በሲዳማ ዞን የ10 ሆስፒታሎች ግንባታ ተጀመረ



አዋሳ (ኢዜአ)፦ በጤናው መስክ የሚሌኒየሙን ግብ ለማሳካት በሲዳማ ዞን ከ210 ሚሊዮን ብር በሚበልጥ ወጪ የ10 ሆስፒታሎች ግንባታ መጀመሩን የዞኑ ጤና መምሪያ ገለጸ፡፡
የመምሪያው የልማት ዕቅድ ዝግጅትና ክትትል የሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ አክሊሉ ዮሐንስ ትናንት እንደገለጹት ፤ በጤናው መስክ በዞኑ የተቀናጀ ጥረት በመደረግ ላይ ነው፡፡
በ2004 በጀት ዓመት መጨረሻ ግንባታቸው የተጀመሩት እነዚህ ሆስፒታሎች በዞኑ በሚገኙ 10 ወረዳዎች መሆኑን ጠቁመው፤ በዞኑ የጤና አገልግሎት ተደራሽ ለማድረግ ባለፉት ዓመታት በተከናወኑ ተግባራት ከፍተኛ ውጤት መመዝገቡን ተናግረዋል። ከአምስት ዓመታት ወዲህ ሁሉም የባለድርሻ አካላት ባደረጉት የተቀናጀ ጥረት የጤና ጣቢያዎች ቁጥር ብቻ ከ16 ወደ 104 ማደጉን ገልጸዋል፡፡
ከግሎባል ፈንድ በተገኘ በጀት በመገንባት ላይ ያሉ ሆስፒታሎች ለአገልግሎት ሲበቁ በዞኑ ሁሉም ወረዳዎች የሚገኙ የህብረተሰብ ክፍሎች ከዚህ በፊት ረጅም መንገድ ተጉዘው የሚያገኙትን የጤና አገልግሎት በአቅራቢያቸው እንዲያገኙ ከማስቻሉም ሌላ የእናቶችና ህፃናት ሞት በመቀነስ የሚሌኒየሙን ግብ ለማሳካት ከፍተኛ አስተዋጽኦ እንዳለው ገልጸዋል፡፡
የሆስፒታሎቹ ግንባታ በተያዘው በጀት ዓመት መጨረሻ ሙሉ ለሙሉ በመጠናቀቅና የውስጥ ድርጅቱ ተሟልቶ ለአገልግሎት እንደሚበቁ የተናገሩት አቶ አክሊሉ፤ በዞኑ ከአንድ ሚሊዮን በላይ ህዝብ ተጠቃሚ ይሆናል፡፡
የጤና ሽፋኑም ቀደሞ ከነበረበት 86 በመቶ ወደ 97 በመቶ እንዲሁም የሆስፒታሎች ቁጥርም ከ5 ወደ 15 እንደሚያሳድግ ተናግረዋል፡፡
መከላከልን መሰረት ያደረገውን የጤና ፖሊሲ ተግባራዊ ለማድረግ በዞኑ በሚገኙ ሁሉም ቀበሌዎች በ482 ጤና ኬላዎች 1032 የጤና ኤክስቴንሽን ባለሙያዎች ተመድበው በጤናው መስክ የሚሌኒየሙን የልማት ግብ ለማሳካት ትኩረት ሰጥተው እየሰሩ መሆናቸውን አቶ አክሊሉ ተናግረዋል፡
http://www.ethpress.gov.et/ethpress/main/news.php?newsLocation=home&newsInstruction=headline&newsId=10067

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር