ለፍትህ ስርዓቱ ማሻሻያ እና ለፍትሀብሄር ጉዳዮች ሚኒስቴሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው

የወንጀል ስጋቶችን በመቀነስ የሀገሪቱን የሀገሪቱ ሰላምና ደህንነት እንዲጠበቅ የተጣለባቸውን ሀላፊነት እንደሚወጡ የፍትህ ሚኒስቴርና ተጠሪ ተቋማት ሰራተኞች አስታወቁ፡፡
ሚኒስቴር መ/ቤቱና ተጠሪ ተቋማት የፍትህ ስርዓቱ ማሻሻያ ማዕቀፍ  የሀገሪቱን የዕድገትና ትራንስፎርሜሽን በፍትህ ዘርፉ የደረሰበትን ደረጃ ገምግሟል፡፡
የፍትህ ሚንስትሩ አቶ ጌታቸው አምባዬ  እንደተናገሩት የዜጎች ቻርተር ሰነድ የለውጥ መሳሪያና የተልዕኮ ማሳለጫ እንዲሆን የህዝቡን ተሳትፎ የለውጡ ሂደት አካል አድረጎ መንቀሳቀስ እንደሚገባ አሳስበዋል፡፡ የዘርፉ ሰራተኛም መልካም አስተዳደርን በማስፈን የህዝቡን ጥቅም በማስቀደም ተገቢውን አገልግሎት ሊሱጡ ይገባልም ብለዋል፡፡
ሚንስትር ዴኤታው አቶ ብርሀኑ  ፀጋዬ  በበኩላቸው ለፍትህ ስርዓት ማሻሻያ እና ለሌሎች የፍትሀብሄር ጉዳዮች ሚኒስቴሩ ትኩረት ሰጥቶ እየሰራ ነው ብለዋል፡፡በተለይም የተቀናጀ የመረጃ ስርዓት ፕሮጀክት፣ነባር ህጎችን ማሰባሰብና ማጠቃለል፣የፍትህ አካላትአገልግሎት አሰጣጥ ውጤታማ፣ቀልጣፋና ተደራሽ እንዲሆን ድጋፍና ክትትል በማድረግ ጭምር እየተሰራ እንደሆነ ተናግረዋል፡፡
የግምገማው ተሳታፊ ሰራተኞች በበኩላቸው በፍትፍ ስርዓቱ የተቀመጠውን የአምስት አመት እቅድ እውን ለማድረግ እንደሚረባሩ አስታውቀዋል፡፡በተለይም በሀገሪቱ የወንጅል ስጋቶችንበመቀነስ የተጀመረውን ልማትና ሰላም ለማጠናከር የበኩላቸውን እንደሚወጡም ተናግረዋል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር