ደኢህዴን ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ያመራር ሚናውን ከምንግዜውም በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት መዘጋጀቱን አስታወቀ


አዲስ አበባ፤ ጥቅምት 2/2005 (ዋኢማ) - የደቡብ ኢትዮጵያ ህዝቦች ዴሞክራሲያዊ ንቅናቄ (ደኢህዴን) ማዕከላዊ ኮሚቴ ሀገራዊ ግቦችን ለማሳካት ያመራር ሚናውን ከምንግዜውም በላቀ ቁርጠኝነት ለመወጣት መዘጋጀቱን አስታወቀ፡፡

ማዕከላዊ ኮሚቴው የእድገትና የትራንስፎርሜሸን እቅዱን የሁለተኛ አመት አፈጻጸም ግምገማውን ለታላቁ መሪ አቶ መለስ ዜናዊ የህሊና ጸሎት በማድረግ ጀምሯል፡፡

የደኢህዴን ማዕካላዊ ኮሚቴ በመደበኛ ስብሰባው በታላቁ መሪ የተቀየሱት፣ መላውን ህዝብ ተሳታፊና ተጠቃሚ እያደረጉ የሚገኙት ፖሊሲዎችና ስትራቴጂዎችን በላቀ ቁርጠኝነት በሚፈፀሙበት ሁኔታ ላይ በዝርዝር ተወያይቷል፡፡ 

በዚህም የጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊን ህልፈት ተከትሎ ህዝቡ ከጫፍ ጫፍ ያሳየውን ቁጭት በተደራጀ መንገድ ለመምራት፣ በየደረጃው የሚገኙ ድርጅታዊ፣ መንግስታዊና ህዝባዊ መዋቅሮችን ተቋማዊ በማድረግ የህዳሴውን ጉዞ ለማፋጠን የሚያስችሉ የአፈጻጻም ስልቶችን በመቀየስ ተግባራዊ እንዲሆኑ ወስኗል፡፡

በገጠር ስራዎች በተለይም በአካባቢ ልማት አና ጥበቃ የተሻለ አፈጻጸም መመዝገቡን የገመገመው ማዕከላዊ ኮሚቴው በበልግ እና በመኸር የግል ማሳ ስራዎች ረገድም በአንዳንድ አካባቢዎች መልካም ውጤት መመዘግቡን አረጋግጧል፡፡

ምርታማነትን ለማሳደግ የቴክኖሎጂ ግብአቶችን በመጠቀም ረገድ የነበሩ ክፍተቶችንም ለይቷል፡፡

ኢሬቴድ እንደዘገበው ማዕከላዊ ኮሚቴው በከተሞች፣ በቤቶች ልማትና በመሰረተ ልማት የተሻሉ ተግባራት ቢከናወኑም በመልካም አስተዳደር ረገድ የሚስተዋሉ ጉደለቶችን ማረም እንደሚገባ ነው ያስገነዘበው፡፡

መስከረም 30/2005 የተጀመረው የማዕከላዊ ኮሚቴው መደበኛ ስብሰባ በ2005 በሁሉም መስኮች የነበሩ ጥንካሬዎችንና ጉድለቶችን በጥልቀት በመገምገም የ2005 እቅድ አቅጣጫዎችን ይወስናል ተብሎ እንደሚጠበቅ የደኢህዴን ጽ/ቤት የላከልን ዘገባ ያመለክታል፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር