የሪፖርተር ጋዜጣ አዘጋጅ አዋሳ ተወስዶ ታሰሮ ተፈታ _ የክልሉ መንግስት ሚዲያን በተመለከተ ስሱ ሆኖ ይሁን?

በተለያዩ ኣጋጣሚዎች ሚዲያዎች በየትኛውም ኣገር የተሳሳተ ዜና ይዘው ልወጡ ይችላሉ፤ መቼም ሰዎች ነንና ስህተት ኣይጣፋም። ለዚህም ይመስላል በጋዜጠኝነት ስራ ላይ ይህን መሰል ስህተት ስፈጠር ጋዜጣው ወይም ዜናውን ያሰራጨው ሚዲያ ዘጋባው ስህተት መሆኑን ከተቀበለ በተመሳሳይ የጋዜጣው ኣምድ ላይ ለምሳሌ የተሳሳተ መረጃ በዜና መልክ ተሰራጭቶ  ከሆነ በዜና ኣምዱ ላይ የተሰራጨው ዜና ስህተት መሆኑን ገልጾ፤ ማረሚያ  መስጠት ያስፈልጋል።በዚህ ነገሩ ይቋጫል።

እንግድህ በሪፖርተር ጋዜጣ ላይ “በደቡብ ክልል ሶስት ምክትል ርዕሳነ መስተዳድሮች ከስልጣናቸው ተነሱ” በሚል ከወጣው ዘገባ ጋር ተያይዞ ጋዜጣው ዘገባው ስህተት መሆኑን ኣምኖ ማስተካከያ የሰጠ ቢሆንም ሰሞኑን የጋዜጣው ማኔጂን ኤዲተር ከአዲስ አበባ ወደ አዋሳ ተወስዶ ለአንድ ቀን ታሰረው ተለቋል፡፡

እንደጋዜጣው ዘገባ ከሆነ ፦ከትላንት በስቲያ ሐሙስ ሶስት ሰዎች “በተጠረጠሩበት ወንጀል ይፈለጋሉ” የሚል መጥሪያ በመስጠት አዘጋጁን ከቢሮው እንደወሰዱትና እንደታሰረ የተገለፀ ሲሆን፤ ትላንት ጠዋት ፍ/ቤት ይቀርባል ተብሎ ቢጠበቅም “ዳኞች አልተሟሉም፤ ስንፈልግህ እንጠራሃለን” ተብሎ መለቀቁ ታውቋል፡፡

እንግድህ ጋዜጣው ስህተቱን ኣምኖ ማስተካከያ ስጥቶ እያለ በክልሉ መንግስት በጋዜጣ ኣዘጋጁ ላይ የተወሰደው ይህን መሰል እርምጃ ክልሉ ሚዲያን በተመለከተ ምን ያህል ስሱ መሆኑን ያሳያል።    

ምንጭ፦http://www.addisadmassnews.com/index.php?option=com_k2&view=item&id=13046:%E1%8B%A8%E1%88%AA%E1%8D%96%E1%88%AD%E1%89%B0%E1%88%AD-%E1%8C%8B%E1%8B%9C%E1%8C%A3-%E1%8A%A0%E1%8B%98%E1%8C%8B%E1%8C%85-%E1%8A%A0%E1%8B%8B%E1%88%B3-%E1%89%B0%E1%8B%88%E1%88%B5%E1%8B%B6-%E1%89%B3%E1%88%B0%E1%88%A8&Itemid=180

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር