በሲዳማ ዞን ዘንድሮ ከ51 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ይለማል

ሃዋሳ ጥቅምት 27/2006 በሲዳማ ዞን በዘንድሮ የበጋ ወራት ከ51 ሺህ ሄክታር በላይ መሬት በመስኖ ለማልማት እቅድ ተይዞ እየተሰራ መሆኑን የዞኑ ግብርና መምሪያ አስታወቀ ። በመምሪያው የግብርና ልማት እቅድ፣ ዝግጅትና ከትትል የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ ደርቤ በትራ ትናንት ለኢትዮጵያ ዜና አገልግሎት እንደገለጹት የመስኖ የሚካሄደዉ በዞኑ 19 ወረዳዎች በመስመር መዝራትን ጨምሮ ሌሎች የተሻሻሉ የግብርና ቴክኖሎጂዎችን በመጠቀም ነው፡፡ በመስኖ ከሚለማው መሬት 9 ነጥብ አራት ሚሊዮን ኩንታል የሚደርስ የስራስር፣ የአገዳ እህሎች፣ የጥራጥሬ ሰብሎችና የተለያዩ የጓሮ አትክልት ምርት እንደሚገኝ አስታዉቀዋል ። ለዚሁ መስኖ ልማቱ 6ሺህ 491 የሞተር ፓምፖች፣ ከ2ሺህ 900 በላይ የእጅ ጉድጓድ ውሃ ።7 ሺህ 950 ምንጮችና ወንዞች በባህላዊ ዘዴ መጥለፍ ጥቅም ላይ እንደሚዉሉ ገልጠዋል ። ለመስኖ ልማቱ አገልግሎት ላይ የሚውል ከ38 ሺህ ኩንታል በላይ የቦቆሎ፣የቦሎቄ፣ አኩሪ አተርና የጓሮ አትክልት ምርጥ ዘር እንዲሁም 34 ሺህ 580ኩንታል ማዳበሪያ ለአርሶ አደሮቹ ለማቅረብ ዝግጅት ላይ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ በመስኖ ልማቱም 230 ሺህ የሚጠጉ አርሶ አደሮች የሚሳተፉ ሲሆን ከመካከላቸዉ 30 በመቶ የሚሆኑት ሴት አርሶ አደሮች እንደሚሆኑ አስታዉቀዋል ። ዘድደሮ በመስኖ የሚለማዉ መሬት ካለፈው ዓመት በ13 ሺህ ሄክታር ፣ ይገኛል ተብሎ የሚጠበቀዉ ምርት ድግሞ በ3 ሚሊዮን ኩንታል ብልጫ ይኖረዋል ብለዋል ። የዞኑ አርሶ አደሮች ቀደም ሰል የዝናብ ወቅትን ጠብቀዉ በዓመት አንድ ጊዜ ብቻ የሚያካሂዱት የእርሻ ስራ ዉጤታማ ባለመሆኑ የመስኖ ልማት በመጠቀም በዓመት ከሁለት ጊዜ በላይ በማምረት የምግብ ዋስትናን ለማረጋገጥ ቁልፍ አማራጭ ሆኖ ተገኝቷል ብለዋል ። እቅዱን ስኬታማ እንዲሆን ከ2 ሺህ 240 ለሚበልጡ ለሰብል፣ ለተፈጥሮ ሃብትና ለእንስሳት እርባት ልማት ሰራተኞች እንዲሁም ለወረዳና ለዞን ግብርና ባለሙያዎች የአቅም ግንባታ ስልጠና መሰጠቱን ተናግረዋል፡፡ እንዲሁም በልማት ቡድንና አንድ ለአምስት አደረጃጀት ጠንካራ የግብርና ልማት ሰራዊት ንቅናቄ የመፍጠር፣ግንባር ቀደም ተሳታፊ አርሶአደሮች የግንዛቤ ማስጨበጫ ትምህርትየመስጠትና ሌሎችም ለልማቱ አጋዥ የሆኑ ስራዎች ከዞን ጀምሮ በመከናወን ላይ እንደሚገኝ አመልክተዋል፡፡ በማልጋ ወረዳ የጉጉማ ቀበሌ አርሶ አደር አቡሌ ክፍሌ እና መላኩ አበጄ በሰጡት አስተያየት ከሶስት ዓመት በፍት የዝናብ ወቅትን ብቻ ጠብቆ ማምረቱ ዉጤታማ ባለመሆኑ ለችግር ሲዳረጉ መቀየታቸዉን አመልክተዉ አሁን ግን በመስኖ ልማት በመሳተፍ ከሚያገኙት ምርት ተጠቃሚ መሆናቸዉን አስታዉቀዋል ።
http://www.ena.gov.et/Story.aspx?ID=13264&K=1

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር