በክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ የተጀመሩ የልማት ተግባራት ከግብ እንዲደርሱ ከመንግስት ጐን በመሆን የበኩላቸውን አስተዋፅኦ እንደሚወጡ የሲዳማ የሀገር ሽማግሌዎች ተናገሩ፡፡

 ከማህበራዊ መረብ የተገኘ ፎቶ


ሲዳማ ለጠቅላይ ሚኒስትር መለስ ዜናዊ ሲያለቅስ
በሲዳማ ህዝብ አንድ ጀግና ወይም የጐሳ መሪ ህይወት ሲያልፍ የሚደረገው ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት ለክቡር ጠቅላይ ሚኒስሩ ተደርጓል፡፡

ባህላዊ የለቅሶ ስርዓቱን የሚገልፀውና ዶሬ በመባል የሚታወቀው እንጨት ከተተከለ ከዘጠኝ ቀናት ቆይታ በኋላ እንዲወድቅ የተደረገ መሆኑን የተናገሩት የሀገር ሽማግሌዎቹ  ስርዓቱ ከተጠናቀቀ በኃላ  ሁሉም የብሔሩ ተወላጆች ወደ ልማት ማተኮር እንዳለባቸውም አሳስበዋል፡፡

ክቡር ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ መለስ ዜናዊ የሲዳማ ህዝብን ጨምሮ የመላው የኢትዮጵያ ህዝቦች መብት እንዲረጋገጥ ያደረጉ ታላቅ መሪ መሆናቸውን የገለፁት የሀገር ሽማግሌዎቹ ለእርሳቸው ያለንን አክብሮትና ፍቅር በልማቱ ጠንክረን በመሳተፍ እንገልፃለን ነው ያሉት፡፡

የሲዳማ ዞን ምክትል አስተዳዳሪ አቶ ደስታ ሌዳሞ በበኩላቸው የሲዳማ ህዝብን ከጭቆና እንዲወጣ ያደረጉት የአቶ መለስን ህልፈት አስመልክቶ የዞኑ ህዝብ በከፍተኛ ሁኔታ ሀዘኑን እየገለፀ የቆየ መሆኑን ተናግረዋል፡፡

እንደ ምክትል አስተዳዳሪው ህዝቡ ከመቼውም ጊዜ በላይ ለልማት ተነሳስቷል፡፡

ባህላዊ የለቅሶ ስርዓት የክቡር ጠቅላይ ሚኒስትሩ የቀብር ስነ ስርዓት ከተፈፀመ ከአንድ ቀን በኃላ መሆኑን ባልደረባችን በኃይሉ  ጌታቸው ዘግቧል፡፡
http://www.smm.gov.et/_Text/28NehTextN104.html

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር