Posts

Sidama and Ethiopian

Image
Sidama and Ethiopian :  the emergence of the Mekane Yesus Church in Sidama Abstract (en)  : The present work belongs to local African church history and international mission history.The author shows why and how the Sidama people in south Ethiopia became part of theevangelical movement. During the last hundred years this group has experienced a lot ofchanges, incorporated in the greater Ethiopia, being influenced by the internationalmissionary movement, occupied by an European power and becoming a part of themodernising movement. As a result of all the changes and impulses the people faced, the Sidama to a great extendturned away from their traditional worldview and practices including their religion andaccepted the Christian Evangelical faith. The origin and the development that led to the foundation of the Ethiopian EvangelicalChurch Mekane Yesus in Sidama are described, as part of the local church history. Theauthor wants to underline how political, social and cultu

ክትባት ለህጻናት እና እናቶች በሲዳማ

Image
ሀዋሳ መጋቢት 10/2006 በሲዳማ ዞን የእናቶችና ህፃናት ጤና አገልግሎትን ተደራሽ በማድረግ የምዕተ ዓመቱን የጤና ልማት ግብ ለማሳካት በትኩረት እየሰራ መሆኑን የዞኑ ጤና መምሪያ አስታወቀ፡፡ በዞኑ በላፉት ስድስት ወራት ከ318 ሺህ ለሚበልጡ ህፃናት የተለያየ የበሽታ መከላከያ ክትባት ሲሰጥ ከ274 ሺህ የሚበልጡ እናቶች የቤተሰብ ምጣኔ አገልግሎት ተጠቃሚ ሆነዋል፡፡ ለልጆቻቸው የሚሰጠው ክትባት ህፃናት ከበሽታ በመጠበቅ ጤናቸው የተሻለ እንዲሆን እንደረዳቸው እናቶች ገልፀዋል፡፡ በመምሪያው የጤና ልማት እቅድ ዝግጅት፣ክትትልና ግብረ መልስ የስራ ሂደት ኦፊሰር አቶ አበበ በካዬ እንደገለጹት የእናቶችና ህፃናትን የጤና አገልግሎት ተደራሽ በማድረግ የምዕተዓመቱን የጤና ልማት ግብ ለማሳካት በትኩረት እየሰራ ነው፡፡ ባለፉት ስድስት ወራት ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ሁሉም ህፃናት ክትባት እንዲወስዱ የጤና ኤክስቴንሽን ሰራተኞች ከፍተኛ ጥረት ማድረጋቸውን ተናግረዋል፡፡ በዚህም ባለፉት ስድስት ወራት በ19 ወረዳና ሁለት የከተማ አስተዳደሮች 318 ሺህ 715 ዕድሜያቸው ከአንድ ዓመት በታች የሆኑ ህፃናት የፖሊዮ፣ የቲቪ፣ የኩፍኝና የሳንባ ምች በሽታ መከላከያ ክትባት መሰጠቱን ገልፀዋል፡፡ ለህፃናት ሞት ምክንያት የሆነው የሳምባ ምች መከላከያ ክትባት በመደበኛ የክትባት አገልግሎት ውስጥ በማካተት 107 ሺህ 751 ህፃናት መከተባቸውን አስታውቀዋል፡፡ በወሊድ እድሜ ክልል ለ274ሺህ ሴቶች ይርጋዓለም ሆስፒታልን ጨምሮ ከ650 በሚበልጡ ጤና ጣቢያዎችና ጤና ኬላዎች የስነ ተዋልዶና ቤተሰብ ምጣኔ የአገልግሎት ተጠቃሚ መሆናቸውን ተናግረዋል፡፡ ወይዘሮ እቴነሽ ጋላናና ወይዘሮ አልማዝ ወርቁ ለህፃናት በሚሰጠው የበሽታ መከላከያ ክትባት ህፃናት ከበሽታ

በሐዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ከመልካም ተሞክሮ ባሻገር ጥቃቅን ችግሮችም አይናቁ

Image
ወደ ሐዋሳ ፖሊቴክኒክ ኮሌጅ ግቢ ስዘልቅ ሞቃታማ አየሯን የምትረጨውን ፀሐይ ተቋቁመው በየትምህርት መስካቸው ተግባራዊ ልምምድ የሚያደርጉ ተማሪዎች እዚህም እዚያም ሲታትሩ ታይተውኛል። በስተቀኝ በመንገድ ሥራ የሚሠለጥኑ ተማሪዎች አፈሩን እየደለደሉና እየጠቀጠቁ ጥራት ያለው መንገድ እንዴት መሥራት እንደሚቻል ተግባራዊ ልምምድ ሲያደርጉ፤ በስተግራ ደግሞ በኮብል ስቶን ሥራ እና በቅየሳ የሚሠለጥኑ ተማሪዎች በየሙያቸው የሚያስፈልጓቸውን ቁሶች ታጥቀው ሙሉ ትኩረታቸውን በልምምዱ ላይ አድርገው ይታያሉ። ከተማሪዎቹ መካከል ወደ አንዱ ጠጋ ብዬ  « ሥልጠና እንዴት ነው ?»  የሚለውን የጋዜጠኛ ጥያቄዬን አስቀደምኩ። ተማሪው አራርሶ ወልዴ ይባላል። የመጣው ከሀዲያ ዞን ሾኔ ከሚባል አካባቢ ነው። የሦስተኛ ዓመት የመንገድ ሲቪል ዎርከ ሠልጣኝ ሲሆን፤ በኮሌጁ በነበረው ቆይታ በክፍተትና በመልካም ተሞክሮነት የሚጠቀሱ ጉዳዮችን እንዲህ በማለት ይገልጽልኝ ጀመር  «  ባለፉት ዓመታት የመምህራን እጥረት ነበር። በሳምንት አምስት ቀን መማር ቢኖርብንም አንዳንድ ቀን መምህራን እየጠፉ ትምህርት የማናገኝበት ቀን ነበር። ይሁን እንጂ ያሉት መምህራን ጊዜያቸውን በመሰዋት ትምህርት እየሰጡን ክፍተቱን ለመሙላት ይጥሩ ነበር። አንዳንድ ለተማሪ ፍቅር የማይሰጡ መምህራንም ነበሩ። ተማሪ ሊያጠፋ ይችላል መምህር መቻል፣ መምከርና ትምህርቱን በአግባቡ መስጠት መቻል አለበት።  » ሠልጣኝ አራርሶ በቴክኒክና ሙያ ዘርፍ የሚሰጡ ሥልጠናዎች ሰባ ከመቶ ተግባር ተኮር እንዲሆኑ በተቀመጠው አቅጣጫ መሰረት የሚሰጠው ሥልጠና በኮሌጃቸው በአግባቡ እየተተገበረ መሆኑን ይናገራል። ሰላሳ በመቶ የሚሆነውን ሥልጠና በክፍል ከተማሩ በኋላ ቀሪውን በተግባር ይሰለጥናሉ። በእነርሱ የሥልጠና ዘርፍ የተሟሉ የተግባር ት

ሲኣን ከኣባላቱ እና ከደጋፊዎቹ ጋር ልመክር ነው

Image
በመጪው መጋቢት 20 ላይ በምካሄደው ህዝባዊ ጉባኤ፤ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ብሔራዊ የፖለቲካ ፓርቲ ከሆነው ከመድረክ ጋር ግንባር መፍጠር ያስፈለገበትን ምክንያት ለማብራራት እና ግንባሩን ወደፊት ለማጠናከር በሚቻልበት ሁኔታ ላይ ከሰፊው የሲዳማ ህዝብ ጋር ይመክራል ተብሎ ይጠበቃል። ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና እንደዘጋበው ለኣንድ ቀን በሚውለው በዚህ ህዝባዊ ጉባኤ ላይ የሲዳማ ኣባቶች በባህሉ መሰረት መርቀው የሚከፍቱ ሲሆን፤ በሲዳማኣፎ ፤ በኣማርኛ እና በኦሮሚፋ ቋንቋዎች እንደየኣስፈላጊነቱ ለመጠቀም ፕሮግራም መያዙ ታውቋል። በተጨማሪም ጉባኤ በተለያዩ የመዝናኛ ዝግጅቶች ይታጀባል። ከዚህም ባሻገር በሃዋሳ በሌሎች የሲዳማ ከተሞች በሚገኙ ዋና ዋና መገናኛ ቦታዎች ላይ ስለ ጉባኤው ዓላማ እና ዝግጅት የሚያትቱ ፖስተሮችን እና ማስታወቂያዎች እንደምሰቀሉ ተገልጿል። በጉባኤው ላይ በድርጅቱ ኣከፋፈል መሰረት በሰባቱ የሲዳማ ክልል ዞኖች ውስጥ ከምገኙ 21 ወረዳዎች እና 502 ቀበሌያት የተጋበዙ የድርጅቱ ኣባላት እና ደጋፊዎች ብሎም ሌሎች ተጋባዥ እንግዶች እንደምገኙ ይጠበቃል። በተጨማሪም ከሲዳማ ህዝብ ጋር በባህልና በሃይማኖት ከተሳሰሩት እና ተመሳሳይ የፖለቲካ ኣካሄድ ካለቸው ብሄሮች መካከል የኦሮሞ ብሄረሰብ ተወካዮች ተሳታፊ እንደምሆኑ ታውቋል። ባለፈው ሳምንት በመድረክ ኣዘጋጅነት በሻሾሚኔ ከተማ በተካሄደው ህዝባዊ ጉባኤ ላይ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ ( ሲኣን ) በ 15 ኣባላቱ የተወከለ ሲሆን፤ ኣባለቱ በሲዳማ ባህላዊ ኣልባሳት ተሽቀርቅረው ወደ ጉባኤው ኣዳራሽ በገቡበት ወቅት የጉባኤው ተሳታፊዎች ከመቀመጫቸው በመነሳት በጭብጨባ ታላቅ ኣቀባበል ማድረጋቸው ይታወሳል። በወቅቱ የሲዳማ እና የኦሮሞ ሽማግሌዎች የተለያዩ ሰጦታዎች

የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ (ሲኣን) በሃዋሳ ከተማ ታላቅ ህዝባዊ ጉባኤ መጥራቱ ተሰማ

Image
ንቅናቄው በቅርቡ ከተቀላቀለው ብሔራዊ ድርጅት ከመድረክ ጋር በጋራ በመሆን በመጪው መጋቢት 20 ታላቅ ህዝባዊ ሰብሰባ በሃዋሳ ከተማ በሲዳማ ባህል ኣደራሽ ኣዘጋጅቷል። በተመሳሳይ ዜና ባለፈው ቅዳሜ በመድረክ ኣዘጋጅነት በተካሄደው ህዝባዊ ሰብሰባ ላይ የሲዳማ ኣርነት ንቅናቄ በ 15 ተወካዮች የተሳተፈ ሲሆን፤ ተወካዮቹ በሲዳማ የባህል ኣልባሳት ኣምረው ዘንጠው ወደ ጉባኤው ኣዳራሽ በገቡበት ወቅት ቤቱ በታላቅ ጭብጭባ ደማቅ ኣቀባበል እንዳደረገላቸው ሪፖርተራችን ጥቻ ወራና ከሃዋሳ ዘግቧል።

Africa Looks To Colombia For Tips On Sustainable Coffee

Image
Producers from Rwanda, Burundi and Ethiopia have visited the Colombian estates of producers to discover the social, environmental and aesthetic benefits of growing shade coffee. BOGOTA  — Which is better,  Colombian  or  African coffee ? Whatever your preference, both regions are major world producers and have begun to work together to produce coffee that offers much more than enticing flavors and aroma. This idea exchange began when producers in  Rwanda  and  Burundi  explored how they could focus on quality but also on environmental care and long-term sustainability. They wanted to generate additional revenues via tourism and improve the welfare of coffee workers at the same time.  “The two countries begin to identify these elements as important practices for sustainable landscape management, with numerous environmental and social benefits,” says Paola Agostini, the World Bank’s Africa Regional Coordinator. So it made sense that they wanted to visit South America, where

የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፤ በሲዳማ ቡና ገበያ ላይ ተጽኖ ይኖረው ይሁን?

Image
ዘመናዊ የግብይት ሥርዓት ለመዘርጋት ምሳሌ ይሆናል የተባለውን የኢትዮጵያ ምርት ገበያ በዋና ሥራ አስፈጻሚነት ሲመሩ የቆዩትን ዶ/ር እሌኒ ገብረ መድኅንን ተክተው ሲሠሩ የቆዩት አቶ አንተነህ አሰፋ ከኃላፊነታቸው ለቀቁ፡፡ ምንጮች እንደጠቆሙት አቶ አንተነህ ከኃላፊነት የለቀቁት አሜሪካ ሆነው ባመለከቱት የሥራ መልቀቂያ ደብዳቤ ሲሆን፣ የምርት ገበያው ቦርድ ጥያቄያቸውን ተቀብሎ አፅድቆታል፡፡  በቀድሞው ምክትል ጠቅላይ ሚኒስትር አቶ አዲሱ ለገሰ ሊቀመንበርነት የሚመራው የኢትዮጵያ ምርት ገበያ ቦርድ የሥራ መልቀቂያውን ተቀብሎ ውሳኔ የሰጠው፣ ሐሙስ መጋቢት 4 ቀን 2006 ዓ.ም. መሆኑን የተገኘው መረጃ ያስረዳል፡፡   አቶ አንተነህ ሥራቸውን ለመልቀቅ ውሳኔ ላይ ያደረሳቸው የጤና ችግር መሆኑን ምንጮች ጠቁመዋል፡፡ በልብ ሕመም ምክንያት በአገር ውስጥ በሕክምና ላይ እንደነበሩና አነስተኛ ቀዶ ጥገና ተደርጐላቸው እንደነበር ታውቋል፡፡ በዚህ ምክንያት ለከፍተኛ ሕክምና አሜሪካ የሄዱት አቶ አንተነህ፣ ሕክምናውን እዚያው በቅርብ እንዲከታተሉ በመወሰኑ ሥራቸውን ለመልቀቅ እንደተገደዱ እየተነገረ ነው፡፡ ወደ አሜሪካም ሲጓዙ ቤተሰቦቻቸውን ይዘው እንደሆነም ለጉዳዩ ቅርበት ያላቸው ለሪፖርተር አስረድተዋል፡፡  በሥራ ገበታቸው ላይ ሳይገኙ ከሁለት ወራት በላይ የቆዩት አቶ አንተነህ፣ ይመለሳሉ ተብሎ በሚጠበቅበት ጊዜ የሥራ መልቀቂያ መላካቸው ያልተጠበቀ ነው ተብሏል፡፡  አቶ አንተነህ ዋና ሥራ አስፈጻሚ በመሆን ሙሉ የምርት ገበያውን ኃላፊነት ተረክበው መምራት ከመጀመራቸው ቀደም ብሎ፣ ከነሐሴ 24 ቀን 2004 ዓ.ም. እስከ መስከረም 20 ቀን 2005 ዓ.ም. ድረስ ዕጩ ዋና ሥራ አስፈጻሚ ተብለው ከዶ/ር እሌኒ ጋር በጋራ ሲሠሩ እንደነበር ይታወሳል፡፡ መስከረም

የኢትዮጵያ መንግስት እና የብድር ኣባዜው

Ethiopia’s Growing Debt Appetite and Eurobond The Ethiopian government has significantly increased its borrowing in recent years. Debt-to- GDP ratio has reached an all time high of 35 percent and continues to grow. Lately, the country has also been shifting slowly from concessional loans to market based loans. The Ethiopian Ministry of Finance & Economic Development (MOFED) data shows that, since the beginning of the 2008 world financial crisis through 2013, Ethiopia’s external debt has grown by 156 percent from USD 4.35 billion to USD 11.17 billion. The total public outstanding debt was at USD 16.11 billion, excluding domestic lending to State Owned Enterprises. During the same period, IMF was estimating Ethiopia’s GDP at Birr 877.5 Billion (USD 46 billion). At the moment, Ethiopia has a government guaranteed soft loan program with a rate below 2 percent, a grace period of up to 10 years, and longer duration loans with multilateral development banks, The World Bank loans m

በሃዋሳ ከተማ ሀሰተኛ የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ኣቅራቢዎች ቁጥር ለምን ጨመረ?

Image
Photo@http://elmartyhawassa.blogspot.com/2012/06/home.html በሃዋሳ ከተማ እና በሌሎች የደቡብ ኣከባቢዎች የሙያ ብቃት ማረጋገጫ ማስረጃ ኣጭበርባሪዎች መበራከታቸው ተሰማ፤ ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል በግማሽ ኣመት ውስጥ የሙያ ማረጋገጫ ፈተና ከወሰዱት 19 ሺ 862 ሙያተኞች መካከል ግማሾቹ ወድቀዋል። ከቅርብ ጊዜ ወዲህ በተለይ ከቴክኒክ እና ሙያ ተቋማት ስልጥነው የምወጡ ሙያቸኞች የሙያ ማረጋገጫ ፈተና እንድወስዱ መገደዳቸውን ተከትሎ የሙያ ማረጋገጫውን ፈተና ውጤት የሚያጭበረብሩ ሙያተኞች ቁጥር መበራከቱ እየተነገረ ነው። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ሰሞኑን ከሃዋሳ እንደዘጋበው፤ ሲዳማን ጨምሮ በደቡብ ክልል ባለፉት ስድስት ወራት 19 ሺ 862 ሙያተኞች የብቃት ማረጋገጫ ፈተና የወሰዱ ሲሆኑ ፈተናውን ያለፉት ግማሾቹ ብቻ ናቸው ። የወኢኔት ሪፖርተሮች ያናገሯቸው እና ስማቸው እንድጠቀስ ያልፈለጉ በደቡብ ክልል የሙያ ብቃት ምዘናና ማረጋገጫ ማዕከል የምሰጠውን ፈተና የወሰዱ ተፈታኞች እንደተናገሩ፤ በማዕከሉ የምሰጠው የሙያ ብቃት ምዘና ከባድ መሆኑን በየተቋማቱ ያለውን የሙያ ትምህርት ጥራት ከግምት ውስጥ ያላስገባ ነው። እንደኣስተያየት ስጪዎቱ ከሆነ፤ መንግስት በምዘና ፈተና ላይ ብቻ ትኩረት ከመሰጠት ወደየሙያ ተቋማቱ የምገቡ ሰልጣኞች በኣግባቡ የምገባውን ትምህርት እና የሙያ ክሎት እንድይዙ የሚያደርግ የትምህርት ስርዓት መዘርጋት ኣለበት ብለዋል። ኣክለውም በየየሙያ ተቋማቱ ያለው የትምህርት ስርዓት ጥራት የሌለው መሆኑን ገልጸው፤ የሙያ ማረጋገጫ ከምወስዱት ከግማሽ በላይ የምሆኑት ምዘናውን ማለፈ ኣለመቻል ለትምህርቱ ጥራት ማነስ ማሳያ ነው ብለዋል ። እንደ ሪፖርተሮቻችን ዘገባ ከሆ

Sidama ...land of untouched culture!

Image
ፎቶ http://www.flickr.com/search/?q=sidama

በኣለማችን ላይ “ሲዳማ” የምትለውን ቃል በኢንተርኔት ላይ ሰርች የሚያደርጉ ሰዎች ቁጥር ከጊዜ ወደ ጊዜ እያደገ መምጣቱን የጎግል መረጃ ኣመለከተ።

Image
ጎግል በኣለም ደረጃ “ሲዳማ” በምል ቃል ስለ ሲዳማ ጎግል የምያደርጉ ሰዎች ቁጥር ካለፉት ኣስር ኣመታት ጀምሮ እያደገ መምጣቱን የገለጸ ሲሆን፤ በተለይ እንደ ፈረንጆቹ ዘመን ኣቆጣጠር በ 2013 ከፍተኛ ቁጥር ያለው የኢንተርኔት ተጠቃሚ ሲዳማን መፈለጉ ታውቋል። እንደጎግል መረጃ በተለይ እኣኣ ከ 2007 በፊት ሲዳማ ብዙም ጎግል የተደረገ ቃል ባይሆንም፤ በ 2008 ኣጋማሽ ላይ በርካታ ሰዎች “ሲዳማ”ን ጎግል ማድረጋቸው ተመልክቷል። ቀጥሎም በ 2009 መጀመረያ ላይ የሲዳማ ጎልጋዮች ቁጥር የወረደ ሲሆን በተመሳሳይ ኣመት መጨረሻ ላይ እንደገና ኣድጓል። ከ 2010 ጀምሮ የጎልጋዮች ቁጥር ኣንዴ ስያድግ ሌላ ግዜ ሲወርድ ቆይቶ በበላፈው ኣመት መጀመሪያ ላይ በታሪኩ ታይቶ በማይታወቅ መልኩ መጨመሩ ታውቋል። ነገር ግን ከ 2013 ኣጋማሽ ጀምሮ ይቁጥር በመውረድ ላይ ይገኛል። ጎግል እንዳመለከተው “ሲዳማ” የምትለውን ቃል የምጎለጉሉ ሰዎች ትራፊክ በኣብዛኛው የምፈጠረው ከሰሜን ኣሜሪካ ሲሆን፤ ኢትዮጵያ እና ሰሜን ኣውሮፓ ኣገራት እንድሁ የትራፊክ ምንጮች ናቸው። የሲዳማ ጎልጋዮች ቁጥር መጨመር እና መውረድ ከሲዳማ ዞን የፖለቲካ ሁኔታ ጋር የተያያዘ መሆኑን የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ትንተና ያመለከተ ሲሆን፤ ለዚህም ማሳያ በሲዳማ ዞን ውስጥ የፖለቲካ ትኩሳት የነበረባቸው ኣመታት ማለትም በ 2006 እና 2013 የተፈጠረውን ትራፊክ ማየት ይቻላል።

የሲዳማ ዘመን መለወጫ /ፍቼ/ በአል አከባበር

Image
ከይረጋዓለም ከተማ አስተዳደር ጋር በመተባበር  ፍቼ በዓል በሲዳማ ፎቶ ከሲዳማ ባ/ቱ/መ/ኮ/መምሪያ “ፍቼ” በሲዳማ ባህል ከትውልድ ትውልድ ሲተላለፍ የቆየ የዘመን መለወጫ በአል ነው፡፡ በአሉ ከሁለት ሳምንት ላላነሰ ጊዜ በድምቀት የሚከበር ሲሆን አከባበሩም ቅደም ተከተላዊ ሂደትና በደረጃ እየሰፋ የሚሄድ የጋራ የአከባበር አድምታ ያለው ነው፡፡ ስለሆነም ፍቼ በቤተሰብ ወይም በጎረቤት ደረጃ ተሰባስቦ በማክበር የሚያበቃ ሳይሆን ከዚህም በሰፋ መልኩ በባህላዊ አደባባይ /ጉዱማሌ/ በጋራ በድምቀት የማክበር ሂደትን ያካትታል፡፡ ለአከባበሩ እያንዳንዱ ቤተሰብ በቅድሚያ እንደ አቅሙ ቅድመ ዝግጅት ያደርጋል፡፡ ከዚሁ አንጻር የቤቱ እመቤት ለበአሉ ቅቤ ታጠራቅማለች ወተት በታጠነ ማለፊያ “ቁሹና” /የወተት እቃ/ ታከማቻለች የእንሰት ውጤት የሆነውን ቆጮ ለበአሉ በሚሆን መጠንና ጥራት ከወዲሁ ታሰናዳለች፡፡ አባወራው በፍቼ ማግስት /በጫምበላላ/ እለት ለከብቱ የሚያበላውን ቦሌ ያዘጋጃል፡፡ ልጃገረዶች ለበአሉ መዋቢያ ለእግሮቻቸውና ለእጆቻቸው ጣቶች ቀለበት፣ ለፀጉራቸው መስሪያ “ሄቆ” /የተለያዩ ቀለማት ያሉት የቱባ ክር/፣ ጨሌ፣ ለአንገታቸው ቡሪቻና ዶቃ የጌጥ አይነት ለጸጉራቸው ማሸሚያ ግንባራቸው ላይ የሚያስሩትን በእራፊ ጨርቅ ላይ ደርድረው የሚሰፉትን ኢልካ /አዝራር/ ወዘተ የመሳሰለውን ያስገዛሉ እግራቸውና እጃቸው ላይ የሚቀቡትን እንሶስላ ያዘጋጃሉ፡፡   ፍቼ/ Fichchaa / የሲዳማ ሸንጎ ፎቶ ከሲዳማ ባ/ቱ/መ/ኮ/መምሪያ የፍቼ ዕለተ በዕለተ ቃዋዶ በአሉ መከበር የሚጀምረው ከአመሻሽ ጀምሮ ነው፡፡ ለዚህም በቅቤ የራሰ “ቡሪሳሜ” ከቆጮ የተሰራ ባህላዊ ምግብ “በሻፌታ” /ከሸክላ በተሰራ ባህላዊ ገበታ/ ቀርቦ በወተት በጋራ የመመገብ ሥርዓት የሚካ

ጥቂት ስለ ሲዳማ ቡና የእግር ኳስ ቡድን

Image
PROFILE ሲዳማ ቡና  ሙሉ ስም ፡  ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ  ምስረታ ፡  1999 ስታዲየም ፡   ይርጋለም ስታዲየም  ሀዋሳ ስታዲየም የክለቡ የወቅቱ አሰልጣኝ ፡  ታረቀኝ አሰፋ   ዳኜ ክለቡ ያገኛቸው ክብሮች ፡  የኢትዮጵያ ብሔራዊ ሊግ ሻምፒዮን 2001 ሲዳማ ቡና በአሁኑ ወቅት በኢትዮጵያ ፕርሚየር ሊግ እየተሳተፈ ያለ ክለብ ነው፡፡ ክለቡ ከተመሰረተ ጥቂት አመታት ብቻ ቢቆጠሩም በብሔራዊ ሊግ ሻምፒዮን ሆኗል፡፡ በፕሚየርሊጉም ጥሩ ተፎካካሪ እየሆነ ይገኛል፡፡ ምስረታ  ሲዳማ ቡና ስፖርት ክለብ የተመሰረተው በ 1999 ዓ/ም ነበር በደቡብ ክልል ክለቦች ሻምፒዮና ላይ ሲዳማ ዞንን በመወከል ሥስት ክለቦች ይሳተፋሉ ከእነዚህ ውስጥ አንዱ ዳራ ከነማ ነበር፡፡ ዳራ በውድድሩ ለፍፃሜ በመድረስ ውጤታማ ይሆናል፡፡ ይህም ክልሉን በመወከል ሀዋሳ ላይ ወደተካሄደው የኢትዮጵያ የክልል ክለቦች ሻምፒዮና ከተሳተፉ አራት ቡድኖች አንዱ ለመሆን አበቃው፡፡ በዚህ ውድድር ቀዳሚዎቹን አራት ደረጃዎች የሚይዙ ቡድኖች ወደ ብሔራዊ ሊግ ሲያልፉ ዳራም ሦስተኛ ደረጃን አግኝቶ ስለነበር ብሔራዊ ሊጉን ተቀላቀለ፡፡ እናም ዳራ ከተማን ብቻ ይወክል የነበረው ክለብ መላውን የሲዳማ ዞንን እንዲወከል በማሰብ ሲዳማ የሚለውን ስያሜ አገኘ፡፡ ሲዳማ ቡና በብሔራዊ ሊግ ሲዳማ ቡና ሁለት አመት በብሔራዊ ሊግ አሳልፏል፡፡ በመጀመሪያው አመት ቆይታው በ 2000 አራተኛ ደረጃን ይዞ ነው ያጠናቀቀው፡፡ በሁለተኛው አመት 2001 ውድድሩ በሁለት ምድብ ተከፍሎ ሲካሔድ በምድብ ሁለት የነበረው ሲዳማ በመጨረሻው ጨዋታ ከአየር ሀይል ጋር ያለ ግብ በመለያየት ከምድቡ ከሜታ አቦ ቢራ ቀጥሎ ሁለተኛ ደረጃን አግኝቷል፡፡ በዚህ ጨዋታ ቢሸነፍ ኖሮ ይህን ደረጃ አ