ኢትዮጵያ የቀርከሃ ዘላቂ ልማት መሰረት በመጣል አረንጓዴ ኢኮኖሚን ግንባታ ስትራቴጂ ቀይሳለች -ግብርና ሚኒስቴር


ኢትዮጵያ የቀርከሃ ተክልን ዘላቂ ልማት መሰረት በመጣል አረንጓዴ ኢኮኖሚዊ  የግንባታ ስትራቴጂ መቀየሷንና የዘርፉን ኢንዱስትሪ የማስፋፋት ስራም አጠናክራ መቀጠሏን የግብርና ሚኒስቴር አስታወቀ፡፡


አህጉራዊ የቀርከሃ አውደ ጥናት መጋቢት 6/2005 ዓ.ም አዲስ አበባ ውስጥ ሲጀመር የግብርና ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ምትኩ ካሳ እንዳስታወቁት በኢትዮጵያ ያለው የቀርከሃ ሃብት እንዲጠበቅና በአግባቡ ጥቅም ላይ እንዲውል የሚያስችል ስትራቴጂ ተነድፎ ተግባራዊ እየተደረገ ነው፡፡

የቀርከሃ ልማት በአገሪቱ እንዲጠናከርና ከተክሉ የሚገኙ ልዩ ልዩ ውጤቶችንና ምርቶችን በማስፋፋት ጥቅም እንዲውሉ መንግስት የጀመረውን ጥረትና ቁርጠኝነት ደረጃ በደረጃ እያጠናከረ መሆኑን ጠቁመዋል፡፡

ኢትዮጵያ የዓለም ዓቀፉን የቀርከሃና ራታን ኔት ወርክ ለሁለት ዓመታት በሊቀ መንበርነት እንድትመራ በ15ኛው የተቋሙ የምስረታ ዓመት ላይ በቅርቡ መመረጧን አስታውሰው የተቋሙ ምክር ቤት በቻይና ባካሄደው 8ኛ ጉባኤ ይህን ኃላፊነት ለኢትዮጵያ መስጠቱንም ገልጸዋል፡፡

በመሆኑም በአውሮፓውያን 2014 ዘጠነኛውን የኔትወርኩ ምክር ቤት ጉባዔን ኢትዮጵያ እንድታስተናግድ መመረጧን ገልጸው ጉባኤውን አዲስ አበባ ለማስተናገድ መዘጋጀቷንም አመልክተዋል፡፡

ኢትዮጵያ ከ15 ዝርያ የሚበልጡ የቀርከሃ ተክል ያለባት አገር መሆኗን አስታውሰው ይህን ተክል በማልማት የአካበቢ መጎሳቆልንና የአየር ንብረት ለውጥን ለመከላከል አገራዊና አህጉራዊ ብቻ ሳይሆን ዓለም ዓቀፋዊ ሚናዋን ኢትዮጵያ እንደምትጫወት አስታውቀዋል፡፡

የኢንዱስትሪ ሚኒስትር ዴኤታው አቶ ታደሰ ኃይሌ በበኩላቸው ቀርከሃ ለፋብሪካ ግብዓት ከሚውሉ የደን ውጤቶች አንዱ በመሆኑ ለኢንቨስትመንትና የስራ ዕድል በመፍጠር ለድህነት ቅነሳ አስተዋጽኦ ስለሚያደርግ መንግስት ልዩ ትኩረት ሰጥቶታል ብለዋል፡፡

ከቀርከሃ የደን ሃብት ለቤት ግንባታና ለተለያዩ የቁሳቁስ ምርት ከመጥቀሙ ባሻገር ለምግብ ዋስትና የበኩሉን ሚና ስለሚጫወት አገሪቱ ለምትከተለው አረንጓዴ ኢኮኖሚ የድህነት ቅነሳ ስትራቴጂ መሰረት በመሆኑ ዋነኛ የትኩረት አቅጣጫ መሆኑን አስረድተዋል፡፡

በዓውደ ጥናቱ ላይ በኢትዮጵያውያን ባለሃብቶችና የምርምር ተቋማት የተመረቱ የቀርከሃ ውጤቶች በዓውደ ራዕዩ የቀረቡ ሲሆን ከሰሃራ በታች ያሉ 12 የቀርከሃ አምራች አገራት ተሳታፊ ሆነዋል፡፡
Africa convene in Addis Ababa to talk bambooPDFPrintE-mail
Friday, 15 March 2013 18:12
African countries gathered in Addis Ababa to discuss the role of bamboo in pro-poor green development.

The gathering had discussions about sustainable development of bamboo, shared experiences and designed common strategies to expand the bamboo sector in Africa.

Ethiopia is reportedly working on bamboo resource management, and introduction of new bamboo technologies to help the sector make quantum leaps.

As bamboo is an important plant in preventing soil erosion, carbon sequestration, and as energy source for communities, developing the sector is essential to help African countries make the most of the benefits like China.

The meeting saw bamboo policy, consider value-chain-development plus sustainable markets. African countries like Nigeria, Kenya, Ghana, Tanzania, Uganda, Rwanda, Cameroon and others reported their bamboo sector development.

The gathering attracted over 100 senior officials and experts in the field hoping it would leave its marks on African bamboo resource management and production.

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር