ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ (መለስ ዋንጫ) የፊታችን እሁድ ይጀመራል፤ በ9 ሰኣት ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ጋር ይጫወታል

አዲስ አበባ ፣ የካቲት 12 ፣ 2005 (ኤፍ ቢ ሲ) ላለፉት ሁለት ወራት በአፍሪካ ዋንጫ ምክንያት ተቋርጦ የነበረው የኢትዮጵያ ፕሪሚየር ሊግ (መለስ ዋንጫ) የፊታችን እሁድ ይጀመራል።
በዚህም መሰረት እሁድ አዲስ አበባ ላይ ፥ የአምናው ሻምፒዮን ቅዱስ ጊዮርጊስ ከመከላከያ በ9 ሰአት  እንዲሁም ኢትዮጵያ ቡና ከ ደደቢት በ11 ሰአት የሚያደርጉት ጨዋታ ይጠበቃል።
ክልል ላይ በሚደረግ ጨዋታ በይርጋአለም ስቴዲየም ፥ በ9 ሰአት ሲዳማ ቡና ከ ኢትዮጵያ ንግድ ባንክ የሚጫወቱ ሲሆን ፥ አርባ ምንጭ ላይ ደግሞ አርባ ምንጭ ሃረር ቢራን በተመሳሳይ ሰአት ያስተናግዳል።
መብራት ሃይል ከሙገር ሲሚንቶ ፣ ኢትዮጵያ ውሃ ስፖርት ከኢትዮጵያ መድን የሚገናኙባቸው ጨዋታዎች የካቲት 21 የሚደረጉ ይሆናል።
http://www.fanabroadcasting.com/index.php?option=com_content&view=article&id=2446:2013-02-19-13-43-22&catid=102:slide

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር