POWr Social Media Icons

Monday, January 5, 2015ሰሞኑን ከኣስተዳደሩ የወጣው መረጃ እንደምያመለክተው፤ በከተማዋ ያለውን የፈሳሽ ማስወገጃ መስመሮች መረብ ይዞታን ለማስገምገም እና ኣዲስ የፍሳሽ ማስወገጃ መረብ ማስተር ፕላን ድዛይን ለማስጠናት በዝግጅት ላይ ነው።

የሃዋሳ ከተማ ነዋሪዎች ቁጥር ከጥቂት ኣመታት ወዲህ በከፍተኛ ፍጥነት በመጨመር ላይ ከመሆኗ ጋር ተያይዞ በከተማዋ ያለውን የፍሳሽ ማስወገጃ መስመሮች ኣቅም ማሳደግ ኣስፈላግ መሆኑ ታውቋል።

የሃዋሳ ከተማ በኣገሪቱ ካሉት ከተሞች መካከል በደረቅ እና ፈሳሽ ቆሻሻ ኣወጋገድ ኣንጻር መልካም ተሞክሮ ያላት ብትሆንም በተለይ በክረምት ወቅት በኣንዳንድ የከተማዋ ቀበሌያት የተዘረጉት የፍሳሽ ማስወጋጃ መስመሮች በቆሻሻ በመዘጋታቸው የተነሳ የጎርፍ መጥለቅለቅ ኣደጋዎች እንደምከሰቱ ይታወሳል።0 comments :