ሰሞኑን በደቡብ መገናኛ ብዙሃን ሲዳማን በተመለከተ የተሰራጩ ዜናዎች


በሲዳማ ዞን ቦርቻ ወረዳ በተያዘው በጀት ዓመት 48 ኪ.ሜትር የመንገድ ሥራ ለማከናወን ታቅዶ እየተሠራ መሆኑን የወረዳው መንገድ ትራንስፖርት ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡ 
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ አበባየሁ በየነ እንደገለጹ በወረዳው 162 ኪ.ሜ ቀበሌን ከቀበሌ፣ ወረዳን ከወረዳ የሚያገናኝ መንገድ ለመሥራት ዕቅድ ተይዟል፡፡ 
በ2005 ዓ.ም 58 ኪ.ሜትር የመንገድ ሥራ በቀበሌ ተደራሽ መንገድ ኘሮግራም ለመስራት ታቅዶ ወደ ሥራ የተገባ መሆኑን ተናግረው ከዚህም፣ በ3 ኪሎ ሜትር መንገድ አፈር የማልበር ስራ በ3 ኪ.ሜትር ድንጋይ የማንጠፍ ተግባር የተከናወነ ሲሆን 15.8 ሜትር በግል ተቋራጮች በኩል በተፈጠረ ክፍተት በተያዘለት ጊዜ አለመጠናቀቁን ተናግረዋል፡፡ 


ባለፈው ዓመት ህብረተሰቡን በማሳተፍ የተሰራው የመንገድ ሥራ በገንዘብ ሲተመን ከ2 ሚሊዮን ብር በላይ የሚገመት መሆኑን  አስረድተዋል፡፡
በተያዘው በጀት ዓመት 48 ኪ.ሜትር ቀበሌን ከቀበሌ የሚያገናኝ መንገድ ለመሥራት ዕቅድ እንደተያዘ ጠቁመው ይህ ሥራም፣ ለሴቶች፣ ለሥራ አጥ ወጣቶች የሥራ ዕድል እንደሚፈጥርላቸው ተናግረዋል፡፡ 
በዚህ ሥራም 22 ሚሊዮን ብር ወጪ እንደሚደረግና ከ7 መቶ በላይ ሰዎች ያሳትፋል ተብሎ እንደሚጠበቅ ጠቁመዋል፡፡ ሪፖርተራችን አካሉ ጥላሁን ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው፡፡



በዘንድሮው የምርት ዘመን ከሁለት ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት መታቀዱን የሲዳማ ዞን የሸበዲኖ የወረዳ ግብርና ጽህፈት ቤት አስታወቀ፡፡
በወረዳው ከሚገኙ የግብርና ባለሙያዎች ፣ የቀበሌ አመራሮችና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ጋር በ2ዐዐ5 ዓ/ም የበልግና የመኸር እርሻ እንዲሁም በ2ዐዐ6 የመሰኖ ልማት ቅድመ ዝግጅት ዙሪያ ውይይት ተካሂዷል፡፡
የጽህፈት ቤቱ ኃላፊ አቶ ለጣ ለገሰ በዚህን ጊዜ እንዳሉት በወረዳው 17 ቀበሌያት የሚገኙ የውሃ አማራጮችን በመጠቀምና 89 ሺህ 958 አርሶ አደሮችን በማሳተፍ 2 ሺህ 7ዐዐ ሄክታር መሬት በመስኖ በማልማት  ከ2 ሚሊዮን ኩንታል በላይ ምርት ከተለያዩ ሰብሎች ለመሰብሰብ ታቅዷል፡፡
ወረዳው የበርካታ ወንዞችና ምንጮች ባለቤት መሆኑን የጠቀሱት ኃላፊው አርሶ አደሩ የተፈጠረለትን ምቹ የውሃ አማራጭ ተጠቅሞ በዓመት ሁለቴና ከዚያ በላይ በማምረት ምርትና ምርታማነትን ማሳደግ እንደሚችል ጠቁመዋል፡፡
የመሰኖ ሥራን አሰልቺ አድርጐ የማየትና፣ የግብአቶች ወቅቱን ጠብቆ አለመቅረብ ባለፉት የምርት ወቅቶች የተስተዋሉ ክፍተቶች በመሆናቸው ችግሮቹን ለመቅረፍ አርሶ አደሩና ሌሎች ባለድርሻ አካላት ያላሰለሰ ጥረት ማድረግ እንደሚጠበቅባቸው ተገልጿል፡፡ የወረዳው የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንደዘገበው፡፡

ጥራቱን የጠበቀ ትምህርት ለዜጎች በማድረስ የምዕተ አመቱን የትምህርት ግብ ለማሳካት ትኩረት ተሰጥቶ አየስራ መሆኑን በሲዳማ ዞን የበንሳ ወረዳ ትምህርት ጽህፈት ቤት ገለፀ፡፡
ጽህፈት ቤቱ በወረዳው ለሚገኙ ርዕሳነ መምህራናንና ሱፐርቫይዘሮች በተለያዩ ርዕሰ ጉዳዮች ዙሪያ የክህሎት ስልጠና ሰጥቷል፡፡
በዚሁ ጊዜ የወረዳው ምክትል አስተዳደርና የትምህርት ጽህፈት ቤት ኃላፊ አቶ ዳዊት ኦዳ እንደገለፁት የምዕተ አመቱን የትምህርት ግብ ለማሳካት ጥራት ያለውን ትምህርት ለዜጎች በማድረስና የተማሪዎችን ውጤት ለማሻሻል በ2ዐዐ5 ዓ/ም በርካታ ሥራዎች ተሰርተዋል፡፡
የተማዎችን ውጤት ለማሻሻል በተሰሩ ሥራዎች በ2ዐዐ5 ዓ/ም ከ8ኛ ክፍል 8ዐ በመቶ ፣ ከ1ዐኛ ክፍል 85 በመቶ እንዲሁም ከ12ኛ ክፍል 87  በመቶ ማሳለፍ መቻሉን ገልፀ ይህም ከ2ዐዐ4 የትምህርት ዘመን ውጤት ጋር ሲነፃፀር ብልጫ እንዳለው ጠቁመዋል፡፡
የስልጠናው ተሳታፊዎች ስልጠናው ለቀጣይ ለሥራቸው ምቹ ሁኔታ እንደሚፈጥርላቸውና የተያዘውን  ግብ ለማሳካት የበኩላቸውን ድርሻ ለመወጣት መዘጋጀታቸውን ተናግረዋል፡፡ ፍፁም ታደሰ ከበንሳ ቅርንጫፍ እንደዘገበው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር