የሲዳማ ብሔረሰብ ዘመን መለወጫ በዓል ተከበረ


ሀዋሳ ነሃሴ 9፣ 2004 (ኤፍ ቢ ሲ) በየዓመቱ የሚከበረው የሲዳማ ብሄረሰብ የዘመን መለወጫ በዓል /ፍቼ ጫምባላላ/ ትናንት በሀዋሳ ከተማ ተከብሯል።

በሲዳማ ባህል አዳራሽ በተካሄደው ክብረ በዓል ላይ በተለያዩ ምሁራን የተዘጋጁ ጥናታዊ ጽሁፎች ቀርበው ውይይት ተደርጎባቸዋል፡፡

የሲዳማ ብሔረሰብ  ቋንቋው ፣ ባህሉና ማንነቱ ተክብሮለት ከሌሎች የሀገሪቱ ብሔር ብሔርሰቦች ጋር ተቀናጅቶ ለአገሪቱ ብልፅግና እየሰራ መሆኑን የደቡብ ክልል ርእሰ መስተዳድር አቶ ሽፈራው ሽጉጤ በስነ ስርዓቱ ላይ ተናግረዋል ፡፡

የዘመን መለወጫ /ፍቼ  ጫምባላላ/ ባህላዊ የአከባበር ስነ ስርዓት በመንግስታቱ ድርጅት የሳይንስ ፣ የትምህርትና ባህል ድርጅት/ ዩኔስኮ / በዓለም ቅርስነት እንዲመዘገብ ጥረት በመደረግ ላይ መሆኑም ተመልክቷል፡፡

ከዘመን መለወጫው በዓል ጋር ተያይዞ የብሔረሰቡ 18ኛው የቋንቋና ባህል ስምፖዚየም መካሄዱን ነው ኢዜአ የዘገበው፡፡

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር