በተጠናቀቀው በጀት አመት ከቀረቡለት 1ሺህ 4 መቶ 11 የክስ መዛግብት ለ1ሺህ 3መቶ 90 ውሣኔ መስጠቱን በሲዳማ ዞን የአለታ ወንዶ ወረዳ ፍርድ ቤት ገለፀ፡፡
የወረዳው ፍርድ ቤት ፕሬዚዳንት አቶ ወንድሙ ቂጤሶ እንደገለተጹት በተጠናቀቀው በጀት አመት ጽህፈት ቤቱ ከቀረቡለት 1ሺህ 4 መቶ 11 የክስ መዛግብት ውስጥ 1 ሺ 3 መቶ 90 ዎቹ ውሣኔ መሰጠቱንና ቀሪዎቹ 21 መዛግብት ደግሞ ለቀጣዩ አመት ማስተላለፉን ተናግራል፡፡
ፍትህ ለህብረተሰቡ ተደራሽ ከማድረግ አንፃር የአመቱነ አፈፃፀም 98 ነጥብ 5 ከመቶ ማድረሱን ጠቅሰው፤ ለቀጣዩ አመት መቶ በመቶ ለማድረስ ጠንክረው እየሰሩ አንደሚገኙ አስረድተዋል፡፡
አርሶ አደሩ ከልማት ሥራው ሣይለይ ፍተህ በአከባቢው ያገኘ ዘንድ በተቋቋሙ 4 ማዕከላት ፍትህ በመስጠት አበረታች ውጤት የተመዘገበ መሆኑን የተናገሩት ፕሬዝዳንቱ በአዲስ አመት ወደ 6 ለማሣደግ ታቅዶ እየተሠራ እንደሆነ ጠቁመዋል፡፡
አርሶ አደሩ በህገ ወጥ ደላላዎች ይገጥመው የነበረውን የግንዛቤ እጥረት ለመቅረፍ ጧት ከችሎት በፊት በባለሙያዎች ትምህርት እየተሰጠ እንዳለ ገልፀዋል፡፡የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች ጽህፈት ቤት እንደገለጸው፡፡
Comments
Post a Comment