Posts

ከቱሪስት ከተማነት እስከ ታላላቅ የስፖርት ውድድሮች መናኸሪያነት_ሀዋሳ

Image
ከሃምሳ ዓመት በላይ ያስቆጠረችው የደቡብ ክልል መዲና ሐዋሳ ከኢትዮጵያ ከተሞች በቁንጅናዋ፣ በዕቅድ ከመከተሟም ጋር ተዛምዶ ለብዙ ነገር ትመረጣለች፡፡ ከቱሪስት ከተማነት እስከ ታላላቅ የስፖርት ውድድሮች መናኸሪያነት ትታጫለች፡፡  አትሌት ኃይሌ ገብረ ሥላሴ በሐዋሳ ስሙን መትከል የፈለገው በቢዝነስ ሥራ ብቻ አይደለም፡፡ በታላቁ ሩጫ ዓመት ጠብቆ የሚጐበኛትን የደቡብ መናገሻ፣ አሁን ደግሞ ለአገሪቱ የመጀመሪያ የሆነውን ማራቶን መሽቀዳደሚያ አውራና ተመራጭ አድርጓታል፡፡  ኃይሌ በሐዋሳ ያልተለመደውንና በስሙ የተሰየመውን የማራቶን ውድድር በከፍተኛ የገንዘብ ሽልማት አንበሽብሾታል፡፡ በሁለቱም ጾታ አሸናፊዎቹ እያንዳንዳቸው የ100 ሺሕ ብር ሽልማት ተበርክቶላቸዋል፡፡  የመጀመሪያው ‹‹ኃይሌ ማራቶን›› ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በደቡቧ መናገሻ ሐዋሳ እንደሚደረግ ይፋ በሆነ በጥቂት ወራት ከ16 አገሮች ከ200 በላይ ተሳታፊዎች በውድድሩ ለመሳተፍ ቅድመ ምዝገባ ማከናወናቸውን የገለፀው ዝግጅት ክፍሉ፣ በሚቀጥለው ዓመት ከተወዳዳሪ ቁጥር ጀምሮ የተሻለና ዓለም አቀፍ ደረጃውን የጠበቀ ለማድረግ አበረታች ተሞክሮ ተገኝቷል ብሏል፡፡  በአገሪቱ ለታላላቅ አትሌቶች መገናኛ እንደሆነ የሚነገርለት ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ፣ በ10 ሺሕ ተሳታፊዎች ጀምሮ በአሁኑ ወቅት በተመሳሳይ የሩጫ ውድድሮች ከዓለም ምርጥ አሥሩ አንዱ ለመሆን በቅቷል፡፡ ዘንድሮም 37 ሺሕ ተሳታፊዎች ለማወዳደር ዝግጅቱን አጠናቆ እንደሚገኝ መገለጹ ይታወሳል፡፡ ውድድሩ ከአዲስ አበባ አልፎ በመላ አገሪቱ የተለያዩ ከተሞች ተወዳጅና ተናፋቂ እስከመሆን ደርሷል፡፡  42 ኪሎ ሜትር 195 ሜትር የሚሸፍነው ማራቶን በአውሮፓና በሌሎች ታላላቅ አገሮች ካልሆነ እንዲህ እንደ አሁኑ በኢትዮጵያ ይደረጋል

ኣንድ የሲዳማ ወጣት ከድህነት ተላቀቀ፤በዕድል ሎተሪ ኣንደኛ ዕጣ ኣሸናፊ በመሆን 1 ነጥብ 2 ሚሊዮን ብር ባለቤት ሆነ

Image
ነዋሪነቱ በኣለታ ወንዶ ከተማ የሆነው ወጣት ከፈለኝ ሞገስ በኣንድ ሆቴል ውስጥ በስጋ ቆራጭነት ይተዳደር የነበረ ሲሆን፤ የዕድል ሎተሪ ኣንደኛ ዕጣ ኣሸናፊ በመሆን 1 ሚሊዮን ሁለት መቶ ሺ ብር ቼክ ከብሄራዊ ሎተሪ ኣስተዳደሪ እጅ ተረክቧል። ወጣቱ በስነስርዓቱ ላይ ያሸነፈውን ገንዘብ ሳያባክን በሃዋሳ ከተማ ሆቴል ለመክፈት ማቀዱን ተናግሯል። የወራንቻ ኢንፎርሜሽን ኔትዎርክ ወጣት ከፈለኝን እንኳን ደስ ኣለህ ማለት ይወዳል።

“የሚፈልጉት የእምነት ቃል ነው” ማሰቃየት እና ጎጂ አያያዝ በኢትዮጵያ ማዕከላዊ ፖሊስ ጣቢያ

Image
የሪፖርቱ ይዘት ባጭሩ  አንዱ (ፖሊስ) በያዘው ረዥም ጥቁር ዱላ ከኋላ ጭንቅላቴን መታኝ ከዚያ አይኔን በጨርቅ  አሰረኝ፤ በመቀጠል ወደ ቢሯቸው ወሰዱኝ፤ ይህንን ያደረጉት መርማሪዎቹ ናቸው…ደጋግመው  በጥፊ መቱኝ፡፡ የምነግራቸውን ለመስማት መርማሪዎቹ ዝግጁ አይደሉም፤ በጥቁሩ ዱላ እና  በጥፊ ደግመው መቱኝ። እዚያው ክፍል እስከ እኩለ ሌሊት ድረስ አቆዩኝ፤ በጣም ተዳክሜ  ነበር። ከዚያ ወደ ታሰርኩበት ክፍል መለሱኝ እና ሌላ ሰው ወሰዱ፡፡ በሁለተኛው ቀን  ምርመራ ድብደባው የባሰ ነበር። የሚፈልጉት ጥፋተኛ ነኝ ብየ እንዳምን ነው ፡፡  በ2003ዓ.ም ዓመት አጋማሽ ማዕከላዊ ታስሮ የነበረ ጋዜጠኛ - ናይሮቢ፣ ሚያዚያ 2004ዓ.ም  በኢትዮጵያ ዋና ከተማ አዲስ አበባ መሃል ከአንድ ሆቴል እና አንድ የኦርቶዶክስ ቤቴክርስቲያን አጠገብ በመላ ሃገሪቱ በጣም  ታዋቂ የሆነ አንድ ፖሊስ ጣቢያ ይገኛል።ይህም የፌዴራል ፖሊስ ወንጀል ምርመራ ዘርፍ ሲሆን በተለምዶ ማዕከላዊ  በመባል ይታወቃል። ተቃዋሚ ፖለቲከኞች፣ ጋዜጠኞች፣ የተቃውሞ ሰልፍ አደራጆች፣ በብሄር የተደራጁ አማፅያንን  ይደግፋሉ የሚባሉ ሰዎች እና ሌሎችም በርካታ የኢትዮጵያ የፖለቲካ እስረኞች ሲያዙ በቅድሚያ የሚወሰዱት ወደ ማዕከላዊ  ነው፡፡ ማዕከላዊ ከገቡ በኋላ ምርመራ ይካሄድባቸዋል። በአብዛኞቹ ላይ ደግሞ ሁሉም ዓይነት እንግልት እና በደል  የሚደርስባቸው ሲሆን ይህም ማሰቃየትን ይጨምራል፡፡  በማዕከላዊ የሚገኙት መርማሪ ፖሊሶች ታሳሪዎች ጥፋታቸውን እንዲያምኑ፣ እንዲናገሩ ወይም ሌላ መረጃ እንዲያወጡ  የሚያደርጉት በሃይል የማስፈራራት መንገድን በመጠቀም ሲሆን ይህም እስከ ማሰቃየት እና ሌላ ጎጂ አያያዝ እስከ መፈጸም  ይደርሳል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እስረኞ

አዲሱ የጉድጓድ ውሃ መቆፈሪያ ቴክኖሎጂ እና በሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ ነዋሪ የሆነው የአቶ በቀለ ፉኤ ታሪክ

Image
አዲሱ የጉድጓድ ውሃ መቆፈሪያ ቴክኖሎጂ -ለመጠጥ ውሃ አቅርቦት ተደራሽነት አዲሱ የጉድጓድ ውሃ መቆፈሪያ ቴክኖሎጂ  50  ሜትር ጥልቀት ድረስ መቆፈር የሚያስችል ነው፤ ኑሮውን በውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ሥራ ላይ ያደረገው የ 42  ዓመቱ አቶ በቀለ ፉኤ በሕይወት ዘመኑ በርካታ ነገሮችን አይቷል። በተለይም ከሥራው ጋር በተያያዘ ብዙ ፈተና አሳልፏል። ወገቡን በገመድ ታስሮ ቁልቁል የጉድጓድ ውሃ ሲቆፈር መሬት ተደርምሶ አፈር ተጭኖት በሰዎች ዕርዳታ ከሞት ተርፏል። ጥልቀት ያለው ጉድጓድ ቆፍሮ ውስጥ እንዳለ አየር አጥሮት ራሱን ስቷል። ወገቡን ታስሮ ቁልቁል የተላከበት ገመድ ተበጥሶ ሕይወቱ አደጋ ላይ ወድቋል። በደቡብ ብሔር፣ ብሔረሰቦችና ሕዝቦች ክልላዊ መንግሥት ሲዳማ ዞን ሁላ ወረዳ ነዋሪ የሆነው አቶ በቀለ እንጀራ ሆኖበት እንጂ የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ሥራው በሞትና በሕይወት መካከል ያለ ነገር እንደሆነ ያምናል። የእለት ጉርሱን ከመሙላት አልፎ ቤተሰቡን የሚያስተዳድረው በእዚህ ሕይወትን የሚፈትን ሥራ ላይ ተሰማርቶ ነው። ሥራውን ለመተው ፍላጐት አለው። በርካታ ጊዜም የጉድጓድ ውሃ ቁፋሮ ሥራ እንዲሠራላቸው ጥያቄ ያቀረቡለትን ደንበኞቹን ጥያቄ ሳይቀበልም ቀርቷል።  « የጉድጓድ ውሃ የሚቆፍሩ አባቶች ልጆቻቸውን ስመው ነው ቁፋሮ የሚጀምሩት። እኔም ልጆቼን ስሜ ተሰናብቼ ብዙ ጊዜ ሥራዬን ጀምሬያለሁ። ፈተና እያለፍኩ እዚህ ደርሻለሁ። አሁን እግዚአብሄር የተመሰገነ ይሁን ለእጅ ውሃ ጉድጓድ ቁፋሮ ወደጉድጓድ መግባት ቀርቶልኛል » ሲል ይናገራል። አሁን የአቶ በቀለ ሥራ አስጊነት ምን ዋስትና አግኝቶ ነው በቀለ ለአምላኩ ምሥጋናውን ለማቅረብ የበቃው ?  ብለን ስንጠይቅ ቀላል በሆነ ቴክኖሎጂ በእጅ የሚሠራ የውሃ ጉድጓድ ለመቆፈር የሚያስችል መሣሪያ በመፈጠሩ ነው።

በሃዋሳ ስም የተሰዬመችው የኢትዮጵያ ንግድ መርከብ በቅርብ ወራት ውስጥ ነዳጅ መጫን ትጀምራለች

Image
Ethiopia: New Ethiopian Ships to Carry Petroleum in Early 2014 The Ethiopian Shipping Lines & Logistics Service Enterprise's (ESLSE) two new petroleum carrying ships will finally go into business in early 2014. This comes after a year of carrying other goods, pending a deal to be concluded with the Ethiopian Petroleum Enterprise (EPE). To date, petroleum suppliers in the Gulf were also responsible for transporting the product. As the current contract is now approaching its closing date, the EPE has told these suppliers to make their new offers excluding transport, said Abayneh Awol, fuel supply manager at the EPE. These companies include - Kuwait Independent Petroleum Corporation and the Saudi-based Bekri International Petroleum. The Sudanese Petroleum Corporation supplies an overland transport service. The shipping enterprise ordered a total of nine vessels fromChina, at a total cost of 300 million dollars, in 2010. They have already received eight of them, with the

Ethiopia's first marathon draws crowds to 'land of runners'

Image
Photo from  http://sports.yahoo.com/news/ethiopias-first-marathon-draws-crowds-land-runners-165923969--spt.html   HAWASSA: The sun had barely risen but the cool morning air was buzzing with excitement: 350 participants had gathered in Ethiopia, the land of runners, for the country's first international marathon organised by athletics legend Haile Gebrselassie.  Sunday's race, which drew 150 elite Ethiopian athletes and about 150 foreign "fun runners", promises to boost professionalism in a country that has produced scores of world-class runners, many of whom started running barefoot along dusty country roads.  "Believe me, we can produce more big names, we can produce more marathon runners, more Olympic champions, world champion and world record holders," said Gebrselassie, two-time marathon record-breaker and 10,000 Olympic champion.  Race organisers sought to draw Ethiopia's top athletes to the race in Hawassa, 275 kilometres (170 miles) south o

በኣገሪቱ ከፍተኛ ወታደራዊ እርከኖች ላይ የሲዳማ ብሄር ተወላጆች ኣሉ?

Image
Photo from Internet እንደምታወቀው የሲዳማ ህዝብ ካለው ከፍተኛ የህዝብ ብዛት የተነሳ በተለያዩ ጊዜያት በኣገሪቱ ህዝባዊ ስራዊት ውስጥ እየተመለመለ በፍቃደኝነት የሰራዊቱ ኣባል የምሆነው የሲዳማ ተወላጆች ቁጥር ከፍተኛ ነው። ሲዳማውያን በኣገሪቱ ጦር ሰራዊት በብዛት ከመሳተፍ ባለፈ በተለያዩ የጦር ሜዳ ውጊያዎችን ኣኩር ድሎችን በማስመዝገብ ዝና የተረፉ ናቸው። ሲዳማውያን የኣገሪቱን ህገመንግስት በመጠበቅ ብሎም የኣገሪቱን ሎዕላዊነት በማስከበር ለህገመንግስቱ መከበር ያላቸውን የማወላዳ ኣቋም በተለያዩ ጊዚያት ኣሳይተዋል። ነገር ግን ባለፉት ኣንድ መቶ  ኣመታት ሲዳማዎች በኣገሪቱ ጦር ሰራዊት ውስጥ ያለ ማቋረጥ የተሳተፉ ሆኖ ሳለ በከፍተኛ ወታደራዊ ማዕረግ ወይም በከፍተኛ ወታደራዊ ኣመራርነት ስማቸው የምጠቀሱ ሲዳማዎች ብዙ ኣይደሉም ምክንያቱ ምን ይሁን?ለኣብነት ያህል በኣጭር ጊዜ ውስጥ በተደጋጋሚ የኣገሪቱ መንግስት ለከፍተኛ ወታደራዊ መኮንኖች ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመቶችን መስጠቱ የምታወስ ሲሆን፤ በእነዚህ ከፍተኛ ወታደራዊ ሹመቶች ውስጥ ምን ያህል የሲዳማ ተወላጅ ተካተው ይሁን ? መረጃው ያላችው ጀባ በሉን።

ከሀዋሳ ዲላ ያለው መንገድ ስራ እስኪጠናቀቅ ነሪዎች ትብብር እንዲያደርጉ ጥሪ ቀረበ

Image
አዲስ አበባ፣ ጥቅምት 8፣ 2006 (ኤፍ ቢ ሲ)  ከሀዋሳ ዲላ ያለው መንገድ ርዝመቱ 90 ኪሎ ሜትር ይደርሳል ። ይህ መንገድ ከተማዎቹን አቋርጠው ለሚወጡ የንግድና የማህበራዊ አገልግሎቶች ከፍተኛ ደርሻ አለው። መንገዱ ረዘም ላለ አመታት ያገለገለና ጠንካራ ጥገናም ያልተደረገለት ነው። አሁን ላይ መንገዱ ለረጅም ጊዜ ከማገልገሉ ጋር ተያይዞ አገልግሎት መስጠት የማይችለበት ደረጃ ላይ መድረሱን በመንገዱ የሚገለገሉ ሰዎች ይናገራሉ። የአካባቢው ነዋሪዎች መንገዱን ለዚህ ያደረሰው አልፎ አልፎ  የሚደረግለት  መጠነኛ ጥገና በመቋረጡ  ባጠቃላይ ለአንቅስቃሴ አስቸግሯል ባይ ናቸው። አንዳንዴ ለመኪኖች የርእስ በእርስ ግጭትም ምክንያት መሆኑን ነዋሪዎቹ ይናገራሉ። ከዚህ ባለፈም የመንገዱ ምቹ አለመሆን የተሽከርካሪ እቃዎች ላይ የሚያደርሰው ችግርን የከፋ አድርጎታል። ባለንብረቶችም ይህም  ያሳሰበ ጉዳይ ሆኖብናል እናም የሚመለከተው አካል መፍትሄ እንዲሰጠው ይላሉ። በኢትዮጵያ መንገዶች ባለስልጣን የህዝብ ግንኙነት ዳይሬክተር  አቶ ሳምሶን ወንድሙ  እንደሚሉት ከሀዋሳ በሀገረ ማርያም እስከሞያሌ የሚደርስ መንገድ አለ። ይህ መንገድ ደግሞ በስድስት ኮንትራክተሮች ተከፋፍሎ የሚሰራ ሲሆን አሁን ቅሬታ የተነሳበት ከሀዋሳ እስከ ዲላ ያለው መንገድም  ከሀዋሳ ሀገረ ማርያም በሚደርሰው የመንገድ ከፍል ግንባታው በያዝነው አመት የተጀመረ ነው ይላሉ። በርግጥ አሁን ከሀዋሳ እስከዲላ ያለው መንገድ ረዘም ላሉ አመታት የአገልግሎት የሰጠ መሆኑን የሚያስታውሱት አቶ ሳምሶን ይህ ደግሞ መንገዱ አሁን መስጠት የሚገባውን አገልግሎት እንዳይሰጥ አድርጎታል ባይ ናቸው። በመሆኑም በነዋሪው የሚነሳው ቅሬታ ተገቢ መሆኑ ላይ ይስማማሉ። አቶ ሳምሶን  ይህ መንገድ ከፍተ

ነገ በሚካሄደው በሃዋሳው የኃይሌ ገብረ ሥላሴ ማራቶን አሸናፊዎች 100 ሺሕ ብር ይሸለማሉ

Image
ለመጀመሪያ ጊዜ በሐዋሳ ከተማ ዛሬ ጥቅምት 10 ቀን 2006 ዓ.ም. በሚካሄደው የኃይሌ ገብረ ሥላሴ ማራቶን በሁለቱም ጾታዎች አሸናፊ ለሚሆኑት አትሌቶች ለያንዳንዳቸው የ100 ሺሕ ብር ሽልማት እንደሚሰጥ አዘጋጁ ታላቁ ሩጫ በኢትዮጵያ አስታወቀ፡፡ አዘጋጁ አክሎ እንደገለጸው በሐዋሳው የኃይሌ ማራቶን በወንዶች ከ2 ሰዓት 12 ደቂቃ በታች፣ በሴቶች ከ2 ሰዓት 30 ደቂቃ በታች በማሸነፍ ክብረ ወሰን ለሰበረ ተጨማሪ 100 ሺሕ ብር ጉርሻ ይሸለማል፡፡ 20 OCTOBER 2013 ተጻፈ በ   በጋዜጣው ሪፖርተር

የኢትዮጵያ መንግስት የፖለቲካ ተቃዋሚዎችን እንደምያሰቃይ የሰብኣዊ መብት ጥበቃ ድርጅት (Human Rights Watch)ኣስታወቀ

Image
HRW: Abuse is a political weapon in Ethiopia Photo@ Internet NAIR, Kenya, Oct. 18 (UPI) --  Ethiopian authorities are using torture and other forms of mistreatment to quiet the voice of opposition, Human Rights Watch said in a report Friday. "Ethiopian authorities right in the heart of the capital regularly use abuse to gather information," Leslie Lefkow, deputy director of African programs at Human Rights Watch, said Friday. Her organization published a 70-page report documenting serious human rights abuses committed by a national police force since 2010. Those detained by a federal police force, known as Maekelawi, reportedly abused opposition leaders, civil activists and journalists at their main detention center in Ethiopia's capital, Addis Ababa. Lefkow said Ethiopian authorities were using restrictive legal measures as justification for arbitrary arrest and political prosecution. This was in addition to the claims of prisoner abuse. Detainees Human

የሲዳማ ቡና ኣምራቾች በዚህ ኣመት የቡና ገበያ የተሻለ ገቢ እንዲያገኙ የዞኑ መንግስት የተለያዩ የገበያ ኣማራጮችን መፍጠር ይጠበቅበታል

Image
Photo:  James Jeffrey/IRIN የሲዳማ ዞን በኢትዮጵያ ከኦሮሚያ ክልል ቀጥሎ ከፍተኛ የቡና ምርት የምመረትባት ዞን ናት። ኣብዛኛው ማለትም ወደ 80 ከመቶ የምሆነው የዞኑ ነዋሪ ኑሮውን የምደግፈው በግብሪና ስራ ላይ ተሰማርተው ሲሆን፤ የቡና ምርት በዞኑ ውስጥ ከዌሴ ምርት ቀጥሎ በግንባር ቀደምትነት በመመረቱ የሚጠቀስ ነው። ሲዳማዎች በስማቸው በምጠራው የቡና ኣይነት ወይም የቡና ምርት ምልክት / መጠሪያ በኣለም ላይ የሚታወቁ ሲሆን፤ በቡና ምርታቸው የምታወቁት ያህል ከሽያጩ ተጠቃሚ ኣይደሉም። የኣለምን የቡና ገበያ የተመለከቱ መረጃዎች እንደምያሳዩት ከሆነ፤ በቡና ምርት ሽያጭ ከፍተኛ ገቢ በማጋበስ ላይ የምገኙት የሲዳማ ቡና ኣምራቾች ሳይሆኑ የሲዳማን ቡና ቆልተው እና ፈጭተው የሚቸረችሩ ኩባኒያዎች ናቸው። እነዚህ ኩባኒያዎች ከሲዳማ ቡና ኣምራቾች በዝቅተኛ ዋጋ የሚገዙትን ቡና በመሸጥ በሚያገኙት ዳጎስ ያለ ገንዘብ ከጊዜ ወደ ጊዜ ኢኮኖሚያቸውን እያፈረጠሙ ሲሆን፤ የሲዳማ ኣርሶ ኣደሮች ግን ከምርታቸው ተጠቃሚ ካለመሆናቸው የተነሳ በሚያጋጥማቸው ኢኮኖሚያዊ ችግር የቀን ተቀን ኑሮ ኣስቸጋሪ እየሆነባቸው ነው። ከቅርብ ኣመታት ወዲህ በጉዳዩ ዙሪያ መንግስት የተለያዩ እርምጃዎችን የወሰደ ሲሆን፤ የቡና ኣምራቾችን በማህበር በማደራጀት በኢትዮጵያ የምርት ገበያ በኩል የቡና ኣምራች ማህበራቱ ምርቶቻቸውን በቀጥታ ለኣለም ገበያ እንድያቀርቡ መደረጉን እንደኣብነት ማንሳት ይቻላል። ይህ የመንግስት እርምጃ የማህበራቱ ገብ በኣንጻሩ ያሳደገው ብሆንም በቡና ኣምራች ኣርሶ ኣደሩ ገብ ላይ ያመጣው ለውጥ ይህን ያህል ነው። በኢትዮጵያ፤ ፓናማ እና ኢልሳልቫዶር በብሄራዊ የቡና ማህበራት በኣማካሪነት ያገለገሉት ካላ ዊልያም ቦልት እንደምሉት ከሆነ፦

ሰለ እሁዱ የሃዋሳው ማራቶን በተመለከተ ኣንዳንድ ጠቃሚ ጥብጦች

Image
The races will be held entirely within the city limits of Hawassa and be contested on a flat, accurate, two-loop course (one loop for the half marathoners). Other than a short stretch on a hard-packed dirt road, the race will be on pavement with plenty of aid stations with purified water and sports drinks, as well as native musicians along the course. The start/finish of the races are within easy walking distance of the race hotels.  Course Information and Description The Haile Gebrselassie Marathon, to be held on October 20, 2013 in Hawassa, Ethiopia, will be on a two-lap course. Each lap of the citywide course will be 13.1 miles. Half-marathoners and marathoners will start together at the convenient start/finish which is located two miles from the center of Hawassa, and within two miles of any of the race hotels. Transportation will be provided to and from the start/finish to any hotel more than a kilometer away. The 13.1-mile lap is almost entirely on well-paved