የምርት ገበያው ደካማ አሠራር ቡና አቅራቢውን እያኮላሸው መሆኑ ተገለጸ
የምርት ገበያው ደካማ አሠራር ቡና አቅራቢውን እያኮላሸው መሆኑ ተገለጸ የጽሑፍ መጠን ኢሜይል 0 አስተያየት шаблоны RocketTheme Форум вебмастеров የኢትዮጵያ ምርት ገበያ አሠራር ችግር እየፈጠረባቸውና ለከፍተኛ ኪሳራ እየዳረጋቸው መሆኑን የቡና አቅራቢዎች በተደጋጋሚ ሲገልጹ መቆየታቸው የሚታወቅ ሲሆን በተለይ የሲዳማ ቡና አቅራቢዎች ማኅበር ለችግሩ መፍትሔ እንዲሰጠው ጥያቄ ማቅረቡ ታውቋል፡፡ ማኅበሩ በቅርቡ በሐዋሳ ከተማ ባካሄደው ስብሰባ፣ በሐዋሳ የሚገኘው የምርት ገበያው ማዕከል፣ አደረሰብን ያሉትን ችግር በዝርዝር በማስቀመጥ፣ ይህንን ችግር እንዲፈታላቸው ለመንግሥት አቤት ብለዋል፡፡ በስብሰባው ወቅት እንደተገለጸውና መንግሥት እንዲያውቅልን በማለት በጽሑፍ ያዘጋጁት መረጃ እንደሚያሳየው፣ ችግሩ ከአገልግሎት አሰጣጥ ጀምሮ የተዛባ የቡና ጥራት ደረጃ አሰጣጥን የሚያጠቃልል ነው፡፡ የቡና ደረጃ አሰጣጥ ላይ ያለው የተዘበራረቀ አሠራር ከአቅማችን በላይ ሆኗል የሚሉት የማኅበሩ አባላት፣ ደረጃውን ጠብቆ የተዘጋጀ ቡና በአንዱ የምርት ገበያው ማዕከል ባለሙያዎች የተሰጠው ደረጃ በሌሎች ማዕከሎች ግን ደረጃውን አልጠበቀም ተብሎ ይጣልባቸዋል፡፡ ባለፉት ሁለት ወራት የሐዋሳው የምርት ገበያ መጋዘን ጥበት አጋጥሞታል በመባሉ ወደ አዲስ አበባ የላኩት ቡና፣ ሐዋሳ ላይ ደረጃ አምስት ተብሎ አዲስ አበባ ላይ ግን በጥራቱ የደረጃ ሁለት ማዕረግ እንደተሰጠ የተመደበ ሲሆን ለአብነት ጠቅሰዋል፡፡ እንዲህ ባሉ አግባብ ያልሆኑ አሠራሮች ምክንያት የቡና ላኪዎች ጉዳት ላይ እየወደቁ መሆናቸውን አስረድተዋል፡፡ በዚህም ችግር አንድ ቡና አቅራቢ ድርጅት በአንድ መኪና በግምት ከ80 እስከ 100 ሺሕ ብር እየከሰረ