሚቀርበው ቡና ወደ 53 ሺህ ቶን ለማድረስ ግብ ተጥሎ የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑን አመልክተዋል፡፡
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=14167&K=1

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር