በሲዳማ ዞን የቦርቻ ወዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የወባ በሽታን በመከላከልና በመቆጣር ረገድ የአንድ ለእምስት ትስስር ስኬታማ ውጤት እያስገኘ መሆኑ አስታወቀ:


በሲዳማ ዞን የቦርቻ ወዳ ጤና ጥበቃ ጽህፈት ቤት የወባ በሽታን በመከላከልና በመቆጣር ረገድ የአንድ ለእምስት ትስስር ስኬታማ ውጤት እያስገኘ መሆኑ አስታወቀ::ጽህፈት ቤቱ ሰሞኑን ሜዳ ላይ ከመፀዳዳት ነፃ የወጡ ቀበሌያትን ባስመረቀበት ወቅት የጽህፈት ቤቱ ምክትል ኃላፊ አቶ ዱባለ ባራሳ እንዳስታወቁት በወረዳው በሚገኙ 42 ቀበሌያት በአንድ ለአምስት ትስስር በተደረገው ጥረት 16ቱን ጤና ፖኬጅ ተግባራዊ በማድረግ አበረታች ውጤት ማየት ተችሏል::
ለውጤቱ መገኘትም የጤና ልማት ሠራዊት በአንድ ለአምስት ትስስር መሠረታዊ የግል ንጽህና፣ የአካባቢ ጤና አጠባበቅ ፣ የቤተሰብ ጤና አገልግሎት እንዲሁም የወባ በሽታን በመከላከልና በመቆጣጠር ቀዳሚ ተዋናይ መሆናቸውን ተናግረዋል::
በተይም የጤና ኤክስቴንሽን ሠራተኞች ፣በጎ መልክተኞችና የጤና ባለሙያዎች ድርሻ የጎላ መሆኑን ኃላፊው ገልፀው በጥረቱም 9 ሺህ ሞዴል ቤተሰብ መፍጠር መቻሉንም ጠቁመዋል::
የዞኑ በሽታ መከላከልና ጤና ማጎልበት ሥራ ሂደት አስተባባሪ አቶ ኢማላ ላማቻ በበኩላቸው ህብረተሰቡ ግንባር ቀደም ተዋናይና በማህበረሰብ ውይይት ንቁ ተሳትፉ በመሆን ጤናውን ማጐልበት እንደሚገባው የዞኑ የመንግስት ኮሚኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ እንደዘገበው::

Comments

Popular posts from this blog

ፓርቲው ምርጫ ቦርድ ከተፅዕኖ ነፃ ሳይሆን የምርጫ ጊዜ ሰሌዳ ማውጣቱን ተቃወመ

የሐዋሳ ሐይቅ ትሩፋት

በሲዳማ ክልል የትግራይ ተወላጆች ምክክር