በሃዋሳ ከተማ ኣስተዳደር ውስጥ በርካታ የኣመራር የስራ መደቦች ላላፉት ሰባት እና ስምንት ወራት ክፍት ሆነው መቆየታቸው በከተማዋ ለሚካሄዱት ማህበራዊ እና ፖለቲካዊ ስራዎች ማነቆ መሆናቸውን ኣንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ገለጹ፤የኣመራር ስራ መደቦችቹ ለረዥም ጊዜያት ክፍት ሆነው መቆየታቸው መንግስት የከተማዋን ኣስተዳደር ከሲዳማ ለመንጠቅ ከሚያደርገው እንቅስቃሴ ጋር ሳይያያዝ ኣቀርም የሚል ጥርጣሬ ፈጥሯል



ስማቸው እንዲገለጽ ያልፈለጉ ነዋሪዎችና ሰራተኞች ለወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ እንደተናገሩት፤ የከተማው ኣስተዳደር ምክትል ከንትባና ንግድና ኢንዱስትሪ መምሪያ የስራ መደብን ጨምሮ በማዘጋጃ እና በስምንቱም ክፍለ ከተማዎች ቢያንስ ኣራት ኣራት የኣመራር የስራ መደቦች ላላፉት ሰባት እና ስምንት ወራት ሰው ኣልተመደበባቸውም።
የእነዚህ  መደቦች የእለትተእለት ስራዎች በተወከሉ ሰዎች በመከሄድ ላይ ያሉ ሲሆን፤ ሰው ካልተመደበባቸው መደቦች መካከል የከተማዋ የመንግስት ኮሚኒኬሽን፤ የማዘጋጃ ቤቱ ምክትል ኣስተዳዳር መደብ፤ ግቢይትና ህብረት ስራ መምሪያ እና የፍትህ መምሪያ ይገኙበታል።
በየስራ መደቦቹ ላይ ከዚህ በፊት ተመድበው ይሰሩ የነበሩ ግለሰቦች በተለያዩ ምክንያቶች ስራ የለቀቁ ወይም እንዲለቁ የተደረጉ መሆኑ ሲገለጽ፤ መደቦቹ ለረዥም ጊዚያት ክፍት መሆናቸው በከተማዋ ለሚካሄዱ የልማት ስራዎች ኣፈጻጸም ላይ ችግር መፈጠራቸው ተገልጿል።
እንደኣንዳንድ የከተማዋ ነዋሪዎች ኣስተያየት ከሆነ መንግስት የከተማዋን ኣስተዳደር ከሲዳማ እጅ ለማውጣት ከተማዋን ያስተዳድሩ በነበሩ የብሄሩ ተወላጆች ላይ የተለዩ ስነ ምግባራቸውን የሚያወርዱ ገጽታዎችን እየቀባ ያለ ምንም ተጨባጭ  ሲያስር ቆይቷል።
ይህ ኣይነቱ የመንግስት ድርጊት የሲዳማ ኣመራሮች የማስተዳደር ኣቅም የላቸውም፤ በክራይ ስብሳብነት የተዘፈቁ ናቸው የምል ግንዛቤ በከተማው ነዋሪ ዘንድ ለማስያዝና ኣመራሩን በሌላ ኣመራር ለመተካት የሚያደርጉትን እንቅስቃሴ በህዝቡ ዘንድ ተቀባይነት እንዲያገኝ ለማድረግ የታለመ  ሳይሆን ኣይቀርም ተብለዋል።
ለዚህም ማሳያነት በቁልፍ የኣመራር መደቦች ላይ ከነበሩ ግለሰቦች መካከል መሬት በመቸብቸብ እና በሌሎች ወንጀሎች ተወንጅለው ላለፉት ሰባት እና ስምንት ወራት ታስረው የከረሙ ግለሰቦች ምንም ኣልተገኘባቸውም ተብለው በመፈታት ላይ መሆ ናቸውን በኣብነት ኣንስተዋል።

Comments

Popular posts from this blog

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር